የሰላ ትችት በመሰንዘር የሚታውቀት ስዩም ተሾመና ሙክታሮቪች ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ሰዎች ታፍነው ድብደባ እንደተፈጸማቸው ተሰማ።

ስዩምና ሙክታሮቪች በትላንትናው እለት፣ ከምሽቱ አንድ ሰአት ግድም ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች የግድያ ሙከራ እንደተፈፀመባቸው የገለጹት የአይን እምኞች እንደሆኑ አርአያ ተስፋ ማርያም ነው።

አንድ አምቡላንስ እነስዩም የተሳፈሩበትን መኪና መንገድ ዘግቶ ካስቆማቸው በሁዋላ አንዱ ሬንጀር ጄኬት የለበሰ እነስዩምን ከመኪናቸው በሃይል ያስወርዳቸዋል። ካስወረዷቸው በኋላ በአምቡላንሱ ይጭናቸዋል። የአደጋ ጥሪ እያሰማ በፍጥነት ወደ ጎሮ አቅጣጫ ያመራል። እማኞቹ እንዳሉትና አርአያ እነሱን ጠቅሶ እንዳለው።

ወደ ጎሮ አቅጣጫ ደእወል እያስጮኸ የከነፈው አውቶሞቢል የት እንዳስገባቸው በመረጃው አልተካተተም። ይሁንና ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ይገልጻል።

የእጅ ስልካቸውንና የያዟቸውን ዶክመንቶች እንደወሰዱባቸው ተጠቁሟል። በድብደባ ስለተጎዱ ወደ ሆስፒታል ተወስደው በህክምና ላይ ርድታ ላይ እንደሚገኙ አርአያ ጽፏል። የት ሆስፒታል እንዳሉና የጉዳታቸው መተን ምን ያህል እንደሆነ ግን አልተሰማም።

ዜናው ከሃሳብ ነጻናት ጋር በተያያዘ እጅግ አሳሳቢና አስደንጋጭ ሲሆን ችግር እንኳን ቢኖር በመወያየት ማረም እየተቻለ፣ ጥፋትም ካለ በህግ መጠየቅ እየተቻለ፣ እንዲህ ዓይነት አሳፋሪ ድርጊት መፈጸሙ በነጻ ሃሳብን የመግለጽ ነጻነት ላይ የተቃጣ ዘመቻ ተደርጎ የሚወሰድ ነው።

ደረሰ የተባለውን አደጋ አስመልክቶ ከመንግስት ወይም ከግህ ተቋማት እስካሁን የተባለ ነገር የለም።

Leave a Reply