የአማራ ብልጽግና ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በዝግ እየመከሩ ነው

የብልጽግና ፓርቲ በአማራ ክልል የሚገኙ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች የተሳተፉበት “ድሎችን የማጽናትና ፈተናዎችን የመሻገር ወቅታዊና ታሪካዊ የአመራር ተልዕኮ” በሚል ርዕስ ነው ውይይቱ እየተካሄደ የሚገኘው።

የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሠሞኑን ባካሄደው ውይይት ያሣለፋቸውን ውሣኔዎች ተከትሎ ነው፤ በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ ትኩረት ያደረገ ውይይት መካሄድ የጀመረው፡፡

የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ እና የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ግርማ የሽጥላ የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሠሞኑን ባካሄደው ውይይት ያሣለፋቸውን ውሣኔዎችን የያዘ የውይይት ሰነድ ገለፃ አድርገዋል፡፡

አመራሩ እያጋጠሙን ያሉ ውስጣዊና ውጫዊ ተግዳሮቶችን በብቃት ተሻግሮ የብልጽግናን ራዕይ ከግብ በማድረስ በየደረጃ ለሚገኘው አመራር፣ አባላትና ለሕዝቡ በቂ ግንዛቤ በመፍጠርና ኃይል በማሰባሰብ ተጨማሪ የፓርቲና የመንግሥት ተቋማዊ አቅም ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።

በመድረኩ ላይ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መሥተዳደር ጌታቸው ጀምበር (ዶ.ር)፣ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ዳይሬክተር ጀነራል ተመስገን ጥሩነህ ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

ለክልሉ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች እየተካሄደ የሚገኘው ውይይት ዛሬና ነገ የሚካሄድ መኾኑ ተገልጿል።

መረጃው የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ነው።

See also  የአማራ ሕዝብ ነጻነቱን የሚያስከብረው በክንዱ ነው - የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር

Leave a Reply