ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ ዓለም ኢትዮጵያ ላይ የያዘውን ያልተገባና ሚዛናዊነት የጎደለው አቋሙን እንዲስተካከል፣ የውጭ አገር መንግስታት እያደረጉ ያሉትን ቅጥ ያጣ ጫናና ጣልቃ ገብነቶችን፣ በተጨማሪም ህፃናትን ለውትድርና እየተጠቀመ ባለው የህወሓት ቡድን ላይ ጫና እንዲደረግ የሚጠይቅ የትዊተር ዘመቻ አካሂደዋል። በተለይም አንቶኒ ብሊንከን ” ነጭ ወያኔ” በሚል ክፉኛ ተንኳሰዋል። ሊንዳ ቶማስም በተመሳሳይ ተወግዘዋል።
በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የትዊተር ዘመቻው በተለይም አሸባሪው ሕወሓት እያደረገ ያለውን ትንኮሳ እና ህጻናትን ለውትድርና መጠቀሙ የህጻናት መብቶችን እና ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎችን የሚጣረስ በመሆኑ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲያወግዘው የሚጠይቅ ነው። ይህን ከፍተኛ ወንጀል እንደ መልካም አድረገው የዓለም አቀፍ ሚዲያዎች የህጻናቱን ምስል አስደግፈው መዘገባቸው የሚታወስ ነው።
ይህ አሸባሪ ቡድን ” አልደገፋችሁኝም” በሚል በርካታ ንጹሃንን ማረዱ፣ መረሸኑና አስሮ እያሰቃየ እንደሚገኝ ከበቂ በላይ መረጃ ቢኖርም እኚሁ የተንሸዋረረ አቋም የያዙት አገራትና ዓለም ዓቀፍ ተቋማት ዝምታን መምረጣቸው እጅግ አነጋጋሪ ሆኗል። በዚህ ዘመቻ ይህ ጉዳይ እጅግ ጎልቶ የወጣ ሆኗል። ትህንግ እየፈጸመ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰትና ትንኮሳ በአስቸኳይ ያቆም ዘንድ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጫና እንዲያሳድርም በዘመቻው ተጠይቋል። ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችም በትግራይ ስላለው ግጭት እያቀረቡት ያለው መረጃ በእውነታ ላይ ያልተመሰረተ መሆኑንም የዘመቻው ተሳታፊዎች አንስተዋል፡፡
” ወዳጅ” እያለች የምትጠራው አሜሪካም በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የያዘችው አቋምና በውስጥ ጉዳይ ላይ እያደረገች ያለው ጣልቃ ገብነት አግባብነት የሌለውና አሸባሪውን ቡድን የሚደግፍ ነው በሚል የዘመቻው ተሳታፊዎች ተቃውሟቸውን ገልጸዋል፡፡ አሜሪካ በዓለም ላይ አሸባሪ ከሚባሉ አካላት ጋር ግንኙነት እንደማታደርግ ሁሉ ከትህነግ አሸባሪ ቡድን ጋር በቀጥታም ሆን በተዘዋዋሪ ገጥማ ኢትዮጵያ ላይ እያደረገች ያለው ዘመቻ በእጅጉ ተወግዟል።
በተለይም አይሁዳዊው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አንቶኒ ብሊንከን በኢትዮጵያ ላይ የያዙት አቋም የለየለት ሚዛን የሳተ፣ አንዳንዶች እንደሚሉት የአሸባሪው ቡድን አባል እስከመምሰል የደረሰ፣ ስራቸውን ሁሉ ትተው በወያኔ ጉዳይ የተጠመዱ ሆነው መታየታቸውን በቃላት ብቻ ሳይሆን በምስልም አስደግፈው የዘመቻው ተሳታፊዎች አኮስ ሰዋቸዋል። ምዕራባውያን አሸባሪው ህወሓት ከፊት ለጦርነት ያሰለፋቸው ህፃናት ጉዳይ ግድ ሳይሰጣቸው ባለየ ማለፋቸው ተገቢነት እንደሌለውም በስፋት መጠቀሱን ተከትሎ አንዳን አፍሪካ ተኮር ሚዲያዎች ድርጊቱን በማውገዝ ኮንነው ጽፈዋል።
ትግራይንና የትግራይን ሕዝብ ሲጠብቅ በኖረው በመከላያ ሰራዊትና በማይካድራ ንጹሃን ላይ ትህነግ የፈፀመውን ዘግናኝ ጭፍጨፋን በማስታወስ ምዕራባውያን ለዚህ የከፋና በዓለም ዓቀፍ ተቋማት ሳይቀር ገሃድ ለሆነ ወንጀል ጆሮ ዳባ ማለታቸው የዘመቻው ሌላው አበይት የመቃወሚያና አሜሪካንን ጨምሮ ዓለም በጥቅሉ ሚዛኗን እንደሳተች ለማሳየት የቀረበ ጉዳይ ነበር።
አሜሪካን ጨምሮ ምዕራባውያን ሃገራት የኢትዮጵያን ጉዳይ በፍትሃዊነት እንዲመረመሩ፣ ሉዓላዊነቷን እንዲያከብሩና ከመቶ አስራ አምስት ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ያላትን አገር ለማፍረስ የሚያደርጉት መረባረብ እንዲያቆሙ በዘመቻው ተጠይቋል።
- የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ዳግም ዝርፊያ እያፈጸሙ ነው፤ የተማሪዎች መጽሃትን “የአማራ ክልል ናቸው እየሉ ቀደዋል”በአላማጣ ከተማ በተለየ መልኩ የትግራይ ክልል ታጣቂዎች በከተማዋ ውስጥ እንደሚንቀሳቀሱ ነዋሪዎች መመስከራቸውን ቢቢሲ አስታወቀ። ይህ የተገለጸው ከአለማጣ እና አካባቢው… Read more: የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ዳግም ዝርፊያ እያፈጸሙ ነው፤ የተማሪዎች መጽሃትን “የአማራ ክልል ናቸው እየሉ ቀደዋል”
- በዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ችግኝ ልትተክል ነውለዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር 6 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል ዕቅድ መያዙንna ለዚህም ተግባራዊነት ከሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊየን በላይ… Read more: በዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ችግኝ ልትተክል ነው
- አፍሪካ ህብረት ” የውጭ ምንዛሪ ሒሳቡን ወደ ሌላ ሀገር ሊያዘዋውር ነው” የሚለው ዜና ሃሰት መሆኑን ህብረቱ አረጋግጠአፍሪካ ህብረት የውጭ ምንዛሬ አካውንቱን ወደ ሌላ አገር እንደሚያዘዋውር ተጠቅሶ በህብረቱ ስም የወጣው ዜና ሃሰት፣ ሆን ተብሎ የተቀነባበረ መሆኑን… Read more: አፍሪካ ህብረት ” የውጭ ምንዛሪ ሒሳቡን ወደ ሌላ ሀገር ሊያዘዋውር ነው” የሚለው ዜና ሃሰት መሆኑን ህብረቱ አረጋግጠ
- አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎችባንኩ የክፍያ ሰነድ ቀረበለት። ማጣሪያ ጥያቄ ለህብረቱ አቀረበ። ሃሰት ሆኖ ተገኘና ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን ያዘ። ጉዳዩ ወደ ህግ አመራ። አሁን… Read more: አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎች
- የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል 300 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ዕዳ አለብኝ አለ፤ ዕዳውና የክፍያው ጫና እንደከበደውም አስታውቋልየኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከንግድ ባንክ 300 ቢሊዮን ብር ዕዳ እንዳለበት ተገለጸ። የዕዳ ጫናውን ለማቃለል የባንክ ወልዱም ጭምር ተፅእኖ እያሳደረ… Read more: የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል 300 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ዕዳ አለብኝ አለ፤ ዕዳውና የክፍያው ጫና እንደከበደውም አስታውቋል