ኢራን እና አርጀንቲና የ “ብሪክስ”ን ቡድን ለመቀላቀል ማመልከታቸው ተሰምቷል፡፡

ኢራን እና አርጀንቲና ቡድኑን ለመቀላቀል ጥያቄ ያቀረቡት ባሳለፍነው ሣምንት በተካሄደው የ“ብሪክስ ፕላስ” ጉባዔ ላይ መሆኑም ነው የተጠቆመው፡፡

የኢራኑ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራኢሲ እና የአርጀንቲናው ፕሬዚዳንት አልቤርቶ ፈርናንዴዝ በ“ብሪክስ ፕላስ” ጉባዔ ላይ መሳተፋቸው ይታወሳል፡፡

የአርጀንቲናው ፕሬዚዳንትም “ብሪክስ” በምዕራባውያን የሚዘወሩ የኢኮኖሚ ተቋማትን የሚገዳደር መሆን አለበት ሲሉ በጉባዔው ላይ አስተያታቸውን ሰጥተዋል ነው የተባለው፡፡

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሰኢድ ኻቲብዘዴህ ÷ “የብሪክስ አባል ሀገራት የዓለምን 30 በመቶ ኢኮኖሚ የሚዘውሩ እና 40 በመቶ የሚሆነውን ህዝብ የያዙ መሆናቸው ሊታወቅ ይገባል” ሲሉ የቡድኑን ተጽእኖ ፈጣሪነት ማሳየታቸውን አርቲ ዘግቧል ፡፡

ቃል አቀባዩ ኢራን አባል መሆኗ ትልቅ ዕሴት እንደሚጨምርም ነው የተናገሩት፡፡

የብሪክስ ቡድን መስራቾች ብራዚል፣ ሩስያ፣ ሕንድ፣ ቻይና እና ደቡብ አፍሪካ ናቸው፡፡

(ኤፍ ቢ ሲ)

Leave a Reply