የኩሪፍቱ ሪዞርት ባለቤት “ያፈነኝ የለም፣ ሰላም ነኝ” አሉ

“አቶ ታዲዮስ ጌታቸው በታጣቂዎች አልታገቱም” ሲሉ እሳቸውን አስመልክቶ የተባለው ሃሰት እንደሆነ፣ እሳቸው የስራ ሰው በመሆናቸው የሚፈልጋቸውም እንደሌላ መናገራቸው ተሰምቷል።

የኩሪፍቱ ሪዞርት ባለቤት በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መታፈናቸና መወሰዳቸውን አስቀድሞ ያስታወቀው ማን እንደሆነ ባይታወቅም፣ ዜናው በማህበራዊ ሚዲያዎች በስፋት ተሰራጭቶ ነበር። ዜናውን በማራባት ከፍተኛ ሚና የነበራቸው ክፍሎች የባለሃብቱን መታፈን ለምን ማረጋእብ እንደፈለጉ በውል የተገለጸ ነገር የለም።

የኩሪፍቱ ሪዞርት ባለቤት አቶ ታዲዮስ ጌታቸው በታጣቂዎች ታግተዋል በሚል በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ እየተዘዋወረ መነጋገሪያ በሁነበት ቅጽበት፣ ኢትዮ ኤፍ ኤም የኩሪፍቱ ሪዞርት ባለቤት የሆኑት አቶ ታዲዮስ ጌታቸው ላይ ስልክ ደዉሎ ወሬው ሃሰት መሆኑንን ይፋ አድርጓል። ለስራ ጉዳይ በሱዳን እንደሚገኙና የሚባለዉ መረጃ ፍጹም ሃሰተኛ መሆኑን በአንደበታቸው ማረጋገጣቸውን አመልክቷል።

አቶ ታዲዎስ አክለዉም በቀጣይ በአርባ ምንጭ አካባቢ ለሚሰሩ ስራዎች ከአጋሮች ጋር ለመነጋገር ወደ ሱዳን ማቅናታቸዉን ተናግረዉ፣ እርሳቸዉን በሚመለከት በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ የሚናፈሰዉን መረጃ እንደማንኛዉም ሰዉ ዛሬ ጠዋት አካባቢ መመልከታቸዉን ገልጸዋል፡፡ “እኔ ሰላም ነኝ”፤በሚወራዉ ነገር ለተደጋገጡና ትክክለኛዉ መረጃን ለማወቅ ለሚፈለጉ ሰዎች የምለዉም ይህንኑ ነዉ ብለዋል፡፡

You may also like...

Leave a Reply