ህዩዋ..ህዩዋ
ህንግጫ-የኮንታ_ብሔር_ዘመን_መለወጫ!!
የኮንታ ብሔር በሀገር አቀፍ ደረጃ በተለየ መልኩ የሚገለጽባቸው በርካታ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ታሪካዊ እና ባሕላዊ ቅርሶች ባለቤት ነው።
ብሔሩ ካሉት በርካታ የማይዳሰሱ ሀብቶች መካከል አንዱ የኮንታ ብሔር ዘመን መለወጫ በዓል-ህንግጫ አንዱ ነው፡፡
ህንግጫ በብሄሩ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ታላቅ የዘመን መለወጫ በዓል ሲሆን ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣ የብሔሩ ማንነት መገለጫም ነው።
በኮንታ ብሔር ዘንድ ህንግጫ የአሮጌው ዓመት ማብቅያ እና የአዲሱ ዓመት መጀመሪያ ወይም መሸጋገሪያ በዓል ነው፡፡
የሚከበረው የዘመን መለወጫ ‹‹ህንግጫ›› በአል ዘመን ተሸጋሪና ሁሉም የብሔሩ ተወላጆች በአብሮነት የሚያከበሩበት በአል ነው።
‹‹ህንግጫ›› ያማረ፣ ያጌጠ፣ የለመለመ ማለት ሲሆን አደይ አበቦች ፈክተው የሚታዩበት በአል ከመሆኑም ባለፈ በብሄረሰቡ ዘንድ በታላቅ ጉጉት ተጠብቆ በየአመቱ የሚከበር ልዩ በዓል ነው።
በዓሉ ከጳጉሜ 5/6 እስከ መስከረም 30 ድረስ የመስቀል በዓልን አካቶ የሚከበር ሲሆን ህብረተሰቡ ከቤት ውስጥ ጀምሮ ደጃፍና አከባቢውን የማጽዳት ዘመቻ በማድረግ በማጽዳትና በማስዋብ አዲሱን ዓመት በአዲስ መንፈስ ለመቀበል የሚሰናዱበትና ለበአሉ ከ12 አይነት በላይ ባህላዊ ምግቦች የሚዘጋጅበት በብሔሩ ተወላጆች ዘንድ እጅግ ልዩ ቦታ የሚሰጠው ነው።
የዘመን መለወጫ በአል ማብሰሪያ እሳት የሚወጣው ከጳጉሜ5/6 ምሽት ሲሆን ሲነድ የቀረው የማገዶ ጫፍ ከእሳት ዳር ተመዞ ወደ ዉጪ በመጣል ነዉ፡፡
መጠሪያውም ‹‹ ፂፋ ››ተብሎ ይጠራል።
የቤቱ አባወራው በያዘው ‹ፂፋ› ለዘመን መለወጫ/ለህንግጫ/በዓል ያደረሰውን ፈጣሪ እያመሰገነ እቤት ውስጥ ሰላም፤ ደስታና ጥጋብ እንዲሆን እየተመኘ ከቤት ደግሞ ክፉ መንፈስ እንዲወጣ እቤት ውስጥ ባሉት እቃዎች ላይ ‹በጺፋው› እየነካካ ወደ ውጪ ይዞት ይወጣና ይጥለዋል፡፡
በህንግጫ በዓል ያለው ለሌለው አካፍሎ የሚበላበት፥ ድሃውም ሀብታሙም እኩል የሚያከብሩት የአብሮነት ተምሳሌት ክብረ-በዓል ነው።
ህንግጫ በአል ታሪካዊ ይዘቱን ሳይለቅ ከትውልድ ወደ ትውልድ ተሸጋግሮ ዛሬ ላለንበት ጊዜ የደረሰ በመሆኑ ሁሉም የብሄሩ ተወላጆች የታሪክ መዛነፍ ሳይኖር ባህሉን ጠንቅቆ በማወቅና ለመጪው ትውልድ በማስተላለፍ ኃላፊነታችንን ሊንወጣ ይገባል፡፡
“ህዩዋ ህዩዋ” ህንግጫው ብለናል።
አቤ ነኝ ከኮንታ ከሃበሻ የተወሰደ
- የደም ግፊት በመለካትና ክትትል በማድረግ የስትሮክ ተጋላጭነትን መቀነስአንድ ሰው የደም ግፊት መጠኑ ከፍተኛ ከሆነ እና በጊዜው ሕክምና ካላደረገ ለከፍተኛ የልብ በሽታና በደም ዝውውር ማነስ ምክንያት ለሚከሰት የአዕምሮ… Read more: የደም ግፊት በመለካትና ክትትል በማድረግ የስትሮክ ተጋላጭነትን መቀነስ
- የስኳር ህመም አይነቶች እና ምልክቶችየስኳር ህመም በደም ውስጥ የስኳር መጠን ከሚገባው በላይ ሆኖ በሚገኝበት ሰዓት የሚከሰት ተላላፊ ያልሆነ የህመም አይነት ነው። በዋናነት አራት የስኳር… Read more: የስኳር ህመም አይነቶች እና ምልክቶች
- ማንኮራፋትና ትዳርን እስከ ማፍረስ የሚያደርሰው መዘዙ ? ማንኮራፋት መፍትሄ አለው?የማንኮራፍት መዘዙ እንቅልፍ ማሳጣት ብቻ አይደለም። ማንኮራፋት ከሚያንኮራፉት ሰዎች ጎን በሚተኙ ሰዎች አካላዊ እና አእምሮ ጤና ላይ ጉዳት ያስከትላል። ትዳርንም… Read more: ማንኮራፋትና ትዳርን እስከ ማፍረስ የሚያደርሰው መዘዙ ? ማንኮራፋት መፍትሄ አለው?
- የባህር ወንበዴ ሲሳዮች – በገሃነም የሚመሰለው ስቃይየ34 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ ከአውሮፕላኑ ሲወርድ እግሮቹ ቆስለው መራመድም ሆነ መቆም አቅተውታል። ብርክ ይዞት ይንገዳገዳል፡፡ ይህ ሰው የተሻለ ህይወት ይኖረናል ብለው… Read more: የባህር ወንበዴ ሲሳዮች – በገሃነም የሚመሰለው ስቃይ
- ሙሉቀን – የዘመን ቅርስ ድምጸ መረዋ የዘመናዊ ሙዚቃ እንቁገና የ13 ዓመት ታዳጊ ሳለ ሙዚቃን የጀመረው የቀድሞው ድምፃዊ ሙሉቀን መለሰ በ1958 ዓ.ም በፓትሪስ ሉሙምባ ምሽት ክለብ ፈጣን ኦርኬስትራን ተቀላቅሎ… Read more: ሙሉቀን – የዘመን ቅርስ ድምጸ መረዋ የዘመናዊ ሙዚቃ እንቁ