“ሻምቡ፣ ወለንጪቲ ዙሪያ፣ ፊንጫና አንገር ጉቲን ሂዱና ህዝብ አነጋግሩ፣ ቢያንስ ሃምሳ ከመቶ ወደ እውነት ትደርሳላችሁ”

“ሲጀመር ራሱን የፖለቲካ ተቋም አድርጎ ክልልንም ይሁን አገርን ለመምራት የሚዘጋጅ ሃይል ራሱን ስልጣን ላይ ካለው አካል የተሻለ አድርጎ ያቀርባል እንጂ ዜጎችን አያፍንም፣ አይገልም፣ አያግትም፣ አይፈናቅልም፣ መከራ ውስጥ አይከትም” የሚሉት ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁና በኢትዮጵያ ፖለቲካ አውድ በሚሆነው ሁሉ ያዘኑ የኦፌኮ አባል ናቸው።

ስለድርጅታቸውም ሆነ ስለግል ፖለቲካ እምነታቸው ምንም መናገር እንደማይፈልጉ ገልጸው ለአዲስ አበባ ተባባሪያችን “”ሻምቡ፣ ወለንጪቲ ዙሪያ፣ ፊንጫና አንገር ጉቲን ሂዱና ህዝብ አነጋግሩ፣ ቢያንስ ሃምሳ ከመቶ ወደ እውነት ትደርሳላችሁ” ሲሉ ለሚዲያዎች አቅጣጫ አሳይተዋል። ይህን ሲሉ ግን መረጃው እኒመጣጠን እንጂ ማንንም ለመከለል ወይም ለማሳጣት እንዳልሆነ አመልክተዋል።

“ቢያንስ” ሲሉ እኚሁ ሰው እንዳሉት ” ቢያንስ የተጠቀሱት አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች ሰው ናቸውና ሚዲያው ፖለቲከኞቹን ወደ ጎን ትቶ ያነጋግራቸው፤ ህዝብ ይናገር፤ ሚዲያ የህዝብ መናገሪያ እንጂ አቋም የያዙ አጋፋሪዎች ሃያ አራት ሰዓት የሚለፈለፉበት አውድ አይደለም” ይህን ለማለት ያነሳሳቸው ሚዲያው በተጠቀሱት አካባቢዎች እየተፈጸመ ያለውን ክፉ ድርጊት በስማ በለው፣ በፖለቲካ ትርፍና ዕቅድ፣ በግልና በተጠና የሌሎች ዓላማ በተቃኘ መልኩ የሚቀርበው መረጃ ስለሰለቻቸው ነው።

“በግል ወጥቼ የማውቀውን ብናገር ኦሮሞ ስለሆንኩ ከትችት አልድንም፣ በኦሮሚያ በኩልም ተቃዋሚ ፓርቲ ውስጥ ስላለሁ ከፓርቲዬና ከግል ፍላጎቴ የምናገረው ተደርጎ ይወሰዳል” ያሉት እኚሁ የኦፌኮ አመራር ” ለምሳሌ ፊንጫ፣ ሻምቡና አካባቢው ላይ ማን እንደነበረ፣ ማን ዝርፊያ እንደፈጸመ፣ ስኳር ፍራብሪካውን ሲወሩ እነማን በጋር ፈጸሙት፣ እነማን ነዋሪዎችን እንደገደሉ፣ አሁንም ማን እዛ አካባቢ ጫካ ጫካውን እንዳለ ሚዲያዎች ሂዱና ህዝቡን ጠይቁና ዘግቡ” የሚል ጥሪ አስተላልፈዋል። በየ ቤተክርስቲያኑ ምን ሲፈጸም እንደነበር፣ አሁንስ ምን እየሆነ ነው? የሚለውን መዕመኑን በመጠየቅ ሃቁን ማስተላለፍ የወቅቱ ግዴታ እንደሆነ ይናገራሉ።

“አንገር ጉቲን ሙሉውን ምን ሲደረግ እንደነበር፣ ማን ይፈጽመው እንደነበር፣ ህዝቡን እንዴት ይዘርፉትና ይቀሙት እንደነበር፣ ከስሚ ስሚ ይልቅ አርሶ አደሩ እንዲናገር፣ ምስክርነቱን እንዲሰጥ ማድረግ ወደ ሚዛናዊ ድምዳሜ ያመጣሎ” ሲሉም ቦታ ጠቅሰው ተናግረዋል። ማንም ይፈጽመው ማን ንጹሃን ላይ የሚፈጸም ወንጀል ተቀባይነት እንደሌለው ባምስታወቅ፣ ሃቁን በመረጃ ይፋ ማድረግ ደግሞ ለፍትህ ውሳኔ እንደሚጠቅም አስታውቀዋል።

See also  ከአሸባሪው ትህነግ ተልዕኮ ተቀብለው አዲስ አበባ የመሸጉ የሽብር ቡድን አባላት ተያዙ ሁለቱ ወዲያው ተገደሉ

“እገታ፣ ስርቆት፣ አፈና የፖለቲካ ድረጅት ባህሪ አይደለም። ምንም ተቃዋሚ ብሆን በየትኛውም መስፈርት አገር የሚመራ ፓርቲ ንጹሃንን እያገተ በድርድር ገንዘብ አይቀበልም” ያሉት የኦፌኮ አመራር በተመሳሳይ ስልጣን ለመያዝም የሚነቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶችም ህዝብን እያሰቃዩና እያገቱ በድርድር ገንዘብ ሊቀበሉ እንደማይችሉ በአመክንዮ ያስረዳሉ።

“ሃቁ ይህ ከሆነ” አሉ ፖለቲከኛው ” ሃቁ ይህ ከሆነ ማን ነው ይህን የሚፈጽመው? ብሎ መጠየቅና መመርመር እንጂ የጅምላ ጩኸትና ፍረጃ ጉዳት እንጂ ጥቅም ያስገኝም” ባይ ናቸው።

ከጅምላ የመርዶና የለቅሶ፣ የምሬትና የሰቆቃ ሪፖርት ይልቅ የሚሰማውን ዜና ተከትሎ ለማጥራትና ትክክለኛ የሆነውን መረጃ ለህዝብ ለመስጠት የሚተጉ ሚዲያዎች አለመኖራቸው ትልቅ ችግር እንደሆነ ይናገራሉ። በተጠቀሱት አካባቢዎችም ሆነ በሌሎች አካባቢዎች ሚዲያዎች ግብተው ለመስራት ስጋት አለባቸው በሚል ለተጠየቁት ” አዎ ስጋት አለ። መከላከያ ሽፋን ሰጥቶ የግል ሚዲያዎች ወደ ተጠቀሱት አካባቢዎች ገብተው ህዝብን አነጋገረው የሰሙትንና ያዩትን እንዲዘግቡ ቢደረግ ታሪኩ ሌላ እንደሚሆን ጥርጥር የለውም” ሲሉ መንግስት በጉዳዩ ላይ ተባባሪ ሆኖ ይህን አውድ እንዲያመቻች ይጠይቃሉ።

ከዚህ ቀደም ባሰራጨነው ዜና “ኦሮሚያ ውስጥ የሚሆነው ሁሉ በመናበብ የሚሰራ ላለመሆኑ ምን ማስረጃ ማቅረብ ትችላለህ” ሲሉ አንድ ጉምቱ ፖለቲከኛ የተናገሩትን ማስነበባችን ይታወሳል።

ኦነግም ይባል ኦነግ ሸኔ በዚህ ጉዳይ ላይ ስማቸው በገሃድ የሚነሳ፣ በግልጽ ተጠያቂ የሚደረጉ፣ ለወንጀሉ ግንባር የሆኑ ድርጅት እነድመሆኑ በሚከሰስበት ጉዳይ ላይ በይፋ ሲሞገት አይታይም። ለኦነግ አመራሮች ቅርብ የሆኑ ሚዲያዎች ቢቢሲና ቪኦኤን ጨምሮ ከተራ የማስተባበል ዜና ባለፈ በሚከሰሱበት ልክ ሲሞግቱዋቸው አይታይም። በዚህም የተነሳ ቀደም ሲል ያነጋገርናቸው ፖለቲከኛ ቢቢሲና ቪኦኤን የድርጅቶች የማስተባበያ ልሳን አድርገው እንደሚቆጥሯቸው መግለጻቸው ይታወሳል።

በየቀበሌው፣ በየሰፈሩ ዱካ እየቀያየሩ ንጽሃንን የሚዘርፉ፣ የሚያገቱ፣ የሚያፍኑና የሚገድሉ አካላት አንዳንዴም ፖለቲካዊ ተልዕኮ አላቸው ብሎ መቀበል እንደማይቻል የሚገልጹ ” ህዝብን ምሬት ውስጥ ለመክተት የተደራጁ ተከፋይ ገዳዮችና አፋኞች ናቸው፣ አለያም የራሳቸውን አደረጃጀት ፈጥረው አፈናና እገታን ስራ ያደረጉ የማፍያ ቁጥቋጦ ናቸው” ይላሉ።

See also  ቻይና ከ1600 በላይ የኢትዮጵያ ምርቶች ከቀረጥ ነጻ ወደ አገሯ እንዲገቡ ፈቀደች

ኢትዮጵያን እያመሳት ያለው የ”ገፊና ጎታች ሤራ” ሲገለጥ

ማንም ይሙት የሚገደለው ሁሉ አማራ፣ ገዳዩ ደግሞ ሸኔ ብቻ እንዲባል ለምን ተፈለገ? የሸኔ የፖለቲካ ፕሮግራምና ዓላማ ምንድነው? ሸኔን በፋይናንስ የሚደጉመው ማነው? ሸኔ ወለጋ ላይ በተለይ ያተኮረው ለምንድነው? ሸኔ ሲገድል የአማራ ተቆርቋሪዎች በምን ግንኙነትና ፍጥነት እየተቀበሉ


ይህ መስል ያጣ፣ ህዝብን እያማረረና ወደ ቁጣ ውስጥ እየከተተ ያለ ጉዳይ ለየትኛውም የህብረተሰብ ክፍል የሚጠቅም ባለመሆኑ ከወዲሁ በርብርብ መፍትሄ ሊበጅለት እንደሚገባ ዜጎች እየጠየቁ ነው። በውይይትና በንግግር የሚፈታውን በዚሁ አግባብ ማስተናገድ፣ በሌላ አግባብ መፍትሄ የሚፈለግለትን ጉዳይም ሃቁን ለህዝብ ይፋ አድርጎ እንዲፈታ ማድረግ ለነገ የማይባል እንደሆነ አሁንም ስጋት የገባቸው እየገለጹ ነው። ከምንም በላይ ግን ሁሉንም ጉዳይ፣ በግለሰብ የተፈጸመን ተግባር ሁሉ መንግስትን ለማቆሸሽ ተግባር መጠቀም መፍትሄ ስለማያመጣ በምስኪኖች ስቃይ ፖለቲካ የሚቆምሩም ራሳቸውን ከጸጸት ሊጠብቁ እንደሚገባ የሚመክሩ አሉ።

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ)፣ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) እንዲሁም ኦፌኮ በተለያዩ ጊዜያት መግለጫ በማውጣት ዜጎች ላይ የሚደርሰውን ግፍ ይቃወማሉ። የሚከሰሰው ኦነግ ራሱ ድርጊቱን ያወግዛል።

ጃዋር መሐመድ ታህሳስ ቀን 2022 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በወለጋ ዞኖች ውስጥ ባጋጠመው ግጭት ዋነኛ ተሳታፊዎች መንግሥት ‘ሸኔ’ እያለ የሚጠራው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና የአማራ ታጣቂዎች ናቸው በማለት ተጠያቂ አድርጎ ባወጣው ሪፖርት ላይ ለቢቢሲ አስተያየት ሲሰጥ ”  ተኩስ በማቆም ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ጋር ንግግር መጀመር አለበት፤ በተጨማሪም የፋኖ ሚሊሻዎችን ከኦሮሚያ አስወጥቶ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው መመለስ አለባቸው ፣ አጠቃላይ ብሔራዊ የሰላም ሂደት ብቸኛው መፍትሄ በመሆኑ ይህን ለማሳካት አቅዶ መተግበር ያስፈልጋል” ማለቱ ይታወሳል።

በገሃድ የጎጃም አካባቢ ፋኖ አማራ ክልል ዘልቆ መግባቱ በየትኛውም የተቃዋሚ ሚዲያዎችም ሆነ ፓርቲዎች በገሃድ ሲወገዝ አይሰማም። እስክንድር ነጋ የብሄር ፖለቲካ አቀንቃኝ እንደሆነ ሲጠየቅ ለበርካታ ዓመታት ሲያስተባብል ቢቆይም፣ አሁን በገሃድ የአማራ ህዝባዊ ሃይል ግንባር የአገር ውስጥ አመራር መሆኑ ሲጠቅስ የውጭ አገር የግንባሩ መሪ ሻለቃ ዳዊት እንደሆኑ ማስታወቁ ይታወሳል።

See also  እስራኤል ያነደደችው ኤፒ ለቅጥፈቱ ይቅርታ አልጠየቀም - ምርጫ ተራዘመ፤ ለምን?

የቀድሞ የእርዳታ ማስተባበሪ ኮሚሽነር የነበሩትና ከርሃብተኞች ገንዘብ ዘርፈው አገር እንደከዱ ቢቢሲና ኤፒ በሰነድ አስደግፈው በወቅቱ ዜና የሰሩባቸው ሻለቃ ዳዊት፣ “ድፍን ወለጋ የአማራ ነው” ሲሉ አስቀድመው መናገራቸው የሚታወስ ነው።

ሰፊ ቁጥር ያለው አማርኛ ተናጋሪ በሁሉም አገሪቱ ተሰራጭቶ ለፍቶና ላቡን አንጠፍጥፎ ሃብት በማፍራት እንደሚኖር የሚገልጹ፣ የአንዳንድ ፖለቲከኞች፣ አክቲቪስት ነን ባዬችና ለአማራ እንደሚቆረቆሩ የሚናገሩ የሚራምዱት አቋም ሰላማዊውን ህዝብ እንዳይጎዳው ይሰጋሉ። በጥቅልም ዓላማው ኦሮሞና አማራን ማጫረስ እንደሚመስላቸው ይናገራሉ። በጋህድ በተቃውሞ ስም በጅምላ ህዝብን መፈረጅ፣ ማስቀይም፣ ስሜት ውስጥ መክተት መመረጡ የአገሪቱን ፖለቲካ ጡዘት እየጨመረው እንደሆነ በርካቶች ይናገራሉ።

መንግስትን በሰለጠነና በተጠና ፖለቲካዊ ትግል መገዳደልና ማበሻቀጥ እየተቻለ፣ በዘር፣ በሃይማኖትና በጎሳ ላይ ተቸክሎ ልዩነትን ማጋም ጉዳቱ ለጸጸት እንኳን የማይመች እንደሆነ የሚገልጹ ” ህዝብ ትከሻው ብርቱ፣ አብሮነቱ ጠንካራ፣ እምነቱ ጽኑ መሆኑ ረዳ እንጂ እንደሚታሰብው ቢሆን ኖሮ ይህን ጊዜ በጠፋን” ሲሉ ችግሩን ሁሉ ተቋቁሞ በስሜት ለማይነዳው ህዝብ ምስጋናቸውን ያቀርባሉ።

Leave a Reply