መከላከያ የተዘጋ መንገድ ድንጋይ ሲያነሳ በጥይት እርምጃ ተወስዶበታል፤

የአገር መከላከያ የተዘጋ መንገድ ለመክፈት ድንጋይ ሲለቅም ጥይት ተተኩሶበት ጓዶቹን አጥቷል። ድርጊቱ መከላከያ ጥይት እንዲተኩስና ክልሉ ወደ ለየለት ግጭት እንዲያመራ ለማድረግ ሆን ተብሎ የታቀደ መሆን እየተነገረ ነው። መንገድ ባተዘጋባቸው አካባቢዎች እስካሁን ክልሉም ሆነ የፌደራል ሃይል ይህ እስከተጻፍበት ድረስ ማናቸውንም ሃይል አልተጠቀመም።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ማለዳ ላይ ባስተላለፉት ጥሪ ይህ አካሄድ ክልሉን ከማድቀቅ ውጭ አንዳችም የሚኦያመጣው ጠቀሜታ ስለሌለ ረጋ ብሎ ማሰብ እንደሚገባ፣ አባቶች፣ እናቶች፣ የሃይማኖት መሪዎችና ያገባናል የሚሉ በትብብር የሃይል አካሄዱን በምክር እንዲያስቆሙ ተማጽነዋል።

አሁን ማምሻውን እንደተሰማው የኢትዮጵያ መከላከያ ላይ ጥይት በመተኮስ ጉዳት ደሷል። የጉዳቱ መጠን ባይገለጽም፣ የአገር መከላከያ ሃይል ጉዳቱ ሲደርስበት ምንም ዓይነት የአጻፋ እርምጃ እንዳልወሰደ ምስክሮች ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የተለያዩ የኢትዮጵያ ልጆች የተካተቱበት በመሆኑ አማራ ክልል በስውርም ሆነ በድብቅ መከላከያ ላይ የሚደርሰው ግድያ የማራን ህዝብ ከሌሎች ወገኖቹ እንዳይለየው አመጹን ከጀርባ ሆነው የሚመሩ ወገኖች ሊያስቡበት እንደሚገባ ዜናውን የነገሩን ገልጸዋል።

በዘር እሳቤ ላይ ተተክላ በትህነግ መሃንዲስነት የተሰራቺው ኢትዮጵያ፣ የጎሳና አጥንት ፖለቲካ ከውስጧ እንዲነቀል በየክልሉ ያሉትን ታጣቂዎችና የኮንትሮባንድ አመላላሾች ወደ ህጋዊ መስመር፣ ወደ ማዕከላዊ የዕዝ ሰንሰለት ማስገባት ለነገ ሊባል የማይገባው ጉዳይ መሆኑንን ቀደም ሲል በተለያዩ ወገኖች ማለትም ምሁራን፣ ተቅዋሚ ፓርቲዎች፣ ህዝብ፣ እንዲሁም አማካሪዎች ሲገልጹት የቆዩትና መንግስት “አልሰማ አለ” ተብሎ የሚወቀስበት የምርጫ መሟገቻ አጀንዳም እንደነበር ይታወሳል።

ዛሬ ላይ የጎሳ ፖለቲካ የሚቃወሙ፣ ጎሳ ላይ ተንጠልጥሎ የተዘጋጀውና መፈራረስን የሚያበረታታው ህገመንግስት እንዲቀደድ ሲሟገቱ የነበሩ ሳይቀሩ ሁሉም ክልሎች ተግባራዊ ለማድረግ የወሰኑትን የክልሎች ልዩ ሃይልን ወደ ህጋዎ የእዝ ሰነሰለት ማስገባት ስራ ለምን እንደፈሩትና በዚህ ደረጃ እንደተቃወሙት ግልጽ አይደለም።

በመከላከያ ላይ ዕምነት ማጣት ወይም ሌላ አጀንዳ ግልጽ ባልሆነበት በአሁኑ ሰዓት የአማራ ክልል አንዳንድ ከተሞች ራሳቸው ላይ መንገድ ቆልፈዋል። የተጀመረው ተግባር እንዲቆም የጠየቁ አሉ። ጥያቄያቸው ግን በሁሉም ክልል ልዩ ሃይል እስከ አፍንጫው ታጥቆ ይቀጥል ወይም የአማራ ክልል ብቻ ባለበት ሳይነካ ሌሎቹ ላይ ተግራዊ ይደረግ እያሉ እንደሆነ ግልጽ አላደረጉም።

See also  የትግራይ የተቆላለፈ እጅ፤ እየቀለበች የምትደማ አገር

ይህንኑ አለመግባባት ተከትሎ ኦሮሚያ የሸገር ከተማ ማቋቋሙን መቃወምና ክልሉ ህገወጥ ናቸው ብሎ ግንባታ ያፈረሰባቸውን ዜጎች “አማራዎች ላይ በተለይ የተደረገ በደል ነው” በሚል አንስተዋል። አብን በግልጽ ይህን ጉዳይ አንስቶ ተቃውሞውን አሰምቷል።

የተጀመረው የልዩ ሃይልን መልሶ የማደራጀት ተግባር፣ እንዲቆም ቢጠየም መንግስት በውይይት በማሳመን፣ ከገፋም ህጋዊ እርምጃ ወስዶ እንደሚያከናውነው ይፋ አድርጓል። ጉዳዩን ረጋ ብሎ መመርመርና በተለይ አማራ ክልል ላይ የሚደረግ ምንም ዓይነት ነገር እንደሌለ ያመለተው የክልሉ መንግስት፣ ስከኑ ብሏል። መከላከያም ፖለቲከኞች በተጣሉ ቁጥር መታኮስ እንደሰለቸው ገልጹ የተጀመረውንንና ህገ መንግስታዊ ድጋፍ ያለውን ሂደት እንደሚገፋበት አስታውቋል።

ከሁሉም በላይ ኮንትሮባንድና ሌብነት፣ ሽፍትነት መንግስትን እንዳማረረው ገልጾ መንግስት እንዳስታወቀው በዚህ መልኩ እያነከሱ መኖር አይቻልም። ኢትዮጵያን የሚወድ ልዩ ሃይል ፣ ክልሉንንና ህዝቡን የሚወድ መከላከያ ወይም ፌደራልና የክልሉ ፖሊስ አባል በመሆን ህጋዊ መስመርና የዕዝ ሰንሰለት ውስጥ መግባት ለምን አስፈሪ ሊሆንበት እንደሚችል ለብዙዎች ግልጽ አይደለም።

ጉዳዩ በጥንቃቄና በምክክር እንዲከናወን ከማሳሰብ ውጭ በመርህ ደረጃ ተግባሩ ነቀፌታ አልተሰማበትም።

ቆቦ ከተማ የሰዎች ህይወት አልፏል።አሁን ላይ የቆቦ ከተማን ፀጥታ የሀገር መከላከያ ሰራዊቱ እየተቆጣጠረ ነው።

Leave a Reply