በተቋማት ለተታለሉ ዜጎች ማን ይካስ? ዘጠኝ መቶ የሃሰተኛ ትምህርት ማረጃ ተገኘ

የትምህርት ሚኒስቴር ይፋ እንዳደረገው ሆን ብለው የተመሳሰለ የትምህርት ማስረጃ ያሰሩ እንዳሉ ሁሉ ፈቃድ ባላገኙበት የትምህርት ዘርፍ አስልጥነናል በሚል ማስረጃ የሰጡ አታላዮች ላይ ቢገልጽም ስለተጠያቂነት ያለው ነገር የለም።

በአንዳንድ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ በተደረገው ማጣራት ከባለስልጣኑ እውቅና ውጭ ካምፓስ ማስፋፋትን ፍቃድ ባላገኙበት የትምህርት ዘርፍ ስልጠና ሲሰጡ መገኘታቸውን እንዳረጋገጠ ያስታወቀው የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ነው።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በ18 ሺህ የትምህርት ማስረጃዎች ላይ በተደረገ የህጋዊነት ማረጋገጫ 900 የሚሆኑት ሀሰተኛ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። ኢዜአ እንደዘገበው በ18 ሺህ የትምህርት ማስረጃዎች ላይ የህጋዊነት ማረጋገጫ ተደርጎ 900 የሚሆኑት በተለያዩ ምክንያቶች ሀሰተኛ ማስረጃዎች ናቸው።

ሃሰተኛነታቸውን የማረጋገጥ ስራ የተከናወነው በዘንድሮው በጀት ዓመት የትምህርት ማስረጃ ህጋዊነትና ትክክለኝነት እንዲረጋገጥላቸው ከጠየቁ 18 ሺህ ደንበኞች መሆኑም ታውቋል።

የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን በተቀናጀ ከፍተኛ ትምህርት ፍቃድ አሰጣጥ፣ የፍቃድ እድሳት፣ ክትትልና ቁጥጥር ዙሪያ በትብብር ለመስራት ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሂዷል።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ፤ በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልእክት ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ጉዳይ እየተባባሰ መምጣቱን ገልጸዋል።

በዘንድሮው በጀት ዓመት እስካሁን 18 ሺህ ደንበኞች የትምህርት ማስረጃ ህጋዊነትና ትክክለኝነት እንዲረጋገጥላቸው ጠይቀው ከእነዚህ ውስጥ 900 የሚሆኑት በተለያዩ ምክንያቶች ሀሰተኛ ሆነው መገኘታቸውን ተናግረዋል።

በመሆኑም የትምህርትና ስልጠና ጥራትንና አግባብነትን እንዲሁም ትክክለኛነትን ለማረጋገጥ የጋራ ጥረት የሚጠይቅ መሆኑን ገልጸዋል።

የትምህርት ማስረጃዎቹ ተመሳስለው የተሰሩ፣ እውቅና ከሌለው ተቋም የተሰጡ፣ ባልተፈቀደ የሙያ መስክ የሰለጠኑ፣ የመቁረጫ ነጥብና የብቃት ማረጋገጫ ሳይኖራቸው የሠለጠኑ ስለመሆኑም አብራርተዋል።

በአንዳንድ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ በተደረገው ማጣራት ከባለስልጣኑ እውቅና ውጭ ካምፓስ ማስፋፋትን ፍቃድ ባላገኙበት የትምህርት ዘርፍ ስልጠና ሲሰጡ መገኘታቸውንም አረጋግጠናል ብለዋል።

ባልተፈቀደላቸው የትምህርት መርሃ ግብርና ከተቀመጠላቸው ቁጥር በላይ ተማሪዎችን ተቀብለው ሲያስተምሩ የነበሩም መገኘታቸውን ጠቅሰዋል።

ለሁለት ቀናት በሚካሄደው የውይይት መድረክ የክልልና የከተማ አስተዳደር የሲቪል ሰርቪስ ሃላፊዎች፣ የፖሊስ፣ የትምህርትና ስልጠና እንዲሁም የትምህርት ተቋማት ሃላፊዎች እየተሳተፉ ነው።

See also  ሰሞኑን እየታየ ያለው ጉንፋን መሰል ወረርሽኝ ኮቪድ የመሆን እድሉ ከፍተኛ ነው

Leave a Reply