ተከሳሽ (ለተጎጂው ሲባል ስሙ ያልተጠቀሰ) የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀፅ 631/1/ለ ስር የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ በጥቅምት እና ህዳር ወር 2011 ዓ.ም በተለያዩ ቀናት በአቃ/ቃ/ክ/ከተማ ወረዳ 09 ልዩ ቦታዉ ኮዬ ፈጬ ኮንዶሚኒየም ዉስጥ ዕድሜዉ 7 ዓመት የሆነዉን የራሱን ልጅ የግብረሰዶም ጥቃት ወንጀል የፈፀመበት በመሆኑ በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አቃቂ ቃሊቲ ምድብ ወንጀል ችሎት በአቃቤ ህግ ክስ ቀርቦባታል፡፡

ተከሳሽ በችሎት ቀርቦ የእምነት ክህደት ቃሉን ሲጠየቅ ድርጊቱን አልፈፀምኩም በማለት ክዶ በመከራከሩ የዓቃቤ ህግ የሰው እና የሰነድ ማስረጃ ቀርበው ተከሳሽ ወንጀሉን ስለመፈፀሙ እንደክስ አመሰራረቱ ያስረዱ በመሆኑ እንዲከላከል ችሎቱ ብይን ቢሰጥም ተከሳሽ ባቀረባቸዉ የሰነድና የሰዉ መከላከያ ማስረጃዎች መከላከል ባለመቻሉ ፍ/ቤቱ መዝገቡን መርምሮ የጥፋተኝነት ፍርድ ሰጥቶ ነበር ለመስከረም 14 ቀን 2013 ዓ.ም ቀጠሮ ይዞ መዝገቡ ያደረው፡፡ በዚህም መሰረት ፍርድ ቤቱ ከላይ በተገለጸው እለት በዋለው ችሎት ተከሳሽ በአስራ ስድስት (16) ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል፡፡

Attorney general FB

Leave a Reply