በርካታ መጠን ያላቸው የውጭ ሀገራት ገንዘቦችን በማተምና ጥቁር ገበያን በማስፋፋት ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡ። ተጠርጣሪዎቹ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ተረኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበው ጉዳያቸው ታይቷል።
የፀሃይ ሪል ስቴት ዋና ስራ አስኪያጅ ኪያ ዦንግን ጨምሮ ዘጠኝ የውጭ ሀገራት ዜጎች እና ሶስት ኢትዮጵውያን ተጠርጣሪዎች ናቸው ፍርድ ቤት የቀረቡት።
መርማሪ ፖሊስ ግለሰቦቹ በርካታ መጠን ያላቸው የውጭ ሀገራት ገንዘቦችን በማተምና ጥቁር ገበያን በማስፋፋት ወንጀል መጠርጠራቸውን ለችሎቱ አስረድቷል፡፡
በቁጥጥር ስር በዋሉበት ወቅትም የተለያዩ የውጭ ሀገራት ገንዘቦች የሚታተሙባቸው ማተሚያ ማሽኖችና ለግብዓት የሚያገለግሉ ኬሚካሎች እንዲሁም በርካታ ዩሮ፣ የአሜሪካ ዶላርና የሌሎች ሀገራት ገንዘቦች መያዙን ፖሊስ ጠቅሷል።
ተጠርጣሪዎቹ ላይ የተጀመሩ ሰፊ የምርመራ ስራዎችን አከናውኖ እና የተናጠል ተሳትፏቸውን ለይቶ ለመቅረብም የ14 ቀን ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል። ከአራተኛ ተጠርጣሪ ውጪ ያሉ ግለሰቦች ከወንጀል ድርጊቱ ጋር ግንኙነት እንደሌላቸው ገልጸዋል።
በተጨማሪም የተጠርጣሪዎቹ ጠበቆች የግለሰቦቹ የወንጀል ተሳትፎ ባልተገለጸበት ሁኔታ ላይ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ሊሰጥ አይገባም ሲሉ ተከራክረዋል።
የፀሃይ ሪል ስቴት ዋና ስራ አስኪያጅ ኪያ ዦንግን የተባሉት ግለሰብ በበኩላቸው÷ የተገኘው የውጭ ሀገራት ገንዘብ ማተሚያ በእርሳቸው ቤትና ቢሮ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የወንጀል ድርጊቱ የሚገናኘው ከእርሳቸው ጋር ብቻ መሆኑን ገልጸው÷ ሌሎች ተጠርጣሪዎች ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት እንደሌላቸው ለችሎቹ አብራርተዋል።
መርማሪ ፖሊስ በበኩሉ÷ ተሳትፏቸው አልተገለጸም ተብሎ የተነሳውን መከራከሪያ በሚመለከት በቀጣይ ተሳትፏቸውን ለይቶ በስፋት ምርመራውን አከናውኖ እንደሚቀርብ ገልጾ መልስ ሰጥቷል።
የግራ ቀኙን ክርክር የተከታተለው ጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ ተጠርጣሪዎች ላይ ተጨማሪ የማጣሪያ ምርመራ መደረግ እንዳለበት በማመን የተጠርጣሪዎቹን የዋስትና ጥያቄ ለጊዜው ውድቅ አድርጎታል።
ፖሊስ በቀጣይ ቀጠሮ የተጠርጣሪዎችን የወንጀል ተሳትፎ ለይቶ እንዲያቀርብ ከነሐሴ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የሚታሰብ የ12 ቀን የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል።
በሌላ በኩል ፍርድ ቤቱ ተጠርጣሪዎቹ ከቤተሰብ ጋር እንዲገናኙ እና ሕክምና ማግኘት የሚፈልጉም ሕክምና እንዲያገኙ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
በታሪክ አዱኛ FBC
- ምን ያክል ተዘጋጅተናል? ጥድፊያ አገር አልባ ለመሆን !! ህጻናቱ ምን አጠፉ?ያለፈውን ግማሽ ምዕተ ዓመት የኢትዮጵያ ፖለቲካ እና ሥነ መንግሥት ታሪክ በጥሞና የተከታተለ ኢትዮጵያዊ የግዛት አንድነቷን እና የፖለቲካ ነጻነቷን በአንጻሩ… Read more: ምን ያክል ተዘጋጅተናል? ጥድፊያ አገር አልባ ለመሆን !! ህጻናቱ ምን አጠፉ?
- የደም ግፊት በመለካትና ክትትል በማድረግ የስትሮክ ተጋላጭነትን መቀነስአንድ ሰው የደም ግፊት መጠኑ ከፍተኛ ከሆነ እና በጊዜው ሕክምና ካላደረገ ለከፍተኛ የልብ በሽታና በደም ዝውውር ማነስ ምክንያት ለሚከሰት… Read more: የደም ግፊት በመለካትና ክትትል በማድረግ የስትሮክ ተጋላጭነትን መቀነስ
- የስኳር ህመም አይነቶች እና ምልክቶችየስኳር ህመም በደም ውስጥ የስኳር መጠን ከሚገባው በላይ ሆኖ በሚገኝበት ሰዓት የሚከሰት ተላላፊ ያልሆነ የህመም አይነት ነው። በዋናነት አራት… Read more: የስኳር ህመም አይነቶች እና ምልክቶች
- ማንኮራፋትና ትዳርን እስከ ማፍረስ የሚያደርሰው መዘዙ ? ማንኮራፋት መፍትሄ አለው?የማንኮራፍት መዘዙ እንቅልፍ ማሳጣት ብቻ አይደለም። ማንኮራፋት ከሚያንኮራፉት ሰዎች ጎን በሚተኙ ሰዎች አካላዊ እና አእምሮ ጤና ላይ ጉዳት ያስከትላል።… Read more: ማንኮራፋትና ትዳርን እስከ ማፍረስ የሚያደርሰው መዘዙ ? ማንኮራፋት መፍትሄ አለው?
- Ethiopia Working To Secure New Development Bank MembershipThe Ministry of Foreign Affairs disclosed that Ethiopia is working hard to become member of BRICS’ New Development Bank.… Read more: Ethiopia Working To Secure New Development Bank Membership