ኢትዮጵያን እየወጉ ያሉት በትግራይ በዕርዳታ ስም የገቡ ከፍተኛ ክፍያ የሚከፈላቸው ስውር ኤጀንቶች መሆናቸው ተሰማ። እነዚሁ ኤጀንቶች አስቀድመው ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጡት የራሳቸውን የሳተላይት መገናኛ መሆኑ የዚሁ ማረጋገጫ አንዱ ማሳያ ሲሆን አገባባቸው ቁንጮ የትህነግ ሰዎችን በሱዳን በኩል ለማስወጣት ነበር።
ግጭት ባለበት ቦታና አገራት ሁሉ በከፍተኛ የክፍያ ስምምነት በማድረግ በተለያዩ ተቋማትና ሰብአዊ ድጋፍ ሰጪነት ስም የተለያዩ የኦፕሪሽን ማካሄድ የተለመደ ተግባራቸው ከሆኑት ኤጀንቶች መካከል የሚታወቁ በትግራይ መከተማቸውን ያመለከቱት ጉዳዩን የሚከታተሉ ዜጋ ናቸው።
በዕርዳታ ስም ትግራይን ያጥለቀለቁት እነዚሁ ተከፋይ ኤጀንቶች የትኛው የስለላ ተቋም እንደላካቸውና ስም መጠቀሱ ለጊዜው አግባብ እንደማይሆን የጠቆሙት አገር ወዳድ፣ እነዚህ ኢጀንቶች የትህነግን የተበጣጠሰ ሃይል ዘመናዊ መገናኛ በማስታጠቅ ዳግም የግንኙነት ሰንሰለት እንደገነቡላቸው ይናገራሉ።
“እጀባና ክትትል አይስፈልገንም” በሚል በረሃ ከመሸገው ሃይል ጋር እንዳሻቸው ሲገናኙ የቆዩትና የሳተላይት ግንኙነት መስርተው የኢትዮጵያን መከላከያ ሰራዊት የሃይል አሰላለፍ ሲከታተሉ እንደነበር መረጃውን ያጋሩት አመልክተዋል። መከላከያ እያዋዛ ነቅሎ ሲወጣ በስተመጨረሻ መረጃ የተሰጠው በዚሁ በዓለም አቀፉ የግንኙነት መስመር ምክንያት እንደሆነ ጨምረው ገልጸዋል።
በውጭ አገር ከትህነግ ሰዎች ጋር ተደራድሮ በለጋሽነት ስም የገባው ኤጀንት አስቀድሞ እርምጃ የተወሰደባቸውንና የተማረኩትን የትህነግ ቁልፍ ሰዎች ከትግራይ ለማስወጣት ስምምነት ነበረው። በአሜሪካ ከትህንግ ሴል ጋር ባለ ግንኙነት መነሻ ያገኙትን መረጃ ያጋሩን እንደገለጹት የነዚህ ኤጀንቶች ክፍያ ከፍተኛ በመሆኑ፣ ትግራይን የሚወዱ ሁሉ በመልሶ ግንባታ ስም መዋጮ እያሰባሰቡ ነው። እነዚህ ኤጀንቶች የዲፖሎማሲው ጫና እንዲበረከት ከማድረግ ጀመሮ ለተመረጡ ባለልጣናት የመሳሪያ ጥቃት እንዳይደርስባቸው ኔትዎርክድ የሆነ ከላለና ጥበቃም ይሰጣሉ።
ኤጀንቶቹ በተደጋጋሚ በሲዳን በኩል ነጻ ኮሪዶር እንዲከፈት ደጋግመው የሚጠይቁና በዚሁ ስራቸው ባላቸው የዲፕሎማሲ መስመር ሁሉ ጫና እንደሚፈጥሩ ዜናውን ያጋሩን ገልጸዋል። ” የሻቸውን ደብዳቤና መግለጫ ከፈለጉት ክፍል እንዲወጣና ለጫና እንዲውል መጠቀሚያ ማድረግ ይችላሉ” ያሉዋቸው ኤጀንቶች እጃቸው የትኛውም ዓለም ዓቀፍ ተቋምና አገራት መሪዎች ዘንድ እንደሚደርስ፣ ሰውር የሚመስል ግን ግልጽ ግንኙነት እንዳላቸው አመልክተዋል።
እነዚህ ኤጀንቶች ባስገቡት ኢትዮጵያ የማትቆጣጠረው ዓለም ዓቀፍ የግንኙነት ቻናል ወታደራዊ ድጋፍ ማድረግ የሚያስችል መረጃ ከአጋሮቻቸው በድሳተላይት እየተቀበሉ ጦርነቱን እንደሚያግዙ ከጥቆማ ሰጪዎቹ ማብራሪያ ለመረዳት ተችሏል። እነዚህ አካላት ተግባራቸው ጫና እየፈተሩ ባሉ አገራትና ዓለም ዓቀፍ ተቋማት በገሃድ የሚታወቅ በመሆኑ ኢትዮጵያ እርምጃ ብትወስድባቸው ምንም የሚመጣ ችግር ሊፈጠር እንደማይችል ሊሎች አገሮች ለተመሳሳይ ተግባር ገብተው እርምጃ የተሰውሰደባቸው መኖራቸውን አመስዳክረው ገልጸዋል።
ትህነግ ሰፊ ሚሊሻና ሃይል አደራጅቶ፣ ወደ ሱዳን የሸሹትንና ሱዳን ውስጥ ግብጽ ያስታጠቀቻቸውን ሃይሎች ለማገናኘት የሱዳን ኮሪዶር እንዲከፈትለት ያለ የሌለ ሃይሉን እያስተባበረ እንደሆነ የትህነግ ታማኝ የውጭ ሚዲያዎች እየዘገቡ ነው። አሜሪካ በተደጋጋሚ ” አማራ” ብላ በመጥራት ይህ ኮሪዶር እንዲከፈት ዛቻ እያሰማች ነው። አውሮፓ ህብረትም በተመሳሳይ እነድ አሜሪካ እየዛት ሲሆን ዓለም አቀፍ ተቋማት ደግሞ ለዕርዳታ ሲባል ኮሪዶሩ እንዲከፈት እየጠየቁ ነው። መንግስት በበኩሉ ” ይህ ጊዜው ያለፈበት ስልት ነው” ሲል ጥያቄውን አይቀበልም። ይሁንና ሰብአዊ ደጋፍ እንዲዳረስ አስፈላጊውን ቁጥጥር እያደረገ የሚፈለገውን የተቸገሩትን የመረዳት ሂደት እንደሚያግዝ አመልክቷል። ነጻ በረራ ወደትግራይ የሚባለውንም ውድቅ በማድረግ አዲስ አበባ ፍተሻ ተደርጎ ወደ ትግራይ መብረር እንደሚችላ አዲስ የአሰራር መመሪያ አውጥቷል።
- የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ዳግም ዝርፊያ እያፈጸሙ ነው፤ የተማሪዎች መጽሃትን “የአማራ ክልል ናቸው እየሉ ቀደዋል”በአላማጣ ከተማ በተለየ መልኩ የትግራይ ክልል ታጣቂዎች በከተማዋ ውስጥ እንደሚንቀሳቀሱ ነዋሪዎች መመስከራቸውን ቢቢሲ አስታወቀ። ይህ የተገለጸው ከአለማጣ እና አካባቢው የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከሃምሳ… Read more: የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ዳግም ዝርፊያ እያፈጸሙ ነው፤ የተማሪዎች መጽሃትን “የአማራ ክልል ናቸው እየሉ ቀደዋል”
- በዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ችግኝ ልትተክል ነውለዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር 6 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል ዕቅድ መያዙንna ለዚህም ተግባራዊነት ከሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊየን በላይ ችግኝ መዘጋጀቱን ተገለጸ። 1… Read more: በዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ችግኝ ልትተክል ነው
- አፍሪካ ህብረት ” የውጭ ምንዛሪ ሒሳቡን ወደ ሌላ ሀገር ሊያዘዋውር ነው” የሚለው ዜና ሃሰት መሆኑን ህብረቱ አረጋግጠአፍሪካ ህብረት የውጭ ምንዛሬ አካውንቱን ወደ ሌላ አገር እንደሚያዘዋውር ተጠቅሶ በህብረቱ ስም የወጣው ዜና ሃሰት፣ ሆን ተብሎ የተቀነባበረ መሆኑን መንግስት አስታወቀ። መረጃው ቀድሞውንም… Read more: አፍሪካ ህብረት ” የውጭ ምንዛሪ ሒሳቡን ወደ ሌላ ሀገር ሊያዘዋውር ነው” የሚለው ዜና ሃሰት መሆኑን ህብረቱ አረጋግጠ
- አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎችባንኩ የክፍያ ሰነድ ቀረበለት። ማጣሪያ ጥያቄ ለህብረቱ አቀረበ። ሃሰት ሆኖ ተገኘና ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን ያዘ። ጉዳዩ ወደ ህግ አመራ። አሁን ምኑ ነው አፍሪካ ህብረትን… Read more: አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎች
- የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል 300 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ዕዳ አለብኝ አለ፤ ዕዳውና የክፍያው ጫና እንደከበደውም አስታውቋልየኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከንግድ ባንክ 300 ቢሊዮን ብር ዕዳ እንዳለበት ተገለጸ። የዕዳ ጫናውን ለማቃለል የባንክ ወልዱም ጭምር ተፅእኖ እያሳደረ መሆኑም ተመልክቷል። የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ… Read more: የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል 300 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ዕዳ አለብኝ አለ፤ ዕዳውና የክፍያው ጫና እንደከበደውም አስታውቋል