ፕሬዚዳንት ኢሳይስ አፉወርቂ ተቃዋሚ በማደራጀትና በማስታጠቅ የተካኑ፣ በዚህም ችሎታቸው ሱዳንን ሲፈልጉ የሚያበሩና የሚያጨልሙ እንደሆኑ በርካቶች ይመስክሩላቸዋል። አሁን የተሰማው ዜና ደግሞ እሳቸው ሲያደርጉት እንደነበረው በአሳቸው ላይ ተጠምዷል።
“ህግ ይንገስ፣ አምባገነንነት ይንገስ” በሚል ፕሬዚዳንት ኢሳያስ የሚመሩትን መንግስት ለመጣል ያለመ የወጣቶች እንቅስቃሴ በይፋ መጀመሩ ተሰምቷል። ዜናው የምስረታ ስብሰባ ጥሪ በማህበራዊ ገጾች በማሰራጨት ቀድሞ ቢሰማም በምስረታ ስብሰባው ላይ መገኘታቸውን ጠሰው የዘገቡም አሉ።
ከኤርትራ 35 ኪሎሜትር ርቀት በምትገኘዋ የዓዲግራት ከተማ እሁድ ጥቅምት 18/2016 ዓ.ም በተካሄደው የምስረታ ስብሰባ ላይ መገኘቱን ገልጾ በማህበራዊ ሚዲያዎች የተሰራጨው የስብሰባ ጥሪ ትክክል መሆኑን አረጋግጫለሁ ያለው ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሚባለው የዜና አውድ ነው።
ብርጌድ ንሓመዱ የተባለው የኤርትራ መንግስት የሚቃወም የወጣቶች እንቅስቃሴ በትግራይ ኢትዮጵያ ተቋቋመ” ያለው ይህ የዜና ገጽ፣
“የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ በስፍራው ተገኝቶ በስብሰባው ታድሟል” ብሏል።
” ምምስራት ብርጌድ ንሓመዱ ጨንፈር ትግራይ መላእ ኢትዮጵያ ” ተብሎ በስብሰባው የጥሪ ወረቀት ላይ የሰፈረውን “የብርጌድ ንሓመዱ መላ ትግራይ ኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ምስረታ” ብሎ ቲክቫህ ተርጉሞታል። “መላ ትግራይ ኢትዮጵያ” የሚለው አገላለጽ ምን ለማለት እንደሆነ ግን አላብራራውም።
የእንቅስቃሴው አስተባባሪዎች እንዳሉት ፤ ” ከ30 ዓመታት በላይ ያለ ህዝባዊ ምርጫ በአምባገነንነት ተቀምጠዋል ” ያሉትን የኤርትራ መንግስት ለመጣል በመላ ዓለም በሚኖሩ ኤርትራውያን ወጣቶች እየተደረገ ያለው ትግል በመደገፍና በመቀላቀል ትግሉ በመላ ኢትዮጵያ በሚኖሩ ኤርትራውያን ተቀባይነት እንዲያገኝ አበክረው ይሰራሉ።
በዚሁ ርዕስ የተሰራጨው ደብዳቤ ትክክል እንደሆነ በስፍራው ተገኝቶ ያረጋገጠው ቲክቫህ የክልሉንም ሆነ የፌደራል መንግስትን በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየት አላካትተም። ወይም ሞክሮ እንዳልተሳካለት ወይም ሞክሮ የተባለው ነገር ስለመኖሩ ያለው ነገር የለም።
በትግርኛ ቋንቋ የተፃፈውና በማህበራዊ ትስስር ገፆች የተሰራጨው ማህተምና ፊርማ የሌለው በመላ ኢትዮጵያ ለሚኖሩ ኤርትራውያን የተፃፈው ደብዳቤ ሙሉ ቃል እንዲህ ይላል።
“… ይፋዊ ምስረታ ‘ብርጌድ ንሓመዱ ‘ መላ ትግራይ ኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ።
‘ብርጌድ ንሓመዱ ‘ የተባለ የኤርትራውያን ህዝባዊ ማዕበል እንቅስቃሴ ለማጠናከር በምናካሂደው ህዝባዊ ስብሰባ እንድትሳተፉ በክብር ጥሪ እናቀርባለን።
የስብሰባ ቦታ ዓዲግራት ትግራይ !!
ሕጊ ይንገስ
ምልኪ ይፍረስ !!
ህግ ይንገስ
አምባገነንነት ይፍረስ ” የሚል ነው።
የጥሪ ደብዳቤውን በመከተል የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል እሁድ ጥቅምት 18/2016 ዓ.ም ከመቐለ ወደ ዓዲግራት ተጓዘ ።
ስብሰባ ይካሄድበታል ወደ ተባለ ቦታ በመሄድ ከአስተባባሪዎች ተገናኘ። አስተባባሪዎቹ ለድህንነታቸው ሲባል ስማቸው ምስላቸውና በኤርትራ የየት አከባቢ ነዋሪዎች እንደነበሩ ለመጥቀስ ፍቃደኞች አይደሉም።
የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ከአስተባባሪዎቹ በመሆን ስብሰባ ወደ ተጠራበት ሰፊ አዳራሽ ይደርሳል። በሰፊ አዳራሹ ቁጥራቸው አነስተኛ ተሰብሳቢዎች ተገኙ።
አስተባባሪዎቹ ለጥንቃቄ ሲባል ፎቶ ማንሳትም ሆነ ድምፅ መቅረፅ አይፈቀድም ባሉት መሰረት የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ሪፓርተር የተባለውን በመቀበል ሰብሰባውን ተከታትሏል።
ይኸው የቲክቫህ ቤተሰብ አባል እንደረጋገጠው ‘ብርጌድ ንሓመዱ ‘የተባለው የኤርትራ መንግስት የሚቃወም የወጣቶች እንቀስቃሴ ‘ ብርጌድ ንሓመዱ ጨንፈር ትግራይ መላእ ኢትዮጵያ ‘ ማለት የ ‘ብርጌድ ንሓመዱ ‘ የመላ ትግራይ ኢትዮጵያ ቅርንጫፍ በይፋ በዓዲግራት ተቋቁመዋል። እንቅስቃሴው የሚያስተባብሩ አመራሮቹም መርጠዋል።
የእንቅስቃሴው አስተባባሪዎች እንዳሉት ፤ ” ከ30 ዓመታት በላይ ያለ ህዝባዊ ምርጫ በአምባገነንነት ተቀምጠዋል ” ያሉትን የኤርትራ መንግስት ለመጣል በመላ ዓለም በሚኖሩ ኤርትራውያን ወጣቶች እየተደረገ ያለው ትግል በመደገፍና በመቀላቀል ትግሉ በመላ ኢትዮጵያ በሚኖሩ ኤርትራውያን ተቀባይነት እንዲያገኝ አበክረው ይሰራሉ።
የ ‘ ብርጌድ ንሓመዱ መላ ትግራይ ኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ‘ በሚል የኤርትራ መንግስት የሚቃወም የወጣት ኤርትራውያን እንቅስቃሴ በይፋ የተመሰረተባት የትግራይዋ ዓዲግራት ከተማ ከኤርትራ ደንበር በ35 ኪሎ ሜትር ርቀት ትገኛለች ሲል ቲክቫህ ኢትጵያ የመቐለ ቤተሰብ ከዓዲግራት ዘግቧል።
የቲክቫህ ዜና ይህን ቢልም ኢትዮጵያና ኤርትራ ወታደራዊ ስምምነትን ያካተተ ውል ማሰራቸውን የሚያውቁ፣ አንዱ በሌላው ላይ አማጺ እንደማያደራጅ ስምምነት መኖሩን ጠቅሰው በዜናው መገረማቸውን አመልክተዋል።
መንግስት ከትህነግ ጋር ስምምነት አድርጎ ጊዚያዊ መንግስት ማቋቋሙን ተከትሎ በኤርትራ በኩል ቅሬታ መሰማቱ አይዘነጋም። ፕሬዚዳንት ኢሳያስ በይፋ ይህንኑ የሰላም ውል ተቃውመው ደስተኛ እንዳልሆኑ መናገራቸውም ይታወሳል። በዚህ ይሁን በሌላ ተጨማሪ ጉዳይ በግልጽ ባይታወቅም ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ከእነ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌና የመንግስት መዋቅር ውስጥ ካሉ ጋር በመሆን የአማራን ክልል መፈንቅለ መንግስት እንዲደረግበት ማሴራቸውን በመግለጽ ውሉ የተጣሰው በነሱ በኩል እንደሆነ የገለጹም አሉ።
ኤርትራ አገር ከመሆኗ በፊትና ከተገነጠለች በሁዋላ ኢትዮጵያ ላይ ተቃዋሚ ማዘጋጀትንና የልዩ ጥቅም ማስከበሪያ ማድረግን እንደ ቁልፍ ስልት የሚጠቀሙት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ፣ በአማራ ክልል ድንገት ተጀምሮ ከተስፋፋው አመጽ ጀርባ እንደሆኑ ማስረጃ ጠቅሰው የሚናገሩ፣ አካሄዱ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው እንደሆነ አመልክተዋል።
ዜናው ከሁሉም አቅጣጫ ቀልብ የሳበ ቢሆንም ይህ እስከታተመ ድረስ ከሁሉም ወገን ይፋዊ ምላሽ አልተሰጠበትም።
- ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያና የደኅንነት ስጋት – አቅራቢ፣ ፈላጊ፣ ነጋዴ፣ ደላላ ተገናኙና መደበኛ ገበያ ሆነ!በፖለቲካም ሆነ በአካባቢያዊ አጀንዳ ነፍጥ ያነገቡ እና ጦርነትን አማራጭ አድርገው የሚንቀሳቀሱ ኢ -መደበኛ አደረጃጀቶች ሁሉ የጦር መሳሪያ ፍላጎት ይኖራቸዋል፡፡ የጦር… Read more: ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያና የደኅንነት ስጋት – አቅራቢ፣ ፈላጊ፣ ነጋዴ፣ ደላላ ተገናኙና መደበኛ ገበያ ሆነ!
- ምን ያክል ተዘጋጅተናል? ጥድፊያ አገር አልባ ለመሆን !! ህጻናቱ ምን አጠፉ?ያለፈውን ግማሽ ምዕተ ዓመት የኢትዮጵያ ፖለቲካ እና ሥነ መንግሥት ታሪክ በጥሞና የተከታተለ ኢትዮጵያዊ የግዛት አንድነቷን እና የፖለቲካ ነጻነቷን በአንጻሩ ጠብቃ… Read more: ምን ያክል ተዘጋጅተናል? ጥድፊያ አገር አልባ ለመሆን !! ህጻናቱ ምን አጠፉ?
- የደም ግፊት በመለካትና ክትትል በማድረግ የስትሮክ ተጋላጭነትን መቀነስአንድ ሰው የደም ግፊት መጠኑ ከፍተኛ ከሆነ እና በጊዜው ሕክምና ካላደረገ ለከፍተኛ የልብ በሽታና በደም ዝውውር ማነስ ምክንያት ለሚከሰት የአዕምሮ… Read more: የደም ግፊት በመለካትና ክትትል በማድረግ የስትሮክ ተጋላጭነትን መቀነስ
- የስኳር ህመም አይነቶች እና ምልክቶችየስኳር ህመም በደም ውስጥ የስኳር መጠን ከሚገባው በላይ ሆኖ በሚገኝበት ሰዓት የሚከሰት ተላላፊ ያልሆነ የህመም አይነት ነው። በዋናነት አራት የስኳር… Read more: የስኳር ህመም አይነቶች እና ምልክቶች
- ማንኮራፋትና ትዳርን እስከ ማፍረስ የሚያደርሰው መዘዙ ? ማንኮራፋት መፍትሄ አለው?የማንኮራፍት መዘዙ እንቅልፍ ማሳጣት ብቻ አይደለም። ማንኮራፋት ከሚያንኮራፉት ሰዎች ጎን በሚተኙ ሰዎች አካላዊ እና አእምሮ ጤና ላይ ጉዳት ያስከትላል። ትዳርንም… Read more: ማንኮራፋትና ትዳርን እስከ ማፍረስ የሚያደርሰው መዘዙ ? ማንኮራፋት መፍትሄ አለው?