ባለፉት ሰባት ቀናት ከመጋቢት 17 እስከ መጋቢት 23 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ 14 ሺህ 437 ግለሰቦች በኮቪድ19 መያዛቸው የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት አስታወቀ፡፡
የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 100 ግለሰቦች ውስጥ 25ቱ ቫይረሱ እንደተገኘባቸውም ኢንስቲቲዩቱ ገልጿል፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥም 149 ግለሰቦች ህይወታቸውን አጥተዋልም ነው ያለው፡፡
በትናንትናው እለት ለ8 ሺህ 294 ግለሰቦች የላቦራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ 2 ሺህ 372 ሰዎች ኮቪድ-19 ሲገኝባቸው ይህም ከ100 ሰዎች 29ኙ ላይ ቫይረሱ እንደተገኘ ያሳያል ነው ያለው፡፡ አሁን ላይም የቫይረሱ ስርጭት በመላ ሃገሪቱ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩንም ነው ኢንስቲቲዩቱ የገለጸው፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞም ህብረተሰቡም ሆነ መንግስታዊ አካላት የወጡ መመሪያዎችን በመተግበርና በሃላፊነት ስሜት በመንቀሳቀስ የቫይረሱን ስርጭት እንዲከላከሉም ጥሪ አቅርቧል፡፡
በሌላ ዜና የኢትዮጵያ መንግስት በኤግዚም ባንክ በኩል ባደረገው የ30 ሚሊየን ዶላር የረጅም ጊዜ ቀላል የብድር ስምምነት የተገዙ የህክምና መሳሪያዎችን መረከቡን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ እንዳስታወቁት የህክምና መሳሪያዎቹ የኮቪድ19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እየተደረገ ያለውን ጥረት እንዲያግዙ የኢትዮጵያ መንግስት ከኮሪያ መንግስት በኤግዚም ባንክ በኩል ባደረገው የ30 ሚሊየን ዶላር የረጅም ጊዜ ቀላል የብድር ስምምነት የተገዙ ናቸው፡፡የህክምና መሳሪያዎቹም የኮቪድ19 መመርመሪያ መሳሪያ፣ የመተንፈሻ ድጋፍ ሰጪ
መሳሪያዎችን ጨምሮ የተለያዩ የጽኑ ህሙማን ህክምና መስጫ ቁሳቁሶች ናቸው ተብሏል፡፡ለዚህም ሚኒስትሯ የኮሪያ መንግስት የኮቪድ ወረሽኝን በመዋጋት ሂደት ከኢትዮጵያ ጎን በመሆን እያደረገ ለሚገኘው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ via FBC
- ከአምስት አመት በፊት በእንጀራ እናቷ ተገደለች የተባለችው ግለሰብ በህይወት ተገኘች
by topzena1
በሰሜን ሸዋ ዞን ሞጃና ወደራ ወረዳ ከአምስት ዓመት በፊት በእንጀራ እናቷ ተገደለች የተባለችው ግለሰብ በህይወት መገኘቷ ታወቀ። ግለሰቧ መሞቷ በሀሰተኛ ምስክሮች ተረጋግጦ የእንጀራ እናቷ የ20 ዓመት እስር ቅጣት ተጥሎባቸው ነበር። ሞታለች የተባለችው ግለሰብ እና ከሳሽ የነበሩት በቁጥጥር ስር ውለዋል። የዞኑ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ኮማንደር ደበበ […]
- “ሌሎች ህወሃቶችና ኦነግ ሸኔ ጨረሱን” የአጣዬ ነዋሪዎች ” ጅብ የሚነክሰው አናክሶ ነው ” የአቶ ምግባሩ ትንቢት
by topzena1
በክፉዎች ሴራ ቤተሰቦቻቸው፣ የአማራ ክልል፣ ኢትዮጵያና ወዳጆቻቸው ያጡዋቸው አቶ ምግባሩ ከበደና ባልደረቦቻቸው የሚረሱ እንዳልሆኑ በሁሉም ዘንድ እምነት አለ። ዶ/ር አምባቸው መኮንን፣ የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የአቶ ምግባሩ ከበደና የርዕሰ መስተዳደሩ አማካሪ የአቶ እዘዝ ዋሴ በጁን 25 ቀን 2019 የቀብር ስነስርዓታቸው የተከናወነው በክፉዎች ሴራ መሆኑንን መላው የአማራ ሕዝብ ጠንቅቆ […]
- የአማራ ሕዝብ ከፖለቲካ ነጋዴዎች ራሱን አግልሎ በአንድነት ይቁም!! ሰሜን ሸዋ፣ ጭልጋ፣ ፍኖተ ሰላም አማራ እየተወጋ ነው
by topzena1
የክልሉ የሰላምና ሕዝብ ደኀንነት ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ሲሳይ ዳምጤ ሲናገሩ እንደተሰማው በሰሜን ሸዋ ያለው ሁኔታ የከፋ ነው። አማራ አንድ ሆኖ መነሳት አለበት። የአካባቢውን አመራሮች የጠቀሱ የሌሎች ሚዲያዎች እንዳሉት ወራሪው ሃይል እጅግ ብዙ ነው። አሁን ስፍራው ላይ ያለው ሊቋቋመው አይችልም። አቶ ሲሳይ ” አማራ በአንድ ይቁም” ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። […]
- “ሁሉንም ያማከለ ዴሞክራሲያዊ ስረዓተ መንግስት ካልተመሰረተ ወቅታዊና ረጅም ጊዜ ያስቆጠሩ ችግሮች ለመፍታት አስቸጋሪ ነው”
by topzena1
በኢትዮጵያ እውነተኛ ሁሉንም ያማከለ ዴሞክራሲያሲዊ ስረዓተ መንግስት ካልተመሰረተ አሁን ያሉትንና ረጅም ጊዜ ያስቆጠሩ የአገሪቱን ችግሮች ለመፍታት ከባድ ሊሆን እንደሚችል በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ምክክር ያደረጉ ምሁራን ገለጹ። ‘ኢትዮጵያዊነት’ በተሰኘ የሲቪክ ማኅበር አዘጋጅነት ምዕራባውያን በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያያዙትን የተሳሳተ አቋም በተመለከተ በአለም አቀፍ ደረጃ የዌቢናር ውይይት እየተካሄደ ነው። በውይይቱ […]
Like this:
Like Loading...
Related