በሶማሌ ክልል ከፍተኛ ወንጀል ከሚፈለጉት አንዱ የትህነግ ሰራዊት መሪ ተማረከ

May be an image of one or more people and outdoors
ኮ. ገዑሽ

ዛሬ የአገር መከላከያ በምስል አስደግፎ ይፋ ያደረገው ዜና ከወደ ሶማሌ ክልል ጩኸት አስነስቷል። ምክንያት የተባለው ደግሞ በወሎ ግንባር የተማረከ መሆኑ ተገልጾ ምስሉ ይፋ የሆነው የቀድሞው ኮሎኔል ግዑሽ ገብሩ በርካታ ሶማሌዎች ለተገደሉበትና በሺህ የሚቆጠሩ የኦሮሞ ልጆች ለሞትና መፈናቀል የተዳረጉበትን ሴራ ጋር የተያያዘ ነው የሚል ነው።

ከዚህ ጉዳይ ጋር ሳያያዝ መከላከያ ይፋ እንዳደረገው ኮሎኔሉ በአሁኑ ሰዓት የሜይዴይ ክፍለጦር አዛዥ መሆኑን እንዳስታወቀና እንደሚታወቅ አመልክቷል። አሸባሪው የትህነግ ቡድን አገር የማፍረስ እቅዱን ለማሳካት በርካታ እኩይ ተግባራትን እየፈፀመ እንደሚገኝ ኮሎኔል ጉዕሽ ገብሩ አስታውቋል።

አሸባሪው ቡድን በወሎ ግንባር እጅግ ሰፊ ቁጥር ያለው ሃይል አሰልፎ እንደነበር፣ በጦርነቱም እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሃይሉ መመታቱን ኮሎኔሉ አምኗል። “የሽብር ቡድኑ በርካታ ህፃናትና ሽማግሌዎችን ያለ ትጥቅ በማሰለፍም ለአላስፈላጊ መስዋዕትነት እየዳረጋቸው እንደሚገኝም ምርኮኛው ተናግሯል ።አሸባሪው ትህነግ አገር የማፍረስ እቅድ ነድፎ መንቀሳቀስ ከጀመረ ድፍን አንድ አመት ተቆጥሯል። ቡድኑ በጥቅምት ወር 2013 ዓ.ም በሰሜን እዝ ላይ ያሰበው እቅድ እንዳሰበው አልሆን ሲለው የትግራይን ህዝብ በሀሰት ፕሮፓጋንዳ በማሰባሰብ ለዳግም የክህደት ተግባር በተለያዩ ግንባሮች ጦርነት ከፍቶ ይገኛል” ሲል መናገሩንም የመከላከያ ዜና ያስረዳል።

“የሽብር ቡድኑ ሰሞኑን እጅግ በርካታ ቁጥር ያለው የሰው ሃይል በማሰለፍ በደሴ ግንባር ውግያ ቢከፍትም በርካታ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ሊደርስበት ችሏል” ሲል ግዑሽ መመስከሩን ያወሳው ዜና “የትህነግ ሃይል ያሰማራው ሃይል ዲስፒሊን የሌለው በመሆኑ በወረራ በያዛቸው አካባቢዎች በርካታ የግድያና ዘረፋ ተግባራትን አከናውኗል” በማለት ቃሉን መስጠቱን ገልጿል።

“በወሎ ግንባር ሰራዊታችን ባደረገው ዘመቻም በርካታ የጠላት ሃይልን የደመሰሰ ሲሆን በርካቶችንም ማርኳል። ከተማረኩት ውስጥም የ ሜይዴይ ክ/ጦር አዛዥ የሆነው የ64 አመቱ ኮ/ል ጉዕሽ ገብሩ ይገኝበታል” ሲል መከላከያ ያለበትን የጦርነት ቁመና ዜናው ጠቁሟል።

የሽብር ቡድኑ ያሰባሰበው የሰው ሃይል ብዛት ከታጠቀው የመሳሪያ ብዛት ጋር የሚመጣጠን ባለመሆኑ አብዛኛውን የሰው ሃይሉን በባዶ ዕጅ በማሰለፍ የጥይት ሲሳይ እያደረገው እንደሚገኝ፣ የትህነግ አመራሮች ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ፣ በትግራይ እድሜውንና ህይወቱን በሰጠው የመከላከያ ሰራዊታችን ላይ የፈፀሙት የክህደት ተግባር ለአሁናዊ ምስቅልቅል እንደዳረጋቸው የገለፀው ምርኮኛው በድርጊቱም እንዳዘነ ጠቁሟል።

“በአሁኑ ሰዓት በሽብር ቡድኑ አመራሮች እብደትና ቅሌት ምክንያት የትግራይ ህዝብ በከፍተኛ የሰላም እጦትና ችግር ውስጥ እንደሚገኝ የገለፀው ምርኮኛው ፣የሽር
ብር ቡድኑ አመራሮችን በቁጥጥር ስር ማዋል ብቸኛው መፍትሄ እንደሆነም ተናግሯል ” ሲል ዜናው አመልክቷል።

DONATE US – ቢረዱን አስፍተን ለመስራት አቅም ይፈጥሩልናል

About topzena1 2650 Articles
A journalist

Be the first to comment

Leave a Reply