የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ኤታማዦር ሹም የነበሩትን ጀነራል ሰዓረ መኮንን እና ጓደኛቸውን ሜጀር ጀነራል ገዛኢ አበራን በመግደል ወንጀል ተከሶ የነበረው አስር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ጥፋተኛ መባሉን ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ገልጸ።
ውሳኔውን አርብ ግንቦት 27/2013 ዓ.ም የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ ሦስትኛ የጸረ ሽብርና የሕገመንግሥት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።
ከሁለት ዓመት በፊት በአዲስ አበባ በጀነራል ሰዓረ መኮንን መኖሪያ ቤት ውስጥ ግድያውን በመፈጸም የተከሰሰው አስር አለቃ መሳፍንት ጉዳይን የተመለከተው ችሎት ተከሳሹ የሰፊ የወንጀል ድርጊት አካል ሆኖ ወንጀሉን መፈጸሙን አመልክቷል።
ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ባወጣው መረጃ መሰረት የጥፋተኝነት ውሳኔ የተላለፈበት ተከሳሹ አስር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ በአማራ ክልል የቀድሞ የሰላምና የሕዝብ ደኅንነት ቢሮ ኃላፊ በነበሩት በብርጋዲየር ጀነራል አሳምነው ጽጌ በተመራ ሰፊ ከባድ የወንጀል ድርጊቶች ሴራ ውስጥ ተሳታፊ እንደነበር አመልክቷል።
በዚህም ተከሳሹ በዚሁ ሴራ ውስጥ የአገሪቱ ጦር ሠራዊት ኤታማዦር ሹም የነበሩትን ጀነራል ሰዓረ መኮንን እንዲገድል እንዲሁም ሌላ ግለሰብ ደግሞ ምክትል ኤታማዦር ሹም የነበሩትን ጀነራል ብርሃኑ ጁላን እንዲገድል ተልዕኮ ሰጥቷቸው እንደነበር ተገልጿል።
ዐቃቤ ሕግ እንዳለውም ግንቦት 15/2011 ዓ.ም ምሽት ሦስት ሰዓት ላይ አስር አለቃ መሳፍንት ባሕር ዳር ከተማ የተፈፀመውን ጥቃት ሲሰማ “ተኩሶ ጀነራል ሰዓረ መኮንንና ሜጀር ጀነራል ገዛኢ አበራን በመግደል ለማምለጥ ሲሞክር ተከቦ በቁጥጥር ስር ውሎ” ጉዳዩ በፍርድ ቤት ሲታይ መቆየቱን ገልጿል።
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ ሦስትኛ የጸረ ሽብርና የሕገ መንግሥት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በክሱ ላይ የቀረበውን የግራ ቀኝ ክርክርና ማስረጃ ከመዘነ በኋላ ነበር ተከሳሹ ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ በመስጠት የቅጣት አስተያየት ለመስማት ለሰኔ 11/2013 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል።
ሰኔ 15/2011 ዓ.ም አዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ የተገደሉት ኤታማዦር ሹሙ፤ ለረጅም ዓመታት በኃላፊነቱ ላይ የቆዩትን ጄነራል ሳሞራ የኑስን ተክተው የአገሪቱ ሠራዊት አዛዥ ከሆኑ ብዙም አልቆዩም ነበር።
በጥቃቱ ወቅት በአጋጣሚ በጄነራሉ ቤት የተገኙት ጓደኛቸውና የቀድሞ የሠራዊቱ አባል ጀነራል ገዛኢ አበራም በተፈጸመባቸው ጥቃት ተገድለዋል።
ዐቃቤ ሕግ የዚሁ ሴራ አካል ነው ባለው ድርጊት በዚያው ዕለት ምሽት ጥቂት ሰዓታት ቀደም ብሎ በባሕር ዳር የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር የነበሩትን ዶ/ር አምባቸው መኮንንና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮቻቸው ላይ ግድያ መፈጸሙ ይታወሳል። BBC amaharic
- የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ዳግም ዝርፊያ እያፈጸሙ ነው፤ የተማሪዎች መጽሃትን “የአማራ ክልል ናቸው እየሉ ቀደዋል”በአላማጣ ከተማ በተለየ መልኩ የትግራይ ክልል ታጣቂዎች በከተማዋ ውስጥ እንደሚንቀሳቀሱ ነዋሪዎች መመስከራቸውን ቢቢሲ አስታወቀ። ይህ የተገለጸው ከአለማጣ እና አካባቢው የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር… Read more: የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ዳግም ዝርፊያ እያፈጸሙ ነው፤ የተማሪዎች መጽሃትን “የአማራ ክልል ናቸው እየሉ ቀደዋል”
- በዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ችግኝ ልትተክል ነውለዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር 6 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል ዕቅድ መያዙንna ለዚህም ተግባራዊነት ከሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊየን በላይ ችግኝ መዘጋጀቱን ተገለጸ።… Read more: በዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ችግኝ ልትተክል ነው
- አፍሪካ ህብረት ” የውጭ ምንዛሪ ሒሳቡን ወደ ሌላ ሀገር ሊያዘዋውር ነው” የሚለው ዜና ሃሰት መሆኑን ህብረቱ አረጋግጠአፍሪካ ህብረት የውጭ ምንዛሬ አካውንቱን ወደ ሌላ አገር እንደሚያዘዋውር ተጠቅሶ በህብረቱ ስም የወጣው ዜና ሃሰት፣ ሆን ተብሎ የተቀነባበረ መሆኑን መንግስት አስታወቀ። መረጃው… Read more: አፍሪካ ህብረት ” የውጭ ምንዛሪ ሒሳቡን ወደ ሌላ ሀገር ሊያዘዋውር ነው” የሚለው ዜና ሃሰት መሆኑን ህብረቱ አረጋግጠ
- አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎችባንኩ የክፍያ ሰነድ ቀረበለት። ማጣሪያ ጥያቄ ለህብረቱ አቀረበ። ሃሰት ሆኖ ተገኘና ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን ያዘ። ጉዳዩ ወደ ህግ አመራ። አሁን ምኑ ነው አፍሪካ… Read more: አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎች
- የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል 300 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ዕዳ አለብኝ አለ፤ ዕዳውና የክፍያው ጫና እንደከበደውም አስታውቋልየኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከንግድ ባንክ 300 ቢሊዮን ብር ዕዳ እንዳለበት ተገለጸ። የዕዳ ጫናውን ለማቃለል የባንክ ወልዱም ጭምር ተፅእኖ እያሳደረ መሆኑም ተመልክቷል። የኢትዮጵያ… Read more: የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል 300 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ዕዳ አለብኝ አለ፤ ዕዳውና የክፍያው ጫና እንደከበደውም አስታውቋል