ነሀሴ 29 ቀን 2013
በሰሜን ወሎ በኩል ሰርጎ የገባው ወራሪው የህውሃት አሸባሪ ሃይል በጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን አፀፋዊ እርምጃ ተወሰደበት ፡፡
በዚህ ስምሪት 142 የሽብር ቡድኑ ታጣቂ ሃይል ሲደመሰስ 4 ስናይፕር ፣ 6 የሞርተር ቅንቡላ ፣ 1 ብሬን ፣18 የእጅ ቦምብ ፣ 15 ክላሽ ፣ 7 ሽህ የብሬን ጥይት ፣ 5 ሽህ የክላሽ ጥይት ፣ 1 የመገናኛ ሬዲዬ (1187 አይኮም) ፣ 1 የዋይፋይ ሪሲቨር ፣ 6 የብሬን ሻንጣና 10 የነፍስ ወከፍ ወታደራዊ የወገብ ሻንጣ ከጠላት ሃይል ተማርኳል ።
ከግንባሩ አመራሮች መካከል የክ/ጦር ም/አዛዥ ለኦፕሬሽናል እንደተናገሩት ፣ ጠላት አሁን ላይ በሰራዊታችን እየደረሰበት ባለው ኪሳራና ባጋጠመው ሽንፈት የተስፋ መቁረጥ እንቅስቃሴዎችን ቢያደርግም ከገባበት መግደያ ወረዳ መውጣት እንደማይቻለው ገልፀው ፤ ወራሪውን ሃይል በገባበት አስቀርተን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለህዝባችን የድል ዜና እናሰማለን ብለዋል ።
በግዳጅ ቀጣናው የብርጌድ ዋና አዛዥ በበኩላቸው ፣ በጭፍን ሃገራዊ ጥላቻ ተነሳስቶ የማይሞከረውን መከላከያ ሰራዊት በመፃረር ህዝብን የተዳፈረው አሸባሪ የትህነግ ቡድን በፈፀመው ስህተት የእጁን እያገኘ ነው ሲሉ ተናግረዋል ።
ሰራዊታችን በተሰለፈበት የወሎ ግንባር በሰርጎ ገቡ ሽብርተኛ ቡድን ላይ እየወሰደ ያለው አሁናዊ እርምጃና በጠላት በኩል የተመለከትነው መፍረክረክ የፍፃሜውን መቃረብ የሚያመላክት ነው ያሉት ደግሞ በግንባሩ የብርጌድ ም/አዛዥ ለኦፕሬሽናል ናቸው።
ኤፍሬም አድማሱ
ፎቶግራፍ ታጠቅ ንጉሴ