የአለም ዋንጫ ገዳሟ ሴት!!

ሴኔጋላዊቷ ሴት ቪቪያን ዲዬ የአለም ዋንጫ ገዳሟ ሴት ተሰኝታለች።

ይህች ሴኔጋላዊት ከቀናት በፊት ትልቅ ግምት የተሰጣት አርጀንቲናን ማሸነፍ የቻለችው የሳውዲ አረቢያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ኸርቬ ሬናርድ ባለቤት ናት።

በአለም ዋንጫ ገዳም ያስባላትም ከሃያ አመት በፊት ሴኔጋል በ2002 የአለም ዋንጫ ሳይጠበቅ ፈረንሳይን 1ለ0 ስታሸንፍ የሴኔጋል አሰልጣኝ የነበሩት ብሩኖ ሜትሱ ባለቤት በመሆኗ ነው።

ቪቪያን አሰልጣኝ ሜትሱ ሴኔጋልን እያሰለጠኑ ፈረንሳይን ሲረቱ በስቴድየም ውስጥ ነበረች። አሁንም በኳታሩ የአለም ዋንጫ ሬናርድ ሳውዲ አረቢያን በማሰልጠን ታላቋን አርጀንቲና ሲያሸንፉ ቪቪያን ከጎናቸው ነች።

ቪቪያን ዲዬ ከቀድሞ ባለቤቷ ሜትሱ እኤአ 2013 ላይ በአሳዛኝ ሁኔታ በካንሰር ህመም ህይወቱ ከማለፉ በፊት ሶስት ልጆችን አፍርተዋል።

የአሁኑ የሳውዲ አሰልጣኝ የ54 አመቱ ሬናርድ ቀደም የሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ በነበረበት ወቅት ከቪቪያን ጋር በትዳር የተጣመረ ሲሆን የሶስት ልጆች አባትም ነው።

ቪቪያን የቀድሞ ባለቤቷ ትንሽ ግምት የተሰጠውን ቡድን እያሰለጠነ በአለም ዋንጫ ትልቅ ቡድን አሸንፏል።

የአሁኑ ባለቤቷም ተመሳሳይ ገድል በመፈጸሙ ገዳሟ የአለም ዋንጫ ሴት እንድትባል አድርጓል።
በቦጋለ አበበ ENA

See also  *የላቀ የጦርሜዳ ኒሻን ተሸላሚው

Leave a Reply