ከአውሮፓ ሕብረትና ፈረንሳይ ጋር የ32 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ተሰጠ

ኢትዮጵያ፣ከአውሮፓ ሕብረትና ፈረንሳይ ጋር የ32 ሚሊዮን ዩሮ የድጋፍ ስምምነት ዛሬ ተፈራርማለች።ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሬታ ሰዋሰው፣ የፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ቫለሪ ቴሂዮና በኢትዮጵያ የአውሮፓ ሕብረት ልዑክ የትብብር ኃላፊ ስቴፋን ሎክ ተፈራርመዋል።

የመንግስት መገናኛዎች እንዳሉት ድጋፉ በግጭት አካባቢ የተጎዱ አካባቢዎች ተግባራዊ ለሚሆነው የምግብ ዋስትና ፕሮጀክትና የግብርና መልሶ ማገገም ስራዎች እንደሚውል የገንዘብ ሚኒስቴር በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው መረጃ ገልጿል።

የፈረንሳይ ልማት ኤጀንሲ 18 ሚሊዮን ዩሮ እንዲሁም የአውሮፓ ሕብረት 14 ሚሊዮን ድጋፉን እንደሚያደርጉ ዜናው አመልክቷል። ፕሮጀክቱ በግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢኒስቲትዩት እንደሚተገበርም ተጠቁሟል።

ኢትዮጵያ ፍትህ ተዛብቶባት ራሷንና ዜጎቿን ከመፍረስ አደጋ ለመከላከል በወሰደችው አስገዳጅ የህልውና ዘመቻ ሳቢያ ዓለም እንዲያድምባት ተደርጎ መቆየቱ አይዘነጋም። አሁን ላይ የተዘጉት በሮች እየተከፈቱ መሆናቸውን የሚያሳዩ ስምምነቶች እየተፈጸሙ ይገኛሉ።

See also  ብዙ ግፍ ለመስማት ተዘጋጁ፤ ሸዋሮቢት በትህነግ ወራሪዎች በቡድን የተደፈሩት እናት ራሳቸውን አጠፉ!

Leave a Reply