ህወሃት የሲቪል ልብስ አልብሶ የሚያዋጋቸውና በዋጅራት የተቆረጠው ሃይሉ ተደመሰሰ፤ «መከላከያ በስምንት ግንባሮች እርምጃ እየወሰደነው»ጠ.ሚ አብይ

ራሱን የትግራይ ህዝብ ነጻነት ግንባር እያለ የሚተራው ትህነግ ያደራጀው ሰራዊት ሲቪል ልብስ ለብሶ ለማጥቃት ሲንቀሳቀስ በድንገት በመከላከያ ሃይል መደምሰሱ ተሰማ። እህል ዝርፊያ ላይ የተሰማሩም እርምጃ ተወስዶባቸዋል።

የሀገር መከላከያ ሰራዊት በተለያዩ ግንባሮች በወሰዱት እርምጃ ጸረ- ህዝብ ሀይሎችን በከፍተኛ ደረጃ ማዳከም መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስተሩ በእንጦጦ ኦብዘርቫቶሪ በተካሄደ ደመናን የማዝነብ ቴክኖሎጂ ማስተዋወቂያ መርሃ ግብር ላይ እንደተናገሩት የፌደራል መንግስት ሀይሎች በስምንት ግንባሮች ጸረ ሰላም እና ጸረ ህዝብ ሀይሎች ላይ እርምጃ እየወሰዱ ይገኛሉ፡፡

በሒዋን የሚገኘውን የመብራት ሃይል ማስተላለፊያ ጣቢያ ለሶሰተኛ ጊዜ በማውደም ሲቪል በለበሱ የሚሊሻና የልዩ ሃይል አባላት ጥቃት ለማድረስ ተዘጋጅቶ የነበረው ሃይል መደምሰሱን የጠቆሙት ክፍሎች ” ሲዋጉ ሲቪል እንዲያደርጉ የተደረገው ሲመቱ ስለማዊ ዜጎች ሞቱ በሚል ለጩኸት እንዲያመች ነው” ብለዋል።

የተሰጠው የሳምንት ጊዜ በመጠናቀቁ፣ ሰራዊቱ ትንፋሽ ወስዶ ባደረገው የማጽዳት እርምጃ በዋጅራት ታላቅ የተባለ ጥቃት ተሰንዝሮ በትህነግ ሰራዊት ላይ ጉዳት ደርሷል።

ዋና አዋጊዎቹ ከተዋጊው ሰአራዊት አርባና ሃምሳ ኪሎሜትር እርቀው እንደሚደበቁ እጃቸውን የሰጡና የተማረኩ አመልክተዋል። ምንጫችን እንዳሉት አሁን በህይወት አሉ የሚባሉትን ተዋጊው አይቷቸው እንደማያውቅና “ትዕዛዝ መጣ” ሲባል ብቻ ነው የሚሰሙት።

በየበረሃው ተቆርጦ የተበተነው ሰራዊት ረሃብ ላይ እንደሆነ፣ አንዳንዱም ለምን ጫካ ውስጥ እንዳለ በደንብ የማያውቅና ለምን ዓላማ ዋጋ እንደሚከፍል እንደማያውቅ እጃቸውን ሲሰጡ አንዳንዶች መናጋራቸው ታውቋል።

ግዕዝ ሚዲያ “ሲቪል ለብሶ እንበር ተጋዳላይ እያለ እየተኮሰ የሚሮጥ ሲገደል ሲቪል ነበረ ሞተ ተብሎ የሚጮህለት ርዝራዥ ሽፍታ የጁንታ ህወሓት ታጣቂ በዛሬው ቀን በዋጅራት ጀግና መከላከያ ሰራዊታችን የማያዳግም እርምጃ ወስዶ ድል ተቀዳጅቷል” ሲል የቅርብ ሰዎቹን ጠቅሶ ዘግቧል። አክሎም ” ሽፍታው የገበሬ ቤት እየገባም በሃይል እህል ይዘርፋል። ርዝራዥ የጁንታ ታጣቂ በረሃብ አለንጋ እየተገረፈ በሰማይም በምድርም እሳት እየዘነበበት እየረገፈ ይገኛል። የትግራይ ህዝብ ልጆቹ ሊመክር ይገባ” ሲል ጥሪውን አቅርቧል። ኪሮስ ሚካኤል የማቻረ ሚሊሻ ፅህፈት ቤት ሃላፊ የነበረ መከላከያ በወሰደው የሽፍታ ማፅዳት እርምጃ ትላንት መገደሉን በማስረጃ ማረጋገጡን ገልጿል።

በተመሳሳይ ዜና የትህንግ ታጣቂዎች ከገበሬ ቤት እህል በሃይል እየዘረፍ፣ ከብት ከገበሬ እየነጠቁና እያረዱ እንደሚበሉ ፣መንግስት ወደ ህዝቡ የሚልከውን እርዳታም በመቀማት ተግባር መሰማራታቸው በስፋት ቅሬታ አቅራቢዎች እያስታወቁ ነው።

ከዚህ ቀደም አንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ በማውጣት ፋብሪካዎችን በማስጠገንና የወደመውን የመብራት አገልግሎት ሁለት ጊዜ በማስጠገን ወደ አገልግሎት መመለሱን፣ በርካታ ሰራተኞች ወደ ስራ ገበታቸው እየተመለሱ እንደሆነ፣ ለሰራተኞች የስራ ፈረቃ ሲባል የሰዓት እላፊ መሻሻሉን አስተዳደሩና ኮማንድ ፖስቱ ይፋ ባደረጉበት ማግስት የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያው ላይ ጉዳት መድረሱ ሰፊ መነጋገሪያ ሆኗል።

ትህንግ በኤሌክትሪክ ጣቢያው ላይ ያደረሰውን ውድመት ተከትሎ አገልግሎት ሰጪዎች፣ ሆስፒታሎችና ስራ የጀመሩ ፋብሪካዎች እንዲቆሙ አሰገድዷል። ይህም ሕዝቡ ወደ መደበኛ ሕይወቱ ለመመለስ የነበረውን ተስፋ ክፉኛ እንደጎዳ አስተያየት ሰጪዎች አስታውቀዋል።


 • ጃል መሮ በትግርኛ – ከትህነግ ጋር ሲመክር ተጠለፈ ” 70 ከመቶ ጨርሰናል አዲስ አበባ ነው የቀረን”
  የአሜሪካ ድምጽ ማንነቱን ሳይጠይቀውና ሳያውቅ ሰፊ ቃለ ምልልስ በተደጋጋሚ ሲያደርገልት የነበረው ጃል መሮ በትግርኛ ከትግራይ ስሙ ካልተገለጸ ባለስልጣን ጋር ስለሚያካሂዱት ኦፕሬሽን ሲመክሩና መረጃ ሲቀባበሉ የሚያስረዳ ድምጽ ሆነ። ሌላው ቢረሳ በኢሬቻ ብቻ ከስምንት መቶ ሰዎች በላይ ሰዎችን የጨረሰ ትህነግ ከመላው ኦሮሞ ጋር ህብረት እንደሌለው በማስረዳት በተዘጋጀው ዶክመንታሪ ዝርዝሩን ይመልከቱ። ኦሮሞ በሃዘንናContinue Reading
 • “ወታደራዊውን ጉዳይ ለእኛ ተውልን” ሌ/ጄ አበባው ታደሰ
  “እናንተ ደጀን በመሆን ከጀርባችን ሁኑልን እንጂ ወታደራዊ ጥበቡን ለእኛ ተውልን” የጦር ኃይሎች ምክትል ኤታምዦር ሹም ሌ/ጄ አበባው ታደሰ ማስታወቃቸው ተሰምቷል። መከላከያ ሰራዊትንም ሆነ ደጀኑንን ሕዝብ በወሬ ለማተራመስ ተከፍሏቸው የሚሰሩ፣ አገር ወዳድ መስለው የሚቀስቀሱና በባንዳነት አገር እያስመቱ ያሉ ላይ ሕዝብ እርምጃ እየወሰደ መሆኑም ተሰምቷል። ጠላትንም ለመመከት ህዝብ እየጎረፈ ነው። “ኢትዮዽያ እየሞትንContinue Reading
 • አሜሪካ የባድመ ጉዳይ በውሳኔው መሰረት ተግባራዊ እንዲሆን ጥሪ ማቅረቧን አስታወቀች
  አሜሪካ የባድመ ጉዳይ ሁለቱ አገሮች ቀደም ሲል በ2008 የድንበር ኮሚሽኑ ውሳኔ በደረሱበት ስምምነት መሰረት ተግባራዊ እንዲሆን ስታሳስብ መቆየቷንና ሁለቱ አገሮች ይህንኑ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ጥሪ ማሰማቷን አስታወቀች። “ባለፉት ጥቂት ሳምንታት አብዛኞቻችሁ ባድሜን አመልክቶ አሜሪካ (ያላት ወይም የያዘችው አቋም ለማለት ነው) ፖሊሲ ምን እንደሆነ ስትጠይቁን ነበር” ይላል የአሜሪካ መንግስት አስመራ በሚገኘው ኤምባሲውContinue Reading
 • የሽብርተኛው የሀሰት ፕሮፖጋንዳ የሠራዊታችንን የድል ግስጋሴ አይገታውም !
  ሽብርተኛው ከሚታወቅባቸው ስልቶቹ መሀል አንዱ ቅጥፈቱ ነው ፡፡ ጉልበት ሲያንሰው ምላሱ ይረዝማል ፤ ያልሆነውን ሆንኩ ፣ ያላደረገውንም አደረኩ…ይላል ፡፡ ይህ ደግሞ ጥርሱን የነቀለበት እና ተወልዶ ያረጀበት ባህሪው ነው ፡፡ አንድም ቀን ከአፉ እውነት ተገኝታ የማታውቀው ይህ ሽብርተኛ ፣ ሽንፈቱን የሚሸፍነው የሠራዊታችንን ስም በማጠልሸት ነው ፡፡ ደጋፊዎቹ ኪሳራውን እንዳያወቁ ፣ ሰላማዊውContinue Reading

Leave a Reply