መከላከያ የሕወሓት ታጣቂዎችን ከዋግ ኽምራ ሊያስወጣ መሆኑ ተሰማ

በፌደራል መንግስትና ሕወሓት መካከል ከተፈረመው የሰላም ስምምነት በኋላም፣ በሕወሓት ቁጥጥር ሥር የነበሩት የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ኹለት ወረዳዎች በመከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ሥር ሊውሉ እንደሆነ ታውቋል፡፡

በሕወሓት ቁጥጥር ሥር ያሉት ወረዳዎች ጻግብጂና አበርገሌ ሲሆኑ፣ በአካባቢዎቹ ከ67 ሺሕ በላይ የሚሆኑ የኹለቱ ወረዳ ነዋሪዎች ተፈናቅለው በችግር ላይ እንደሚገኙ መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ተፈናቃዮቹ ለከፍተኛ ችግር መዳገራቸውን ተከትሎ ወደ ቀየያቸው ተመልሰው እንዲቋቋሙ ለማድረግ እየጣርኩ ነው ያለው የዋግ ሕምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን አደጋ መከላልና የምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽ/ቤት፣ መከላከያ ሰራዊት በአጭር ቀናት ውስጥ አካባቢዎቹን ነጻ እንደሚያደርግ ቃል መግባቱን ለአዲስ ማለዳ አስታውቋል፡፡

የጽ/ቤቱ ኃላፊ ምኅረት ታምሩ ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት፣ መከላከያ ሰራዊት ኹለቱን ወረዳዎች በአጭር ቀናት ውስጥ ከሕወሓት ነጻ በማውጣት የአካባቢው ነዋሪዎች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ለማድረግ እንደሚሰራ ለዞኑ አስታውቋል፡፡

በዚህም መከላከያ ሰራዊት ለዞኑ የጸጥታ ማረጋገጫ እስኪሰጥ ድረስ እየተጠበቀ ነው ያሉት ምኅረት፣ ሰራዊቱ በምን አይነት ሁኔታ ወረዳዎቹን እንደሚቆጣጠር አናውቅም ብለዋል፡፡

ይህንኑ መሰረት በማድረግም ጽ/ቤታቸው ከ15 መንግስታዊ ያልሆኑ የእርዳታ ድርጅቶች ጋር ተፈናቃዮችን ወደየቀያቸው መመለስ ስለሚቻልበትና መልሰው ስለሚቋቋሙበት ሁኔታ ሀሙስ የካቲት 23 በሰቆጣ እንደተወያዩ ኃላፊው ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል፡፡

አዲስ ማለዴ

See also  ኢ/ር ይልቃል መንግስት ከትህነግ ጋር ይደራደር አሉ፤ "ወያኔው ይልቃል የወልቃይትና የራያ ህዝብ ላይ ክህደት በመፈጸም ሊጠየቅ ይገባል"

Leave a Reply