ኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካ በወንጀል የሚጠረጠሩ ግለሰቦችን አሳልፎ ለመስጠት የሚያስገድድ ስምምነት ፈረሙ

  • ደቡብ አፍሪካ በርክታ ወንጀል፣ በተለይም በሙስና የሚፈልጉ ንግድ ከፍተው የሚሰማሩባት አገር በመሆኗ ስምምነቱ ከወዲሁ ስጋት መፍጠሩ ተሰምቷል። በቅርቡ ስምምነቱ ተግባራዊ የሚደረግባቸው ይኖራሉ ተብሏል

ኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካ በወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን አሳልፎ ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል። አራተኛው የኢትዮ-ደቡብ አፍሪካ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

በስብሰባው ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የደቡብ አፍሪካ የዓለም አቀፍ ግንኙነቶችና ትብብር ሚኒስትር ዶክተር ናሌዲ ፓንዶር እንዲሁም የሁለቱ አገራት ባለስልጣናት ተሳታፊ ሆነዋል። በዚህ ወቅት ሁለቱ አገራት በወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን አሳልፎ ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱን የፍትሕ ሚኒስትር ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ እና የደቡብ አፍሪካ የዓለም አቀፍ ግንኙነቶችና ትብብር ሚኒስትር ዶክተር ናሌዲ ፓንዶር ተፈራርመዋል።

ሁለቱ አገራት በስብሰባው ንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ ሳይንስ፣ ኢኖቬሽን፣ ትምህርት፣ ጤና፣ ባህል እና በሌሎች በርካታ መስኮች የተፈራረሟቸውን የሁለትዮሽ ስምምነቶች ያሉበት የአፈጻጸም ደረጃ በስብሰባው ገምግመዋል። (ኢዜአ)

See also  በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ላይ በተፈጸመ ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ

Leave a Reply