በርካቶች የኢትዮጵያ ፖለቲካ ወደ መጨረሻው እያመራ መሆንኑ ይጠቁማሉ። አቶ ገመቹ ኢፋ በዚህ አሳብ ቢስማሙም ትኩረታቸው የኦሮሞ ፖለቲካ ላይ እየጠራ በመጣው ጉዳይ ነው። ነዋሪነታቸው አዲስ አበባ የሆነው አቶ ገመቹ እንደሚሉት የኦሮሞ ህዝብ ሁለት ምርጫ አለው። “ዛሬ” ይላሉ አቶ ገመቹ “ ዛሬ ኦሮሞ ያለአስረጂ ሁሉም ነገር ግልጽ ሆኖለታል። ከውያኔና ከኦሮሞ ልጆች ማንን እንደሚያስቀድም አውቋል”

“ወያኔ ኦሮሞዎች” የሚሉት ከወያኔ ጋር በድብቅ ሲሰሩ የነበሩና አሁን ላይ በግልጽ ከወያኔ ጋር እንደሚሰሩ ይፋ ያደረጉትን ነው። አቶ ገመቹ ኦነግን በቅርበት እንደሚያውቁ አሁን ግን እንደተለዩት ይናገራሉ። ምክንያታቸውን ግን ይፋ አላደረጉም።

ኢሬቻ ከተፈጸመው ግፍ በከፊል

ከአዲስ አበባ ተባባሪያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የኢጀሬ ተወላጅ “ ቀደም ሲል አንዳንድ ታዋቂ የኦሮሞ መብት ተሟጋችና የፖለቲካ መሪዎች፣ ከወያኔ ጋር ይሰራሉ ሲባል አላምንም ነበር። እንዲያውም ተራ ስም ማጥፋት ነው ብዬ አምን ነበር” ብለዋል አቶ ገመቹ።

“አሁን ላይ” አሉ አቶ ገመቹ አከሉና  “ አሁን ነገሮች ግልጽ ሆነዋል። የምንወዳቸው ፖለቲከኞች ኦሮሞን በኦሮሞነቱ ብቻ ሲያሳድዱ፣ ሲገሉ፣ ሲገርፉና ቶርቸር ሲያደርጉ፣ ጥፍር ሲነቅሉ፣ በየ እስር ቤቱ ሲያጉሩና ሲያዋርዱ የነበሩት ከኦሮሞ ልጆች በልጠውባቸዋል”

አቶ ገመቹ “ ሁሉም ይቅር ወያኔንን ለማስደሰት ኦሮሞ ኦሮሞን እያደፈጠ መግደሉ አሳፋሪና በየትኛውም ዘመን የማይረሳ ጥቁር ታሪክ ነው” ሲሉ ይህ ከምን ሊመጣ እንደቻለ ለመረዳት እንደሚቸገሩ ይገልጻሉ።

አሁን ያሉትን መሪዎች “እንደየ ደረጃው በደል ሰርተው የዳኑ የኦሮሞ ልጆች ” ሲሉ አቶ ገመቹ ይጠሩዋቸዋል። አያይዘውም እነዚህ ልጆቻችን ጥፋታቸውን በማረም ወደ ትክክለኛው መንገድ እንዲመጡ ማድረግ ሲገባ ከወያኔ ጋር ገጥሞ እነሱን ለመግደል መንቀሳቀስ አግባብ አለመሆኑንን ይጠቁማሉ።

የኢሪቻ ግፍ

“ አንድ ኦሮሞ ብረት አንስቶ አንድን ኦሮሞ ገድሎ በህወሃት ውዳሴ ማግኘት እንዴት ያረካዋል? ከሞራል አንሳርስ እንዴት ይታያል?” ሲሉ አቶ ገመቹ ይጠይቃሉ። አያይዘውም እነዚህን አድፋጮች የኦሮሚያ ሰራዊት ይገላል። ኦሮሞ ኦሮሞን እየገደለ ታሪኩን በደም እያቸማለቀው መሆኑንን ያስረዳሉ። ይህ እስከመቼ እንደሚቀጥልና ማቆሚያው ምን ሊሆን እንደሚችል ለመገመት እንደሚቸገሩም ያመለክታሉ።

ኦሮሚያ ሰፊ የህብረተሰብ ክፍል ያላት፣ ከሌሎች የተዋለዱና እንደየ አካባቢው አመካከቱ የተለያየ ህዝብ ያለባት ክልል መሆኗ የተረሳ እንደሚመስላቸው ይናገራሉ። አሁን ባለው አያያዝ ይህ የተለያየ አመልካከት ኦሮሚያ ውስጥ ወደየ ቀበሌ እንዳይወርድም ይሰጋሉ። ስጋታቸው ብዙም ባይሆን መገፋፋቱ ሲበዛ ወደ አካባቢያዊነት ስሜት መውረድ ሊመታ እንደሚችል ምልክት ማየታቸውን፣ ዝርዝር ውስጥ ባይገቡም አሁን ያለው ችግርም በመጠኑም ቢሆን የዚሁ ነጸብራቅ እንደሆነ አይሸሽጉም።

“በአሁን ጊዜ ኦሮሞን እርስ በርስ ሊያገዳድል የሚችል ምድራዊ ምክንያት ፈልጌ አጣሁ” ሲሉ በቁጭት አስተያየታቸውን የሰጡት አቶ ገመቹ፣ በለኤላ በኩል አሁን ላይ ለኦሮም ሕዝብ ሁሉም ነገር ገሃድ እየሆነ መምጣቱን እንደ በጎ ያዩታል። “ ለምን” ለተባሉት “ የኦሮሞ ሕዝብ ከወያኔ ኦሮሞዎችና ወያኔን ከደቆሱ የኦሮሞ ልጆች ማንን እንደሚያስቀድም እንዲያውቅ አድርጎታል” የሚል መልስ ሰጥተዋል።

irrecha9c
ኢሪቻ ሰላማዊ ህዝብ ላይ የተደቀነ መሳሪያ

በግላቸው የፈለገ ቢበደሉ ከወያኔ ጎን ቆመው ኦሮሞ ላይ ጥይት እንደማይተኩሱ ያመለከቱት አቶ ገመቹ፣ እንደ ወያኔ ካለ አረመኔ ድርጅት ጋር ማበር እጅግ አሳፋሪና ፖለቲካዊ ሞት እንደሆነ ገልጸዋል።

“ኦሮሞ ላይ ምን እንድተፈጸመ እንዴት ይረሳል” ሲሉ የሚጠይቁት አስተያየት ሰጪ “ ለወያኔ ማደርና መታዘዝ ኦሮሞን መካድ፣ በኦሮሞ ደም መሳለቅና በኦሮሞ ክብር መቀለድ ነው” ሲሉ ክፉኛ ተቃውመዋል።

“ ለትግራይ ሕዝብ ማዘን፣ ድጋፍ ማድረግና ወገንተኛነትን ማሳየት ታላቅነት ነው፤ ለወያኔ ድጋፍ ማድርግ ግን ሃፍረት ነው። የኦሮሞ ልጆች፣ አባቶች፣ እናቶችና ኢሬቻ የተረሸኑት ደም ይጮሃል” ሲሉ አጠንክረው ተቃውመዋል።

አሁን ኦሮሚያን የሚመሩት በርካታ ችግሮችና ጥፋቶች አለባቸው። ይሁን እንጂ በምንም መልኩ ለአንድ ወያኔ ኦሮሞ ላይ ምን ሲሰራ እንደኖረ ለሚረዳ ሰው እነሱን አግሎ ወያኔን ሊያስቀድም አይችልም። ይህ አሳፋሪ ነው።

ኢሬቻ ላይ እንዲህ ነበር የሆነው

አቶ ገመቹ ሲያጠቃልሉ እንዳሉት በኦሮሚያም ሆነ በመላው ኢትዮጵያ የተተፋ ድርጅት ነብስ እንዲዘራ በትሥር በኦሮሞ ትግል ስም የሚከናወኑ እንቅስቃሴዎችን ሕዝብ ለይቶ እያወቀ መሆኑን በመረዳት የኦሮሞ ልጆች ከጥፋት መንገዳቸው እንዲመለሱ፣ ከገቡበት ማቆሚያ የሌለው ትግል እንዲታቀቡ፣ አባቶች ሁሉንም ወገን ወደ ጠረጴዛ እንዲያመጡ ጠይቀዋል። አያዘውም መንግስትም ሆነ የክልሉ መሪዎች ለእውነተኛ ንግግር በራቸውን ክፍት ማድረግ እንደሚገባቸው አመልክተዋል። በእስር ላይ ያሉትም ሆን በጫካ፣ ብወጭ አገር ያሉትም ሆነ በየስፋራው የተበተኑ ኦሮሞዎች ከወያኔ ጋር ያላቸውን ጥምረት ባስቸኳይ እንዲያቆሙ በድጋሚ ጠይቀዋል። ሚድያዎችም ይህንን በማጋለጥ፣ በዚህ ረገድ ህዝብ ያለውን አስተያየት በመጠየቅ ይፋ ሊያደርጉ እንደሚገባም አመልክተዋል። ከአቶ ገመቹ ጋር የተደረገውን ቃለ ምልልስ ሙሉውን እናቀርባለን።


Leave a Reply