“የመንግስታቱ ድርጅት ህግጋቶች ለግለሰብ መተቀሚያ እየተሸረሸሩ ነው”

በመንግስታቱ ድርጅት የሚሰሩ ግለሰቦች የግል አጀንዳቸውን በማራመድ የድርጅቱን ህግጋትና እሴት እየሸረሸሩ ነው። በመንግስታቱ ድርጅት የሚሰሩ አንዳንድ ግለሰቦች የግል አጀንዳቸውን በማራመድ የድርጅቱን ህግጋትና እሴት እየሸረሸሩ ነው”ሲሉ በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት የፓኪስታን ሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት (ኦቻ) ኃላፊ ቾይስ ዑፎኦማ ኦኮሮ ተናገሩ።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአገራትን ሉዓላዊነት ባከበረ መልኩ ሰላምን ለማምጣት የሚሰራ ዓለም አቀፍ ተቋም ቢሆንም በአንዳንድ ግለሰቦች ያልተገባ እንቅስቃሴ እየተስተዋለበት መጥቷል ብለዋል።

በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት የፓኪስታን ሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት (ኦቻ) ኃላፊ ቾይስ ዑፎኦማ ኦኮሮ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ተመድ የአገራትን ሉዓላዊነት አክብሮ ሰላም እንዲሰፍን የሚሰራ ድርጅት መሆኑን ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ መንግስት በአሸባሪነት የተፈረጀው የህወሃት ወራሪ ቡድን በአማራና አፋር ክልሎች በጤና ተቋማት፣ ሆስፒታሎች፣ ጤና ጣቢያዎችና ጤና ኬላዎች ላይ ከፍተኛ ውድመት ሲያደርስ የዓለም ጤና ድርጅትን የሚመሩት ግለሰብ ዝምታን መርጠዋል።

የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም፤ ይባስ ብለው ከአሸባሪው ህወሃት ጎን በመሰለፍ ስለሀገሪቱ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ የተሳሳተ መረጃ ሲያሰራጩ ቆይተዋል።

“ምን አልባትም በድርጅቱ የሚሰሩ አንዳንድ ግለሰቦች የተሰጣቸውን ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው ያልተገባ ነገር ሊሰሩ ይችላሉ፤ ያ ግን የድርጅቱ ሚና እና ትዕዛዝ አይደለም” ይላሉ ቾይስ።

በድርጅቱ እየሰሩ ኢትዮጵያን በሚጎዱ ተግባራት ላይ የተጠመዱ ግለሰቦች ከድርጅቱ መርህ ውጭ ስህተት እየፈጸሙ መሆኑን ይናገራሉ።

ድርጅታቸው ‘ኦቻ’ም ገለልተኛና ከማንኛውም ፖለቲካዊ ጉዳይ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት ሊኖረው እንደማይገባ ጠቅሰው በማንኛውም ቀውስ ተጎጂ የሆኑ ሰዎችን ማገዝ ዋነኛ ዓላማው መሆኑን አብራርተዋል።

በድርጅቱ የፓኪስታን ‘ኦቻ’ ኃላፊዋ ዑፎኦማ ኦኮሮም በድርጅቱ እየሰሩ ከመንግስታቱ ድርጅት መርህ ውጭ በአንድ አገር ውስጥ ሰላምና መረጋጋት እንዳይሰፍን የሚያደርጉ አካላትን ተጠያቂ ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ማንኛውም ግለሰብ ድርጅቱን በመጠቀም በየትኛውም ሀገር ውስጥ ጉዳይ ገብቶ ግጭቶችን በማስፋፋት የግል አጀንዳ ማራመድ በፍፁም የተከለከለ መሆኑን ተናግረዋል።

ግጭትን በማባባስ ላይ የተጠመዱ አካላት ከመንግስታቱ ድርጅት ህግጋት ጋር እየተቃረኑ መሆናቸውን ጠቁመው ግለሰቦቹ የሚያራምዷቸው ተቃርኖዎችም የድርጅቱ ተልዕኮ አለመሆኑን ገልጸዋል።

አንዳንድ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ በማጋነን፤ችግሮቿን ለመፍታት እያደረገች ያለውን ጥረት በማጣጣል የተሳሳተ መረጃ እያሰራጩ መሆናቸውም ተገቢ አይደለም ብለዋል።

ኢትዮጵያ ያላትን ጠንካራ የመንግስት አስተዳደር ልታስቀጥል ይገባል ያሉት ኦኮራ “በምዕራባዊያን የመገናኛ ብዙኃን የተሳሳተ ትረካ የሚመራውን ጦርነት የመቆጣጠር አቅም እንዳላትም ምንም ጥርጥር የለኝም” ሲሉ አክለዋል።

የአፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ አገራት በመንግስታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንደሌላቸው ጠቅሰው “አፍሪካ ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራት እንፈልጋለን” ብለዋል።

የፀጥታው ምክር ቤትም አምስት ቋሚ መቀመጫ ያለው ሲሆን በቀጣይ ቢያንስ ሰባት መቀመጫዎች እንዲኖሩት ቢደረግ ሲሉም ሀሳባቸውን ሰንዝረዋል።

“ቅኝ ግዛት አብቅቶለታል፤ በመንግስታቱ ድርጅት ውስጥም የቅኝ ግዛት ቋሚ መዋቅር ሊቀመጥ አይገባም፤ አፍሪካም በጸጥታው ምክር ቤት በቋሚነት መወከል አለባት፤ “ይህም ቀላል እና ለድርድር መቅረብ የሌለበት ነው” ብለዋል።

በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት የፓኪስታን ሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት (ኦቻ) ኃላፊዋ ቾይስ ዑፎኦማ ኦኮሮ በአፍሪካ የመንግስታቱ ድርጅት ሰብዓዊና ልማታዊ ተቋማትን መርተዋል፡፡

በካናዳም መንግስታዊ ባልሆኑና በሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ከ20 ዓመታት በላይ ያገለገሉ ሲሆን በኢትዮጵያም ለአራት አመታት በድርጅቱ መስራታቸውን ጠቅሶ የዘገበው ኢዜአ ነው።

Related posts:

በሳዑዲና ኢራን በሞት የሚቀጡ ሰዎች ቁጥር ጨምሯልMay 26, 2022
የመሰረተ ልማት ቀበኞች ላይ " የሞት ቅጣት"May 26, 2022
ኢሳያስ - ዘመቻው እስከ መጨረሻ ቀብር ይሆናል ሲሉ ትህነግን አስጠነቀቁMay 25, 2022
በአማራ ክልል እፎይታ እየነገሰና የትህነግ የወረራ ዕቅድ መምከኑ ተሰማMay 25, 2022
ንግድ ባንክ ለአፈር ማዳበሪያ ግዥ ከ50 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ማድረጉን አስታወቀMay 25, 2022
ቢለኔ ታይም መጽሔትን ማብራሪያ ጠየቁ፤ የተሰላ ጥቃትና የአንድ ወገን ትርክት ማቅረቡን ኮንነዋልMay 25, 2022
"ከውስጥ በር ለማስከፈት ... ከጣራ በላይ ጩኸት" አብን አማራን ለሶስተኛ ዙር ወረራ እያመቻቹ ያሉትን በይፋ አወገዘMay 24, 2022
በኢትዮጵያ በተከሰቱ ግጭቶች ሁሉ የትህነግ እጅ እንዳለባቸው በመረጃ ተረጋገጠMay 24, 2022
ፋኖ እየጨፈረ ከመከላከያና አማራ ልዩ ሃይል ጋር የግዳጅ ቀጠናውን ተረከበMay 23, 2022
ተልዕኮ አስፈጻሚዎችና ከ1780 በላይ ሕዝባዊ ኀላፊነታቸውን ያልተወጡ ተጠርጣሪዎች ተያዙMay 23, 2022
በሕግ ማስከበር ዘመቻ ከ4 ሺህ በላይ ተጠርጣሪዎች በሕግ ቁጥጥር ስር ዋሉMay 23, 2022
በአማራ ክልል መፈንቅለ መንግስት ታቅዶ ነበርMay 23, 2022

Leave a Reply