መንግስ የጸጥታ ሃይሎች ለየትኛውም ዓይነት ትንኮሳ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ማድረጉን አስታወቀ

– የኑሮ ውድነትን ለማቃለል የአጭርና የረጅም ጊዜ ዕቅድ ተነድፎ እየተሰራ ነው

ለየትኛውም አይነት የጦርነት ትንኮሳ ምላሽ ለመስጠት የጸጥታ ኃይሉ ከየትኛውም ጊዜ በበለጠ መልኩ ዝግጁ መሆኑን መንግስት አስታወቀ። ይህ የተገለጸው የአማራ ክልልና በተለይም የውልቃይት ጠገዴ አስመላሽ ኮሚቴ የአንድ ወር ስንቅ በማዘጋጀት “ክተት” ሲባል እንዲነሳ መታዘዙን ተከትሎ ነው። ትህነግ በበኩሉ ሰሞኑንን ከበባውን ለማስከፈት ጦርነት ለመክፈት ከህዝብ ጋር ተወያይቶ መስማማቱን በቪኦኤ በኩል ማስታወቁ ይታወሳል። የሰላም አማራጭንም እንደ መጀመሪያ አማራጭ እንደሚያይ አመልክቶ ነበር።

ሰሞኑንን በተለያዩ ግንባሮች በመዘዋወር የመከላከያ አባላትን የጎበኙትና ያነቃቁት ጠቅላይ ሚኒስትር የጦርነትን አስከፊነት በማጉላት፣ በኢትዮጵያ ከተመጣ ግን መከላከያ የተለመደውን ክንዱን በተንኳሾች ላይ እንደሚያሳርፍ በግልጽ ሲናገሩ ሰንበተዋል። በተመሳሳይ ለዓለም አቀፍና ዲፕሎማቶችና ለአሜሪካ አምባሳደር መንግስት “ምከሩልን” ማለቱንም ውጭ ጉዳይ አስታውቋል።

በጦርነት የትግራይን ህልውና እንደሚያስጠብቁ ይፋ ያደረገው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር፣ ሕዝቡ ከጎኑ እንደሚሰለፍ ማረጋገጡን ቢያስታውቅም ሱዳን ፖስት ከትናንት በስቲያ ትህነግ በግድ የተመለመሉ ሲጠፉ እየያዘ ማሰሩን ከሶስት ሰዎች በኢሜል ደረሰኝ ሲል መዘገቡ ያታወሳል።


TPLF detaining civilians fleeing forced conscription

In an e-mail sent to Sudans Post this morning, three Tigrayans living in Amsterdam, the Netherlands, said seven of their relatives and five of their friends were arrested at Adi Ramet village last Monday by Tigray forces after trying to flee forced conscription to neighboring Sudan.


ትህነግ አስገድዶ ወደ ግዳጅ ያስገባቸው ምልምሎች መካከል ለመሸሽ የሞከሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን እያሰረ መሆኑን ዘመዶቻቸው እንደነገሩት ያመለከተው የሱዳን ፖስት ዘገባ ትህነግ ከፍተኛ የፖለቲካና ወታደራዊ መሪዎችን ያሳተፈ ቅስቀሳ በማድረግ ለጦርነት እየተዘጋጀ መሆኑን የሚያመለክቱ መረጃዎች እየወጡ መሆኑንን አመልክቷል።

ሱዳን ፖስት ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ሦስት የትግራይ ተወላጆች በኢሜይል መልዕክት አድርሰውኛል ብሎ እንደዘገበው ትህነግ የሚያደርገው ጦርነት ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግሥት ጋር ብቻ ሳይሆን የክልሉን ሰላማዊ ዜጎች በማሰር ትርጉም የለሽ ተግባር እየከወነ ማለታቸውን አስታውቋል።

“በመቶዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆችና ሰላማዊ ዜጎች የሕወሓትን የሽብር ተግባር ለመቀላቀል ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ሲታሰሩ ይህ የመጀመሪያ አይደለም” ያሉት ነዋሪዎቹ ዓለም ዐቀፉ ማኅበረሰብ ትህነግ ጦርነት ውስጥ እንዳይገባና ሰላምን እንዲቀበል ጫና ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው መጠየቃቸውን ዘገባው አመልክቷል። ከላይ ሙሉውን ያንብቡ። የመንግስት ኮሙኒኬሽንን ጠቅሶ ኢፕድ ከታች ያለውን ተያያዥ ዜና አስፍሯል።

መንግሥት ለሕዝብ ተቆርቋሪ መስለው አፍራሽ ተልዕኮ በማንገብ በሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ።እየተስተዋለ ያለውን የኑሮ ውድነት ለመቅረፍ መንግሥት የአጭርና የረጅም ዕቅድ ተነድፎ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።

Advertisements

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ በአገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ትናንት በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ መንግሥት በመላ አገሪቱ ሰላምን ለማስፈን በሰራው ተግባር በአብዛኛው የአገሪቱ አካባቢዎች አንጻራዊ ሰላም ማስፈን ተችሏል። መንግሥት ለሕዝብ ተቆርቋሪ መስለው አፍራሽ ተልዕኮ በማንገብ በሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ ይቀጥላል።

ለሕዝብ ተቆርቋሪ መስለው አፍራሽ ተልዕኮ በማንገብ በሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ መንግሥት የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለጹት ለገሰ ቱሉ (ዶክተር)፤ የግጭት ነጋዴዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ መንግሥት ያስጠነቅቃል። በተለያየ መንገድ የሕዝብን ሰላም የሚያውኩ ቡድኖች ከአሸባሪዎቹ ሸኔና ሕወሓት ተለይተው የማይታዩ በመሆናቸው እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት መንግሥት ለየትኛውም አይነት የጦርነት ትንኮሳ ምላሽ ለመስጠት የጸጥታ ኃይሉ ከየትኛውም ጊዜ በበለጠ መልኩ ዝግጁና አስተማማኝ በሆነ ቁመና ላይ ይገኛል ብለዋል።

እንደ ዶክተር ለገሰ ገለጻ፤ መላው የጸጥታ መዋቅር በወሰደው የተቀናጀ ኦፕሬሽን የአገሪቷን ጸጥታ ለማወክ ከሰሞኑ ብቻ በአዲስ አበባ፣ በሶማሌ ክልል በተለያዩ ዞኖች፣ በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ሀረርጌና በምስራቅ ባሌ ለሽብር ተግባር የተሰማሩ 45 የአልሸባብ የሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ነው።

ከሽብር ቡድኑ አባላት 105 ክላሽ እንኮቭ ጠመንጃ፣ 13 ብሬል፣ 25 አረቤጅ፣ 25 ሳጥን የተለያዩ መጠን ያላቸው ጥይቶች፣አራት መትረየስ፣ አራት ስናይፐር መሳሪያዎች ተይዘዋል። በተጨማሪም በየቤተ እምነቶች የተቀበሩ ፈንጂዎች፣ የእጅ ቦንቦችና የነፍስ ወከፍ መሳሪዎች በሚሰጥ ጥቆማ እየተሰበሰቡ መሆኑን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

እንደ ሚኒስትሩ ማብራሪያ፤ እየተከናወነ ባለው ህግ የማስከበር እርምጃ በኦሮሚያ ክልል በጉጂ፣ በወለጋና በሌሎች አካባቢዎች ላይ በሚንቀሳቀሰው ሸኔ ላይ በተወሰደ ኦፕሬሽን በርካታ የቡድኑ አባላት ተደምስሰዋል፤ ተማርከዋል፤ በርካታ ትጥቆችና ተተኳሾችም በቁጥጥር ስር ውለዋል።

የመንግሥትን የሕዝብን ሰላምና ደህንነት የማረጋገጥ ስራ በመቃወም ድምጻቸውን የሚያሰሙ አንዳንድ አካላት መኖራቸውን ያነሱት ሚኒስትሩ፤ እነዚህ አካላት ወይ ወደ ሰላም መንገድ አሊያም ወደ ቡድኖቹ መግባትና ጎራቸውን መለየት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በትግራይ ክልል ያልተገደበ የሰብአዊ እርዳታ እንዲቀርብ መንግሥት አሁንም ቁርጠኛ አቋም እንዳለውና በዚያ ልክም እየሰራ መሆኑን ያስታወሱት ሚኒስትሩ፤ ባለፈው ሳምንት ብቻ 165 ከባድ ተሽከርካሪዎች መቐሌ መድረሳቸውን ተናግረዋል።

አሸባሪው ቡድን ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ለማደናገር በወረራ ከያዛቸው አካባቢዎች እንደወጣ ቢያወራም አሁንም በአማራ ክልል በወረራ ከያዛቸው አዲአርቃይ፣ ጸለምት፣ አበርገሌ እና ሌሎች አካባቢዎች እንዲሁም ከአፋር ክልል ደግሞ ኮኖቫ፣ በራህሌ፣ አብአላና መጋሌ ወረዳዎች እንዳልወጣ ገልጸዋል።

ከበባውን ለማስከፈት ሲባል የግድ ወደ ጦርነት ለመግባት እገደዳለው በሚል በአሸባሪው ሕወሓት የሚገለጸው የጦርነት ጉሰማና ፉከራ ዳግም የትግራይን ወጣቶች ለማስጨረስ ያለመ መሆኑን የሚያመለክት መሆኑን ገልጸው፤ ይህን እኩይ እንቅስቃሴ የትግራይ ሕዝብ መታገል እንዳለበት አሳስበዋል።

መንግሥት ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የኑሮ ውድነትንና፣ የስራ አጥነት ችግሮችን ለመቅረፍ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኘ ጠቁመው፤ በአሁኑ ወቅት እየተስተዋለ ያለውን የኑሮ ውድነት ለመቅረፍ መንግሥት የአጭርና የረጅም ጊዜ እቅድ ነድፎ እየሰራ መሆኑንም ሚኒስትሩ በመግለጫው አስታውቀዋል።

ዋናው የኑሮ ውድነት ችግር ከምርት አቅርቦት ጋር የሚያያዝ በመሆኑ ችግሮችን ለመፍታት ስንዴ፣ ዘይት፣ አልሚ ምግብና ስኳር የመሳሰሉ ምግብ ነክ ፍጆታዎች በአጭር ጊዜ ለመቅረፍ በፍራንኮ ቫሉታ አሰራር የራሳቸውን የውጭ ምንዛሬ ተጠቅመው እንዲያስገቡ ፍቃድ ተሰጥቷል። በተጨማሪም በግዥ ስርዓቱ ላይ ያሉ መስተጓጉሎችን ለመቅረፍ እየተሰራ ስለመሆኑ ለገሰ ቱሉ (ዶክተር) በመግለጫቸው አመላክተዋል።

Related posts:

«ሕወሓት ጦርነትን እንደ አምልኮ የሚቆጥር ቡድን ነው» – ፕሮፌሰር ሀረገወይን አሰፋ
«በሕገወጦች ላይ ያለ ምኅረት እርምጃ መውሰድ አለብን፤ ይህ የመንግሥት ተግባር ነው» የአማራ ክልል
125 አዳዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ
«በአገሩ መከላከያ ላይ አፉን የሚከፍት ሕዝብ የለም፤ መንግስትም አይታገስም» ክብር ለመከላከያ ሰራዊት!!
በኢትዮጵያና ቱርክ መካከል የተደረገውን የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነት ምክር ቤቱ አጸደቀ
የሞት ፍርደኛው የ25 ዓመታት ሰቆቃ! ከመሬት በታች የታፈኑት አባት
«ኢትዮዽያን ማስቀጠል ከሚፈልጉት ጎን በመሆናችን የሚከፋ ከአለ እርሱ መፍረሷን የሚናፍቅ ብቻ ነው!»
ደብዳቤ ለኢትዮጵያ - ከቢልለኔ ስዩም
የዓለም ባንክ የ300 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ፈረመ
"እናቴ ፍጹም እስር ቤት እንድትገባ አልፈግም" ብሎ እግሩን ያጣው ወጣት ምስክርነት ለሮይተርስ
"አልዘምትም" ወይም "ከጠላት ጎን እሰለፋለሁ" ማለት ሲቻል ማውሰብሰብና ማድበስበስ አይገባም!
አብዱላሂ ፋርማጆ ለአዲሱን ፕሬዝዳንት «ሁሉም ወገኖቼ እንዲደግፉህና እንዲጸልዩልህም እጠይቃለሁ»
በትግራይ 5.2 ሚሊዮን ሕዝብ ዕርዳታ እየደረሰ ነው፤ ከሺህ በላይ የጭነት መኪኖች ታግተዋል፤ 76 ቢሊዮን ብር ወደ ትግራይ ተልኳል
የደህንነት ጥናት አዲሱ ምዕራፍ - ጂኦስፓሻል ኢንተለጀንስ
ዳግም ጦርነት እንዳይጀመር ስጋት የገባው ኢሰመኮ የማስጠንቀቂያ ጥሪ አሰማ

Leave a Reply