ለመዓዛ – ከጦር ግንባር የተላከ

እኔ ለሄደው ስርአት የማላዝን ለመጣው የማላሽቃብጥ የፓርቲ ወይም የግለሰብ ጠባቂ ሳልሆን የኢትዮጵያ ወታደር ነኝ ብዬ አምናለሁ❗ በዚህ ሂደት አካሌን ባጣ የህይወት መሰዋዕትነት ብከፍል ግድ የማይሰጠኝ የማምንበት ጦርነት በመሆኑ ብቻ ነው❗

Zerihun Nuri Abote ዘርይሁን ኑር አቦቴ ወታደር ከግዳጅ

ማስታወሻ – መዓዛ የምትባል የዓባይ ሚዲያ ቤተሰብ ሰፊው የአማራና የአፋር ሕዝብ እየተወረረ ባለበት፣ እየተጨፈጨፈና የመኖር ህልውናው እንዲያከትም ሂሳብ እናወራርዳለን ባሉ ሽፍቶች መከራ እያየ ባለበት፣ ኢትዮጵያን እንደ አገር ለማፍረስ ትንቅንቁ ባየለበት ወቅት ጦርነቱን የግለሰብ ስልጣን ጉዳይ ማድረጓ ሰፊ መነጋገሪያ ሆኗል። ዝግጅት ክፍሉ አቋማን የማይቃወም ቢሆንም ሃሳቧን ይጠየፈዋል። ዘሪሁን አቦቴ ከላይ በግዳጅ ምስልሉ ላይ ያለው ጀግና ወታደር የሚከተለውን ጽሁፍ በፌስ ቡክ አምዱ አስቀምጧል። እንዳለ አቅርበነዋል ያንብቡ !!

ባልተመቻቸ ቦታ በችኮላ የተፃፈ በመሆኑ ስተት ካለ በቅድሚያ ይቅርታ እጠይቃለሁ።


መከላኪያን የተቀላቀልኩት በአስራ ሰባት አመቴ በአቶ መለስ ዜናዊ አመራርነት ዘመን ነው።በወቅቱ በሶማሊያ በተካሄደው ጦርነት ተሳትፊያለሁ።የውትድርና ሂዎቴን የመጀመሪያ ሁለት አመታቶች ያሳለፍኩትም ዋና ከተማዋ መቋድሾን ጨምሮ በሌሎች የሀገሪቱ ግዛቶች ነው።

May be an image of text that says 'Meaza Mohammed ወሎ hoursfrom now አታጭበብሩ ጦርነቱ ኢትዮጵያን የመታደግ ሳይሆን የአብይ እህመድን ሰልጣን ለማስጠበቅ ነው። የማዝነው የአብይ አህመድን ስል ሰልጣን ለማስጠበቅ ለሚያልቀው አማራ ነው! የአማራ ኢሊቶች ማሰብ የምትጀምሩት ስንት አማራ ሲያልቅ ይሆን! Like Share'
ይህ መዓዛ መሐመድ የምትባል የዩቲዩብ ተናጋሪ በፌስ ቡክ ገጿ የለጠፈቸውና ትህነግ ባወጣው መግለጫ ከላይ በመሪ ቃልነት የተጠቀመበት ሃረግ ነው።
Mike on Twitter: "Much Respect !! Journalist Meaza Mohammed  https://t.co/rlBXoDCVeW… "
መዓዛ መሀመድ

በአቶ ሀይለማሪያም ዘመንም የሀገራችን የተለያዩ አከባቢዎች ባጋጠሙ የፀጥታ መጓደሎች በብዙ ቦታ በሚባል ደረጃ ተገኝቻለሁ።በቤኒሻንጉል በኦሮሚያ በጋንቤላ በአማራ ክልል ችግሮች በነበሩባቸው ቦታዎች ሁሉ ነበርኩ።በዚህ ሂደት እንደማንኛውም የሰራዊቱ አባላት አቅሜ የቻለውን ሁሉ ለሀገሬ ሰላም መጠበቅ አስተዋፆ አድርጊያለሁ ብዬ በፅኑ አምናለሁ።ወጣትነቴንም ሰላም በራቃቸሁ አከባቢዎች በመንከራተት እያሳለፍኩት ነው።ላለፉት አመታት ሀገሪቷን በመራው መንግስት ለማዕረግ ለውጥ የሚሰጡ ስልጠናዎችን ጨምሮ ከስድስት ላላነሰ ጊዜ በተለያየ ምክንያት ማሰልጠኛ ገብቼ ስልጠና ወስጃለሁ።በዚህ ሂደት ከልፋቱ ባሻገር በርካታ ነገሮችን አይቼ ታዝቢያለሁ ብዙ ልምዶችንም ወስጃለሁ።

May be an image of outdoors and text
ለአገራቸው ህልውና መከበር ከቤታቸው እንደወጡ ወደቤታቸው ላልተመለሱ! በሁሉም አቅጣጫ በየዳርድንበሩ አጥታቸውን የከሰከሱ ደማቸውን ላፈሰሱ ጀግኖች ክብር ይሁ!!

በባለፈው መንግስት አሁን ያለሁበት የማዕረግ ደረጃ ደርሻለሁ።ከማዕረግ እድገት ባለፈም በሶማሊያ በነበርኩበት ጊዜ ከደሞዝ በተጨማሪ በየወሩ ክፍያ በዶላር ተቀብያለሁ። በደቡብ ሱዳን ሰላም ማስከበር ተሳትፌ ለኔ ትልቅ የምለውን ገንዘብም አግኝቼ አውቃለሁ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ለውጡ ከመጣ ወዲህ ግን ምንም አይነት የማዕረግ እድገት አላገኘሁም።ለወታደራዊ ስልጣንም አልታጨሁም።ከገንዘብ ጥቅም አንፃርም ከወራዊ ደሞዜ በቀር አንድም ተጨማሪ ክፍያ የሚያስገኝ እድል አልደረሰኝም።ይልቁንም በዚህ ጊዜ በፊት ከነበሩ ችግሮች በከፋ መልኩ ሀገሪቷ በሚያጋጥማት ከበባድ ችግሮች ቦታ ሁሉ እየተገኘው በብዙ አስቸጋሪ ነገሮች መሀል አልፊያለሁ። ባጭሩ የስርአቱ ተጠቃሚ አይደለሁም!
ይህ ሆኖ ባለበት ሁኔታ ታዲያ እንዴት ሆኖ ነው “የአንድ ሰው ስልጣን ለማዳን ስትል ነው የምትዋጋው!” ልባል የምችለው? በፍፁም!!

እኔ ለሄደው ስርአት የማላዝን ለመጣው የማሽቃብጥ የፓርቲ ወይም የግለሰብ ጠባቂ ሳልሆን የኢትዮጵያ ወታደር ነኝ ብዬ አምናለሁ❗ በዚህ ሂደት አካሌን ባጣ የሂዎት መሰዋዕትነት ብከፍል ግድ የማይሰጠኝ የማምንበት ጦርነት በመሆኑ ብቻ ነው❗

ምክንያቱም እነዚህ መጥፋት ያለባቸው ፀረ አንድነት ሀይሎች ናቸው። ለዘመናት ሲከፋፉሉን አንዳችን በአንዳችን ለይ በማስነሳት ሲያጋድሉን የኖሩ በንፁሀን ደም እጃቸው የጨቀየ እርጉማን ናቸው። የሀገሪቷን የትምህርት ስርአት አበላሽተው ተተኪ ሙሁር ያሳጡን የደንቆሮ ስብስቦች መሆናቸውንም እረዳለሁ።

የሀገሪቷን ሀብት ሙልጭ አድርገው በመዝረፍ ለእራሳቸው እና ለቤተሰቦቻቸው የተመቻቸ ሂዎት በማዋል ሌላውን ዜጋ የበዪ ተመልካች ያደረጉ ስለመሆናቸወም የጠራራ ፀሀይ ሀቅ ነው።
ከምንም ነገር በላይ ዘረኝነትን ወልደው ተንከባክበው ለዚህ ያደረሱት እነሱ ስለመሆናቸው አስረጂ አልሻም።

“ጦርነቱ ኢትዮጵያን ለመታደግ ሳይሆን የአብይ አህመድን ስልጣን ለማስጠበቅ ነው።”የምትሉ! እግዚያብሄር በምህረቱ ይጎብኛችሁ ከማለት በቀር ሌላ ምን ማለት እችላለሁ?!❗

DONATE US – ቢረዱን አስፍተን ለመስራት አቅም ይፈጥሩልናል

About topzena1 2651 Articles
A journalist

Be the first to comment

Leave a Reply