ከሰሜን ሸዋ ዞን የህዝብ ሰላምና ደህንነት መምሪያ የተላለፈ መልዕክት

በትላንትናው እለት ማለትም በቀን 3/08/2014 ከሰአት በኋላ በሰሜን ሸዋ ዞን በሸዋሮቢት ከተማ አቅራቢያና በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን አዋሳኝ ወሰን ቁርቁር በተባለ አካባቢ በነበረ የግለሰቦች ግጭት ተከስቶ የነበረ የፀጥታ ችግር በሸዋሮቢት ከተማ ፣ በቀወት ወረዳ፣ በጅሌ ጥሙጋ አመራሮች ፣ በሀይማኖት አባቶች ፣በአካባቢው ሽማግሌዎች እና ወጣቶች የተቀናጀ ስራ በቁጥጥር ስር ውሏል ሲሉ የመምሪያው ኃላፊ አቶ ዋሲሁን ብርሀኑ አሳውቀዋል።

በአካባቢው የብሔረሰብ ግጭት እንደተነሳ አድርገው ጉዳዩን የሚያራገቡ አካላት ከስህተታቸው መታረም እንዳለባቸው ፤ ከመቼውም ጊዜ በላይ የሁለቱ ዞኖች የፀጥታ አካላትና ህዝቡ ለሰላማቸው ጠንክረው በመስራት ላይ የሚገኙ መሆኑን እና በአሁኑ ሰአት ቀጠናው ሰላሙ ተጠብቆ የማንኛውም እንቅስቃሴ ያልተገደበ እንደሆነ አሳውቀዋል።

በቀጣይም ቢሆን ዘላቂ ሰላምን ከማረጋገጥ አኳያ ህዝቡ ከመንግስት ጎን ሆኖ እንዲሰራ ፣ ከአጉል ሽብር እና መደናገጥ እራሱን እንዲጠብቅ ሲሉ ኃላፊው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ኃላፊው እዛው አካባቢ እንዳሉና ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተሉ አመራር እየሰጡ እንደሆነም ተረድተናል።

ምንጭ :- የሰሜን ሸዋ ዞን የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ፌስቡክ ገፅ

Leave a Reply