በሶማሊያ በሚንቀሳቀሰው አልሸባብ የሽብር ተልዕኮ የተሰጣቸው ስድስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በሶማሊያ በሚንቀሳቀሰው አልሸባብ የሽብር ቡድን ሰልጥነው በኢትዮጵያ የጥፋት ተልዕኮ ተሰጥቷቸው ወደ ስምሪት ሊገቡ የነበሩ ስድስት ተጠርጣሪ ግለሰቦች በአዲስ አበባ ከተማ እና በኦሮሚያ ክልል በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አስታውቋል፡፡

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዛሬ ለኢፕድ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ ጃፋር ያያ ረቢ፣ ሙሳ ቀና ቤኛ፣ አደም ቤካ ኬነሳ፣ አብዱራዛቅ ሻፊ አሊ፣ አብዱል ከሪም አህመድ ኩሽዬ እና ዘቢር ጂያድ ከድር የተባሉት ተጠርጣሪዎች በሶማሊያ በሚንቀሳቀሰው የአልሸባብ የሽብር ቡድን ተመልምለው በኢትዮጵያ በህቡዕ ድጋፍ በሚያደርጉ አካላት አማካኝነት ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ተሰባስበው ከየካቲት 2 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ወቅቶች ወደ ሶማሊያ እንዲገቡ ተደርጓል፡፡

በእዚያም የሽብር ጥቃት ለመፈጸም የሚረዱ የተለያዩ ስልቶችንና የቡድኑን አስተምህሮ የተመለከቱ ስልጠናዎች ለሶስት ወራት ወስደዋል፡፡

በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የሽብር ጥቃት እንዲፈጽሙ የተመለመሉትና ስልጠና የወሰዱት ስድስቱ ተጠርጣሪ ግለሰቦች ግንቦት 3 ቀን 2014 ዓ.ም ከሶማሊያ ተነስተው በሞያሌ በኩል ወደ ሀገር ውስጥ መግባታቸውን የሚያመለክተው የአገልግሎት መሥሪያ ቤቱ መረጃ፤ ሚያዚያ 4 እና 5 ቀን 2014 ዓ.ም በሁለት ቡድን ተከፍለው ወደ ጅማ ለመሄድ አቅደው እንደነበርም ጠቁሟል፡፡

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት በአልሸባብ ቡድን ላይ በሚያደርገው ክትትልና የመረጃ ስምሪት መነሻነት የጥፋት እቅዱን ከውጥኑ ጀምሮ ሲከታተል እንደነበር ያመለከተው መግለጫው፤ የሽብር ቡድኑ በኢትዮጵያ ያለውን የግንኙነት መረብ ጭምር ለማወቅና እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል መረጃ ሲሰበሰብና ሲጠናቀር ቆይቶ ከጸጥታ አካላት ጋር በተከናወነ ኦፕሬሽን ተጠርጣሪዎቹ በአዲስ አበባ ከተማ እና በኦሮሚያ ክልል ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ፣ ከኦሮሚያ ፖሊስ እና ከአዲስ አበባ ጋር በመተባበር በተከናወነ ኦፕሬሽን በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን ገልጿል፡፡

እንደ አገልግሎት መስሪያ ቤቱ መግለጫ የሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር በዋሉበት ወቅት የተለያዩ የጦር መሣሪያዎች፤ የሽብር ቡድኑን አስተምህሮ ለማስረጽ ጥቅም ላይ የሚውሉ ሰነዶች እና ሌሎችም ተቀጣጣይ ቁሶች ተይዘዋል፡፡

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት በአዲስ አበባና በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሽብር ጥቃት ለመፈፀም ዝግጅት ሲያደርጉ የነበሩ 34 የሽብር ቡድኑ የአልሸባብ አባላትን ከሶማሌና ከኦሮሚያ ክልሎች የጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር ባከናወናቸው ኦፕሬሽኖች ሚያዝያ 2014 ዓ.ም በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ማድረጉን አስታውሷል፡፡

በተከታታይ በተደረጉ ኦፕሬሽኖችም ተጨማሪ 11 በሽብር ጥቃት የተጠረጠሩ ግለሰቦች ተይዘው እንደነበር በመጥቀስ፤ በአጠቃላይ 45 የሽብር ቡድኑ አባላት የሽብር ጥቃቶችን ለመፈጸም ካዘጋጇቸው ቦንቦች፣ ክላሽንኮቭ ጠመንጃዎች፣ መትረየሶች ፣ አርፒጂ የጦር መሣሪያዎች እና መሰል ጥይቶች ጋር ከክልልና ከፌደራል ፀጥታ ሀይል ጋር በመሆን በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝ የአገልግሎት መሥሪያ ቤቱ መግለጫ ጠቅሷል፡፡ via ENA

Related posts:

«ሕወሓት ጦርነትን እንደ አምልኮ የሚቆጥር ቡድን ነው» – ፕሮፌሰር ሀረገወይን አሰፋ
«በሕገወጦች ላይ ያለ ምኅረት እርምጃ መውሰድ አለብን፤ ይህ የመንግሥት ተግባር ነው» የአማራ ክልል
125 አዳዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ
«በአገሩ መከላከያ ላይ አፉን የሚከፍት ሕዝብ የለም፤ መንግስትም አይታገስም» ክብር ለመከላከያ ሰራዊት!!
በኢትዮጵያና ቱርክ መካከል የተደረገውን የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነት ምክር ቤቱ አጸደቀ
የሞት ፍርደኛው የ25 ዓመታት ሰቆቃ! ከመሬት በታች የታፈኑት አባት
«ኢትዮዽያን ማስቀጠል ከሚፈልጉት ጎን በመሆናችን የሚከፋ ከአለ እርሱ መፍረሷን የሚናፍቅ ብቻ ነው!»
ደብዳቤ ለኢትዮጵያ - ከቢልለኔ ስዩም
የዓለም ባንክ የ300 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ፈረመ
"እናቴ ፍጹም እስር ቤት እንድትገባ አልፈግም" ብሎ እግሩን ያጣው ወጣት ምስክርነት ለሮይተርስ
"አልዘምትም" ወይም "ከጠላት ጎን እሰለፋለሁ" ማለት ሲቻል ማውሰብሰብና ማድበስበስ አይገባም!
አብዱላሂ ፋርማጆ ለአዲሱን ፕሬዝዳንት «ሁሉም ወገኖቼ እንዲደግፉህና እንዲጸልዩልህም እጠይቃለሁ»
መንግስ የጸጥታ ሃይሎች ለየትኛውም ዓይነት ትንኮሳ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ማድረጉን አስታወቀ
በትግራይ 5.2 ሚሊዮን ሕዝብ ዕርዳታ እየደረሰ ነው፤ ከሺህ በላይ የጭነት መኪኖች ታግተዋል፤ 76 ቢሊዮን ብር ወደ ትግራይ ተልኳል
የደህንነት ጥናት አዲሱ ምዕራፍ - ጂኦስፓሻል ኢንተለጀንስ

Leave a Reply