እብሪተኛው የህወሓት ኃይል የትኛውንም አማራጭ ተጠቅሞ ወደ ሥልጣን መመለስ ወይም ኢትዮጵያን መበታተን የሚል ቀቢፀ ተስፋ ይዞ ነበር ወደ ወረራ የገባው፡፡ ለዚህ ማሳያ የሚሆነው በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከለከለውን በርካታ ሚስማር መሰል ፍንጣሪ (flechette) የተሰገሰገባቸውን በከባድ መሣሪያ ጭምር የሚተኮሱትን የሚስማር ጥይቶች በንፁሃን ላይ ማርከፍከፉ ነው። በሸኔ የውስጥ ቀውስና መከፋፈል መከሰቱ ተገለጸ።
በምስሉ ላይ ወራሪው ኃይል በአፋር ጭፍራ ከተማ በንጹኃን ላይ የተጠቀማቸው የሚስማር ጥይቶች ይታያሉ፡፡ ወራሪው ኃይል ይህን መሣሪያ በአፋር እና በአማራ ክልሎች ተጠቅሟል፡፡ ነዋሪዎች እንደመሰከሩት ሚስማሮቹን ከበርካታ ጉዳት ከደረሰባቸው ንፁሃን ሰዎች ገላ ላይ ነቅለዋል፡፡ ሰቆቃውን ተመልክተዋል፡፡ ኢትዮጵያ እንደዚህ አይነት መሣሪያዎች ጥቅም ላይ ላለማዋል ዓለም አቀፍ ስምምነት ፈርማለች። (አዲስ ሚዲያ)
በሌላ ዜና አሸባሪው ሸኔ አባላት መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ወደ ከፍተኛ ግጭት መሸጋገሩንና መንግስት በቡድኑ ላይ የሚወስደው እርምጃም አጠናክሮ መቀጠሉን የኦሮሚያ ኮሚንኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ አቶ ሀይሉ አዱኛ አስታወቁ።
አቶ ሀይሉ የክልሉን ሰላምና ልማት አስመልክተው ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ እንደተናገሩት፤ የክልሉን ሰላም እያናጋ ያለው የሸኔ ሽብር ቡድን ከሁሉም በማስቀደም በሰላማዊ መንገድ እንዲመለሱ በአባ ገዳዎችና በሀዳ ሲንቄዎች በተደረገው ጥሪ 312 የቡድኑ አባላት ተመልሰዋል። 540 የሚሆኑት ደግሞ በህዝብ ጥቆማ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ከታህሳስ 16 እስከ 30 ዓ.ም በተወሰደው እርምጃ 876 አባላት ሲደመሰሱ ኮማንድ ፖስቱ ስራ ከጀመረ ወዲህ በጥቅሉ ሁለት ሺህ 439 የቡድኑ አባላት ተደምስሰዋል ብለዋል። በተመሳሳይ መልኩ ወደ ሰላማዊ መልኩ ወደ ሰላማዊ ትግል ለመመለስና ላለመመለስ በቡድኑ አባላት መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ወደ ከፍተኛ ግጭት መሸጋገሩን አቶ ሀይሉ ገልጸዋል።
በክልል ደረጃ በርካታ የልማት ስራዎች የመስኖ ስራዎችን ጨምሮ ውጤታማ ስራዎች እየተሰራ መሆኑንና በድርቅ የተጎዱ እንደ ቦረና: ጉጂና ባሌ ከእንስሳት መኖ ጀምሮ የተለያዩ ድጋፎች እየቀረቡ መሆናቸውን ገልጸዋል። አቶ ሀይሉን ጠቅሶ ኢፕድ አስታውቋል።
