ህፃን ልጅ ከአርባ ምንጭ አምጥቶ ጉልበት በመበዝበዝ ገንዘብ ሲያገኝ የነበረው በእስራት ተቀጣ

ህፃን ልጅ ከአርባ ምንጭ አምጥቶ የሽመና ስራ ላይ በማሰማራትና ጉልበት በመበዝበዝ ገንዘብ ሲያገኝ የነበረው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

ተከሳሽ አደለ ዶሌ ሀማ የ12 ዓመት እድሜ ያለውን ህጻን ማርቆስ በሎላን የካቲት 12 ቀን 2015 ዓ.ም ከደቡብ ክልል አርባ ምንጭ ከተማ ጨንቻ ወረዳ ወደ አዲስ አበባ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አጓጎዞ በማስመጣትና ለሽመና ስራ የሚያስፈልጉትን ዕቃዎች በማዘጋጀት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከጥዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ ማታ 12፡00 ሰዓት ድረስ የሽመና ስራ እንዲሰራ በማድረግ ጉልበቱን በዝበዟል፤ እንዳይማር አድርጓል።

በዚህም መሰረት በጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የሴቶችና ህፃናት ምርመራ ክፍል እና በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ዓ/ሕግ ዳይሬክቶሬት በኩል ምርመራ ከተጣራ በኋላ በሰው የመነገድና ሰውን በሕገ ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀልን ለመከናከልና ለመቆጣጠር በወጣውን አዋጅ ቁጥር 1178/12 አንቀፅ 3(1) ላይ በተደነገገው መሰረት በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት መናገሻ ምድብ ችሎት በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ዓ/ሕግ ዳይሬክቶሬት በኩል በተከሳሽ ላይ ክስ ቀርቦበት ክርክር ተደርጓል፡፡

ፍ/ቤቱም በተከሳሽ ላይ የጥፋተኛነት ፍርድ በመስጠት በ5 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት እና በብር 7000 /ሰባት ሺህ ብር/ እንዲቀጣ ሲል ወስኖበታል፡፡

Minstre of justice

See also  በፍትሕ ሚኒስትር ዴኤታ የተመራ የኢትዮጵያ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ለተ.መ.ድ የሰብዓዊ መ.ኮ የአፈጻፀም ሪፖርት አቀረበ

Leave a Reply