በአገር አቋራጭ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ ተደረገ

በአገር አቋራጭ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭ ተሽከርካሪዎች ላይ የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ ተደረገ

በነዳጅ ጭማሪ ምክንያት በአገር አቋራጭ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ለሚሰጡ ተሽከርካሪዎች የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ መደረጉን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ የአገር አቋራጭ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ለሚሰጡ ተሽከርካሪዎች የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ ያደረገው ከሚያዝያ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የነዳጅ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ መደረጉን ተከትሎ ነው፡፡

በዚህም መሠረት ነባር ታሪፍ በደረጃ አንድ ተሽርካሪ በአስፋልት መንገድ በሰው በኪሎ ሜትር 0 ነጥብ 493 የነበረው በአዲሱ ታሪፍ በኪሎ ሜትር 0 ነጥብ 039 ጭማሪ በማድረግ በሰው በኪሎ ሜትር ብር 0 ነጥብ 532 ሆኗል ተብሏል፡፡

ደረጃ አንድ በጠጠር መንገድ በሰው በኪሎ ሜትር ታሪፍ 0 ነጥብ 548 የነበረው ወደ 0 ነጥብ 596 ከፍ ብሏል፡፡ በዚህም በኪሎ ሜትር የ 0 ነጥብ 049 ጭማሪ አድርጓል፡፡

በሌላ በኩል በደረጃ ሁለት በአስፋልት መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎ ሜትር 0 ነጥብ 457 የነበረው በአዲሱ ታሪፍ በኪሎ ሜትር የ0 ነጥብ 039 ጭማሪ በማድረግ በሰው በኪሎ ሜትር 0 ነጥብ 496 ሆኗል፡፡

በደረጃ ሁለት በጠጠር መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎሜትር 0 ነጥብ 505 የነበረው በኪሎ ሜትር 0 ነጥብ 039 ጭማሪ በማድረግ በአዲሱ በኪሎ ሜትር 0. ነጥብ 554 ተደርጓል፡፡

ደረጃ ሦስት በአስፋልት መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎ ሜትር 0 ነጥብ 416 ይከፈልበት የነበረው 0 ነጥብ 039 በኪሎሜትር ጭማሪ በማድረግ 0 ነጥብ 455 በኪሎሜትር እንዲሆን ተወስኗል፡፡

ደረጃ ሦስት በጠጠር መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎ ሜትር 0 ነጥብ 471 የበነረው በኪሎ ሜትር የ0 ነጥብ 049 ጭማሪ በማድረግ በኪሎ ሜትር 0 ነጥብ 520 ሆኗል፡፡

የተደረገው የታሪፍ ማስተካከያ በ100 ኪሎ ሜትር ሲታይ በደረጃ አንድ ተሽርካሪ ለአንድ ሰው በነባር ታሪፉ በአስፋልት መንገድ ብር 49 ነጥብ 29 ይከፈል የነበረው በአዲሱ ብር 53 ነጥብ 16 ሆኗል፡፡ ይህም በ100 ኪሎ ሜትር ጭማሪ ያደረገው የብር 3 ነጥብ 87 ነው፡፡

በደረጃ ሁለት ተሽከርካሪዎች ለአንድ ሰው በነባር ታሪፍ በ100 ኪሎ ሜትር 45 ነጥብ 70 ያስከፍል የነበረው በ100 በኪሎ ሜትር ብር 3 ነጥብ 87 በመጨመር 49 ነጥብ 58 በ100 ኪሎ ሜትር ሆኗል፡፡

በተመሳሳይ በደረጃ ሦስት ተሸርካሪ በ100 ኪሎ ሜትር ለአንድ ሰው ብር 41 ነጥብ 61 ያስከፍል የነበረው በ100 ኪሎ ሜትር የ3 ነጥብ 88 ጭማሪ በማድረግ በ100 ኪሎ ሜትር ብር 45 ነጥብ 49 ሆኗል መባሉን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

Via OBN

Related posts:

በሳዑዲና ኢራን በሞት የሚቀጡ ሰዎች ቁጥር ጨምሯልMay 26, 2022
የመሰረተ ልማት ቀበኞች ላይ " የሞት ቅጣት"May 26, 2022
ኢሳያስ - ዘመቻው እስከ መጨረሻ ቀብር ይሆናል ሲሉ ትህነግን አስጠነቀቁMay 25, 2022
በአማራ ክልል እፎይታ እየነገሰና የትህነግ የወረራ ዕቅድ መምከኑ ተሰማMay 25, 2022
ንግድ ባንክ ለአፈር ማዳበሪያ ግዥ ከ50 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ማድረጉን አስታወቀMay 25, 2022
ቢለኔ ታይም መጽሔትን ማብራሪያ ጠየቁ፤ የተሰላ ጥቃትና የአንድ ወገን ትርክት ማቅረቡን ኮንነዋልMay 25, 2022
"ከውስጥ በር ለማስከፈት ... ከጣራ በላይ ጩኸት" አብን አማራን ለሶስተኛ ዙር ወረራ እያመቻቹ ያሉትን በይፋ አወገዘMay 24, 2022
በኢትዮጵያ በተከሰቱ ግጭቶች ሁሉ የትህነግ እጅ እንዳለባቸው በመረጃ ተረጋገጠMay 24, 2022
ፋኖ እየጨፈረ ከመከላከያና አማራ ልዩ ሃይል ጋር የግዳጅ ቀጠናውን ተረከበMay 23, 2022
ተልዕኮ አስፈጻሚዎችና ከ1780 በላይ ሕዝባዊ ኀላፊነታቸውን ያልተወጡ ተጠርጣሪዎች ተያዙMay 23, 2022
በሕግ ማስከበር ዘመቻ ከ4 ሺህ በላይ ተጠርጣሪዎች በሕግ ቁጥጥር ስር ዋሉMay 23, 2022
በአማራ ክልል መፈንቅለ መንግስት ታቅዶ ነበርMay 23, 2022

Leave a Reply