በመቐለ ከተማ የሚገኙ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራ ዛሬ መጀመራቸውን በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የከተማው ትምህርት ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

የጽህፈት ቤቱ ተወካይ ወይዘሪት ገነት መብራቱ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የመማር ማስተማር ሥራው የተጀመረው በከተማዋ በሚገኙ 32 የመንግስት እና ከ30 በላይ የግል ትምህርት ቤቶች ነው።

ትምህርት ቤቶቹ የመማር ማስተማር ሥራውን የጀመሩት ቀደም ሲል ከመምህራን፣ ከወላጆችና በየደረጃው ከሚገኙ የመንግስት አመራት አካላት ጋር መግባባት ላይ በመደረሱ እንደሆነ ገልጸዋል።

የትምህርት ቁሳቁስ ችግር ላለባቸው ተማሪዎች ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን አመልክተው ጉዳት የደረሰባቸው ትምህርት ቤቶችን የማስተካከልና በቁሳቁስ የማሟላት ሥራ መከናወኑን አስታውቀዋል።

በመቐለ በሚገኙ ሰባት ክፍለ ከተሞች ውስጥ መደበኛ ትምህርቱ ሲጀመር ሁሉም መምህራን መገኘታቸውን የገለጹት ወይዘሪት ገነት፤ ተማሪዎችም እየገቡ መሆኑን መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

One thought on “በመቐለ ከተማ መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራ ተጀመረ

Leave a Reply

Previous post ቦሌ ከዓመት በላይ ጸሃይና ምግብ ተከልክላ፣ አየተቆለፈባት፣አየተበደበች የኖረችው አህት ነጻ ወጣች
Next post ‹‹ሾልኮ ወጣ›› እጅግ አሳሳቢው የሐሰተኛ መረጃ ስርጭት
%d bloggers like this: