የቁርጥ ቀን ልጆች አብዛኞቹ ወጣቶች ነበሩ ። ከመላው ሀገሪቱ የተውጣጡ ትንታጎች። ህይወትን በአግባቡ ያላጣጣሙ፤ በአዲስ ህይወት መጀመሪያቸው ወቅት ላይ ለሀገር ክብር ነፍጥ ያነገቡ ነበሩ። በሚገርም ሁኔታ ጥያቄያቸው በተገኘው አጋጣሚ ከነባልባሉ ተርፈው በህይወት መቆየት ሳይሆን በግንባር ቀደምትነት መስዋዕት ሆነው ሉዓላዊነታቸውን ማስከበር ነበር። ሀገራዊ ስምና ዝናን ለተተኪው ትውልድ ማኖር ብቻና ብቻ ነበር።
በ1991 እና በ1992 ዓ.ም ወደ ሠራዊቱ የተቀላቀሉ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ጀግንነት የኢትዮጵያውያን ማንነት እና መለያ መሆኑን በተግባር እንዳሳዩ ሻለቃው ምስክር ነኝ ይላሉ። የደርግ መንግስትን ጥለው የሀገሪቱን መንበረ ስልጣን የተቆጣጠሩ አካላት ስለ ጀግንነት ይነዙት የነበረው ኘሮፓጋንዳ ጥያቄ ምልክት ውስጥ የገባው ከኤርትራ ጋር በተደረገው የመጀመሪያው ውጊያ እንደነበር መኮንኑ መቼም አይዘነጉም።እነሱ ‘የደርግ ወታደር’ የሚሉት የወቅቱ የኢትዮጵያ ሠራዊት በአፍሪካ ተወዳዳሪ አልነበረውም፡፡
ያ ታጋይ ባይሆን ምንም ምድራዊ ሐይል የማይረታው እንደነበር በስነ- ጥበብና በኪነ-ጥበብ ጭምር ታግዘው ብዙ በመስበክ ለመታመን ጫፍ ደርሰው ነበር። ምን ዋጋ አለው? ከኤርትራ ጋር የተደረገው ጦርነት ነገሩን ቆም ብለን እንድናጤነው አድርጎናል ።በመጀመሪያ ባድመን የማስለቀቅ ውጊያ ፈንጂ እየተራመዱ፤ የጠላትን ምሽግ በቦንብ እያጋዩ ምሽግ ያስለቀቁት ፤ ከዚያ በፊት ምንም ዓይነት የውጊያ ልምድ ያልነበራቸው ፤ ጦርነትን በፊልም ብቻ የሚያውቁ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ነበሩ።
ውጊያ የሰለጠኑበት ስለሆነ አያስገርምም ሊባል ይችላል። የሚያስገርም ፣ ምንም ዓይነት ማስተባበያ ሊቀርብበት የማይችል ተግባራትን የፈፀሙ ደግሞ አሉ። ነባር እና የውጊያ ኤክስፐርት የተባሉት ሲሰዉ ሬዲዮ ተቀብሎ አዋግተዋል። ክላሽ ምድብተኛ ሆኖ ሳለ ከሞተ የተቃራኒ ወታደር የቡድን መሣሪያዎች ለአብነት መትረየስ ፣ ዲሽቃና እስናይፐር ተቀብለው ድጋፍ ሰጥተዋል።
አዋጊ ሲሰዋ አባል አዋጊ ነበር። ተኳሽ ሲሞት ረዳት ሚናውን ተወጥቷል። አባል ሆኖ ጀምሮ መቶና ሻምበል አመራር ሆኖ የጨረሰ የቁርጥ ቀን ልጅ ቁጥሩ በርካታ ነበር። ነባር ታጋዩ ውስጥ ጀግና አዋጊና ተዋጊዎች የነበሩ ሲሆን ፣ የተባለውን ያህል በተግባር ከተባለው በተቃራኒ የተገለፁም ቁጥራቸው ቀላል አልነበረም።
የውጊያው ምክንያት ፣ አስፈላጊ መሆንና አለመሆንን ለታሪክ ትተን አንድ ድምደሜ ላይ ግን መድረስ ይቻላል። (ሁሉም አባባሎች የተራኪው ናቸው።) ኢትዮጵያውያን በአጭር ጊዜ የተዋጣለት የአውደ ውጊያ ጀግና መሆን ይችላሉ።በ1969 ዓ.ም በጎረቤት ሶማሊያ ወራራ በሦስት ወር ስልጠና ተዓምር የሠራው ሚሊሻ ነፍስ ዘርቶ በተረኞቹ ኢትዮጵያውያን በ1991 እና በ1992 ዓ.ም ሰሜን ላይ ተከስቷል።
ለብዙ ሺህ ዘመናት በነፃነት የመኖር ምስጢራችን ዳግም ተፈቷል።“24 ሠዓታት በወታደር ህይወት” የመኮንኑ ትራካ ይቀጥላል። ‘ማን ይናገር የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ” የመኮንኑን እውነተኛ ምስክርነት ተተኪው እንዲማርበት እየጨለፍን ማስነበባችንን እንቀጥላለን።
ሻለቃ ፈይሳ ናኔቻ – ከመከላከያ ፌስ ቡክ የተወሰደ
- አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎችባንኩ የክፍያ ሰነድ ቀረበለት። ማጣሪያ ጥያቄ ለህብረቱ አቀረበ። ሃሰት ሆኖ ተገኘና ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን ያዘ። ጉዳዩ ወደ ህግ አመራ። አሁን… Read more: አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎች
- የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል 300 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ዕዳ አለብኝ አለ፤ ዕዳውና የክፍያው ጫና እንደከበደውም አስታውቋልየኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከንግድ ባንክ 300 ቢሊዮን ብር ዕዳ እንዳለበት ተገለጸ። የዕዳ ጫናውን ለማቃለል የባንክ ወልዱም ጭምር ተፅእኖ እያሳደረ… Read more: የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል 300 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ዕዳ አለብኝ አለ፤ ዕዳውና የክፍያው ጫና እንደከበደውም አስታውቋል
- ዋና ዋና የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ይዘቶች – ሲጨመቁመግቢያ ሽግግር ፍትህ ጉልህ የመብት ጥሰቶች በተፈፀመባቸው ሀገራት ተጠያቂነትን ለማስፈን እና ተበዳዮችን ለመካስ ጥቅም ላይ ሲውል ቆይቷል፡፡ በሀገራችንም የሽግግር… Read more: ዋና ዋና የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ይዘቶች – ሲጨመቁ
- “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”“የሚሊሻ ኀይሉን በተመለከተ የሚዘዋወረው መረጃ ፍጹም መሠረተ ቢስ ነው” ሲሉ ኮሎኔል ግርማ ገሰሰ አስታወቁ። “ቅጥፈት ነው” ያሉትና በፕሬዚዳንቱ ስምና… Read more: “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”
- “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን“የትግራይ ተወላጆች ትህነግ ለፈጸመው ወረራ፣ ዘረፋ፣ ማፈናቀልና የግድያ ተግባራት የተቀናጀ የፖለቲካና የሚዲያ ድጋፍ ሰጥተዋል። በተለይም በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ… Read more: “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን