ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይፋ መሆን የጀመሩ የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎች ” እውን እስካሁን የት ነበርን” የሚያሰኝ እንደሆነ በየአቅጣጫው ቀና ልቡና ካላቸው ወገኖች የሚሰማ ድምጽ ነው። ሰላም ቢሰፍንና አገሪቱ ከሴራ ፖለቲካ ብትፈወስ ምን ሊታይ እንደሚችልም ምኞታቸውን የሚገልጹ ጥቂት አይደሉም። ” ምን ዋጋ አለው?” በሚል የሚያጣጥሉም አሉ።
መልካም ጉዳይን አበረታቶ የጎደለውን በመጠቆም፣ ክፉውን ተግባር የሚተች የተቃውሞ አውድ ወይም የተቃዋሚ ድርጅት ባለመኖሩ፣ በአብዛኛው ሚዲያዎችም ከሟርትና ከአስደንጋጭ ዜና አዙሪት ለመላቀቅ አለመፈለጋቸው፣ ቢፈልጉም ላይክና ሼር ስለሚጉዝደል ጉሮሮ ስለሚዘጋ፣ አብዛናው የማህበራዊ ሚዲያም ተሰበረ፣ ወደመ፣ ተደመሰሰ፣ ፈረሰ፣ ተገደለ፣ ተማረከ ወዘተ ከሚሉ ዜናዎች ውጭ ስሜት ስለማይሰጠው በኤትዮጵያ ነገሮች ሁሉ ግራ የሚያጋቡ እንደሆኑ በዚሁ ችግር ዙሪያ ጥናት ያካሄዱ፣ የታዘቡ ይገልጻሉ።
በተለያ በአብዛኛው ሊባል በሚችል ደረጃ የሚዲያ ዘርፉ ቁልቁል ሄዶ መከስከሱ፣ የፖለቲካ አጀንዳ አራጋቢ መሆኑና በተወሰኑ ሃይሎች የሚደጎም መሆኑ የኢትዮጵያን ፖለቲካ አታካች አድርጎታል። ዓላማው ህዝብ እንዲሰላችና ዘወትር ምሬት ውስጥ እንዲወድቅ በመሆኑ፣ ከመንግስት ድክመት ጋር ተዳምሮ ኢትዮጵያን እጅግ እየጎዳት ነው።
“የአባይ ግድብ ተሸጠ” በሚል “የውስጥ አዋቂዎች ነገሩኝ” የሚል ተከፋይ ሚዲያ፣ ግድቡ እንደተባለው አለመሸጡ፣ ይልቁንም ተጠናቆ ሙሉ በሙሉ ኤለኤክትሪክ ለማምረት ከጫፍ መድረሱ በውል እየታየ ይቅርታ አይጠይቅም። ይህንኑ ልዩ ተልዕኮ ያለው ዜና በጅምላ ያሰራጩ በተመሳሳይ እርምት አይወስዱም። ከሁሉም በላይ ትልልቅ የሚባሉትን ጨምሮ ተከፋዮቹ ሚዲያዎች ሆን ብለው በተደጋጋሚ ስህተት ሲያትሙና ሲያሰራጩ በውል እየታየ አንባቢ፣ ተከታይ፣ አከፋፋይ “ውሸታም” ብሎ ሲቃወምና ጥንቃቄ ሲወስድ አይታይም። የጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክን ጭምሮ የጫካ ፕሮጀክትና መላው የገበታ ለአገር ፕሮጀክቶች ላይ የተረጨው የሃሰት ፕሮፓጋንዳ እንደሚለው ሳይሆን ውጤቱ ሌላ ነው።
የውድቀትና የክስረት ዜና ሲረጭበት የነበረው የጨበራ ጩርጩራ ፕሮጀክት ይህን ይመስላል
የጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በኮንታና በዳውሮ ዞኖች መካከል የሚገኝ ሲሆን ካለው ዕምቅ ከተፈጥሮ ሀብት አንፃር በቀዳሚነት ስሙ ይነሳል፡፡
ብሔራዊ ፓርኩ በ1997 ዓ.ም በኮንታና በዳውሮ ህዝቦችና አስተዳደር አካላት ጥያቄና ተሳትፎ መሰረት በብሔራዊ ፓርክ ደረጃ የተቋቋመ ሲሆን ፓርኩ የሚያካልለው የቆዳ ስፋት 1410 ካሬ ኪሎ ሜትር ስኩዌር ሲሆን በመካከለኛው ኦሞ ሸለቆ ውስጥም ይገኛል፡፡
ብሔራዊ ፓርኩ ከመዲናችን አዲስ አበባ በ475 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል።
ፓርኩ የግዙፉ የአፍሪካ ዝሆን መኖሪያ ሲሆን በውስጡ ከ800 በላይ የሚሆኑ ዝሆኖችና ከ 5 ሺሕ በላይ ጎሾች የሚገኙበት መሆኑ ፓርኩን ልዩ ያደርገዋል፡፡
በተጨማሪም 40 ትላልቅና መካከለኛ አጥቢ እንዲሁም 18 ትናንሽ አጥቢ የዱር እንስሳት ዝሪያዎች በውስጡ ይገኛሉ።
በጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክ እንደ አጥቢዎቹ ሁሉ የበርካታ አዕዋፋት ዝርያዎች መኖሪያም ጭምር ነው፡፡ እስካሁን በተጠናው ጥናት 137 የአዕዋፍ ዝርያዎች የተለዩ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 6ቱ በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙ ናቸው፡፡
ፓርኩ በብዙ መልኩ የተፈጥሮ ሀብቱ የተጠበቀ ፓርክ ነው ያስባለው የእጽዋት ስብጥሩ እና ደኑ ነው። 106 እንጨታማ የእጽዋት ዝሪያዎች የሚገኝበት ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ስድስቱ የእጽዋት ዝርያዎች በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙ ናቸው፤ በተጨማሪም በውስጡ ከሚገኙ የዱር ዕፅዋት ዝሪያዎች መካከል ዝንጅብል፣ ቡና፣ ኮረሪማ፣ እንሰት፣ እጣንና የጌሾ ዝርያዎች ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
በፓርኩ ውስጥ ብቻ 6 ሀይቆች የሚገኙ ሲሆን ባሄ፣ ቡሎ፣ ሺታ፣ ቆቃ፣ ከሪቤላና ጮፎሬ እጅግ አስደናቂና ሊጎበኙ የሚገቡ በብሔራዊ ፓርክ ውስጥ የሚገኙ ሐይቆች ናቸው፡፡
በብሔራዊ ፓርክ ውስጥ ከሚገኙ ሐይቆች በአንዱ ብርቅዬ ወርቃማ የዓሳ ዝርያ የተገኘ ሲሆን በዓለም ሊቃውንት እውቅና አግኝቶ በሳይንሳዊ ስሙ ጋራ ጨበራ በመባልም ይጠራል፡፡
ሌላኛው ከብሔራዊ ፓርኩ ገፀበረከቶች መካከል ለአብነት ፏፏቴዎች፣ ፍልውሃዎችና የማዕድን ውሃዎች የሚጠቀሱ ናቸው።
ብሔራዊ ፓርኩ በአሁኑ ሰዓት በገበታ ለሀገር ኮይሻ ፕሮጀክት እየለማ የሚገኝ ሲሆን ቱሪስቶች ብዙም ሳይጉላሉና ሳይለፉ በቀላሉ ጎብኝተው እንድመለሱ ምቹ ሁኔታ ከመፍጠሩም ባለፈ ፓርኩን በተገቢው ሁኔታ ለማስተዳደርና የዱር እንስሳትን በቅርበት ለመከታተልና ለመጠበቅ ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል፡፡
ይህ ብሔራዊ ፓርክ በኮንታ እና በዳውሮ ህዝብ ፊላጎት እንደተቋቋመ ሁሉ በጥበቃ ሂደት ላይም ህዝቡ ከፍተኛ ዋጋ በመክፈል ብሔራዊ ፓርኩን ከተለያዩ ጥፋቶች በመታደግ መልካም ዝና እንድኖረው አድርገውታል።
ምንጭ ፦ የክልሉ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ
- ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያና የደኅንነት ስጋት – አቅራቢ፣ ፈላጊ፣ ነጋዴ፣ ደላላ ተገናኙና መደበኛ ገበያ ሆነ!በፖለቲካም ሆነ በአካባቢያዊ አጀንዳ ነፍጥ ያነገቡ እና ጦርነትን አማራጭ አድርገው የሚንቀሳቀሱ ኢ -መደበኛ አደረጃጀቶች ሁሉ የጦር መሳሪያ ፍላጎት ይኖራቸዋል፡፡ የጦር መሳሪያ… Read more: ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያና የደኅንነት ስጋት – አቅራቢ፣ ፈላጊ፣ ነጋዴ፣ ደላላ ተገናኙና መደበኛ ገበያ ሆነ!
- ምን ያክል ተዘጋጅተናል? ጥድፊያ አገር አልባ ለመሆን !! ህጻናቱ ምን አጠፉ?ያለፈውን ግማሽ ምዕተ ዓመት የኢትዮጵያ ፖለቲካ እና ሥነ መንግሥት ታሪክ በጥሞና የተከታተለ ኢትዮጵያዊ የግዛት አንድነቷን እና የፖለቲካ ነጻነቷን በአንጻሩ ጠብቃ የኖረች… Read more: ምን ያክል ተዘጋጅተናል? ጥድፊያ አገር አልባ ለመሆን !! ህጻናቱ ምን አጠፉ?
- የደም ግፊት በመለካትና ክትትል በማድረግ የስትሮክ ተጋላጭነትን መቀነስአንድ ሰው የደም ግፊት መጠኑ ከፍተኛ ከሆነ እና በጊዜው ሕክምና ካላደረገ ለከፍተኛ የልብ በሽታና በደም ዝውውር ማነስ ምክንያት ለሚከሰት የአዕምሮ ሥራ… Read more: የደም ግፊት በመለካትና ክትትል በማድረግ የስትሮክ ተጋላጭነትን መቀነስ
- የስኳር ህመም አይነቶች እና ምልክቶችየስኳር ህመም በደም ውስጥ የስኳር መጠን ከሚገባው በላይ ሆኖ በሚገኝበት ሰዓት የሚከሰት ተላላፊ ያልሆነ የህመም አይነት ነው። በዋናነት አራት የስኳር ህመም… Read more: የስኳር ህመም አይነቶች እና ምልክቶች
- ማንኮራፋትና ትዳርን እስከ ማፍረስ የሚያደርሰው መዘዙ ? ማንኮራፋት መፍትሄ አለው?የማንኮራፍት መዘዙ እንቅልፍ ማሳጣት ብቻ አይደለም። ማንኮራፋት ከሚያንኮራፉት ሰዎች ጎን በሚተኙ ሰዎች አካላዊ እና አእምሮ ጤና ላይ ጉዳት ያስከትላል። ትዳርንም ሊያፈርስ… Read more: ማንኮራፋትና ትዳርን እስከ ማፍረስ የሚያደርሰው መዘዙ ? ማንኮራፋት መፍትሄ አለው?