መሀመድ አልአሩሲ ከግብፅና ሳውዲ ተንታኞች ጋር በአልጀዚራ ተናንቋል።

አወያዩ ጋዜጠኛ ኢትዮጵያ ያለግብፅ ፍቃድ ናይልን ለመገደብ፣ እየገነባች ነው ያለፍቃድ ግን ውሃ መያዝ  አትችልም በሚለው የግብፁና የሳውዲው ተንታኝ ሀሳብ ላይ የመሀመድ አልአሩሲን መልስ ይጠይቀዋል።

አልአሩሲ ሲመልስ – እንገድበዋለን፣ ውሃም እንይዛለን። ይገርመሃል ያለፍቃዳችሁ ሀይል እናመነጫለን። ምክንያቱም ይህ አላህ ለኢትዮጵያ የሰጣት የተፈጥሮ ፀጋ ነውና የማንንም ፍቃድ አትሻም።

አንተኛው የሳውዲ ዜጋ ልጠይቅህ፣- ነዳጅ ስታወጡ ኢትዮጵያን አስፈቅዳቹሃል ብሎ ጠየቀ

የተጠየቀው በቁጣ «ለምን እናንተን እናስፈቅዳለን። ነዳጁ መሬታችን ላይ የወጣ የኛ ሀብት አይደል? ” ብሎ መለሰ

አልአሩሲ እየሳቀ፣- “እኔም የምልህ በኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብት ፈቃጅና ከልካይ እናንተን ማን አደረጋችሁ? ከመሬታችን ላይ 86 በመቶ የሚመነጭ ሀብት ፍቃድ የምንጠይቀው አብደን ነው? አንጠይቅም” አለ። ወደ ግብፃዊው እያመለከተ

“አንተ ግብፃዊውም ኢትዮጵያ አብረን እንመከር ማለቷ ፍቃድ ለመጠየቅ አይደለም። መልካም ጉርብትና ስለሆነ መተማመኛ ለመስጠት ነው። አስዋንንን ስትገነቡ አላስፈቀዳችሁንም። እኛም ፍቃድ አንጠይቅም። አለማቀፍ መርህ ይህ ነው። ቱርክ አላስፈቀደችም። አሜሪካ አላስፈቀደችም። ቻይና አላስፈቀደችም። ኢትዮጵያም አታስፈቅድም። ለምሳሌ ጉዳዩን እንገልብጠውና ግብፅ የናይል መነሻ ብትሆን እና ኢትዮጵያ የግብፅ ቦታ ላይ ብትሆን ግድብ ለመገንባት ታስፈቅዱን ነበረ? ” ብሎ ጠየቀው።

ግብፃዊው ዝም አለ። ፈገግ አለ። ፈገግ አባባሉ “ለምን እናስፈቅዳለን” የሚል ትዕቢት አለበት።

“የግብፅ ጦር ታላቅ ነው። ኢትዮጵያውያን ሆይ አትፈታተኑን” አለ ግብፃዊው።

“በጦርነት ኢትዮጵያን አያቶችህ ያውቋታል። ትምህርት ሰጥታ መልሳለች። በፍቅር እንጂ በፀብ ኢትዮጵያን ማንበርከክ አትችሉም። ሀገራችን በትዕቢተኞች መልካም ፍቃድ አልቆመችም። በልጆችዋ ጀግንነት ነው እዚህ የደረሰችው።” አለ አልአሩሲ ጥርሱን በመግጠም

“እስቲ ውሃ ያዙና መልሳችንን ታያላችሁ” አለ ግብፃዊው

“ማብራት አመንጭተን እናሳይህ የለም? ትንሽ ብቻ ጠብቅ።”

የአልጀዚራው ጋዜጠኛ ወደ ሌላ ጥያቄ ዞረ።

አልአሩሲ በራስመተማመን ጥያቄውን ይጠብቅ ያዘ። እነሆ ዛሬ ቀኑ ደረሰ። ጀግናችን አልአሩሲ ሆይ እናት ሀገርህ ኢትዮጵያ ታመሰግንሃለች

Via Muktarovich

Leave a Reply