ዶናልድ ትራምፕ በወንጀል ተጠርጥረው ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ተገለጸ

የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በወንጀል ተጠርጥረው በዛሬው ዕለት በኒውዮርክ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ተገለጸ፡፡

የቀድሞው ፕሬዝዳነት ክስ የተመሰረተባቸው እ.ኤ.አ. ከምርጫ 2016 በፊት ከወሲብ ፊልም ተዋናይዋ ስቶርሚ ዳንኤልስ ጋር የነበራቸውን ግንኙነት በሚስጥር እንድትጠብቅ ለማድረግ ከከፈሉት 130 ሺሕ ዶላር ጋር በተያያዘ እንደሆነ ተዘግቧል፡፡

የክሱ ዝርዝር ይዘት ለተከሳሹ በችሎት የሚነበብ ሲሆን ከፎቶግራፍ አንሺ ባለሙያዎች ውጭ ለሚዲያ ዝግ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

ፕሬዝዳንቱ ክሱን የሌለ ነገር ፍለጋ ነው ሲሉ በማጣጣል ምንም የሰራሁት ወንጀል የለም ብለዋል፡፡

የፕሬዝዳንቱ ጠበቃ ደንበኛዬ ከተጠረጠረበት ክስ ነጻ ነው ብለዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ በሚቀርቡበት ፍርድ ቤት አካባቢ በደጋፊዎች ሁከት እንዳይፈጠር ከፍተኛ የጸጥታ ጥበቃ እየተደረገ መሆኑን ቢቢሲ በዘገባው አመላክቷል፡፡

ትራምፕ በአሜሪካ ታሪክ በወንጀል የተከሰሱ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሆኖ መመዝገባቸውም ተመላክቷል፡፡

ዶናልድ ትራምፕ ለ2024 የአሜሪካ ፕሬዝዳናታዊ ምርጫ ተወዳዳሪ ሆነው ለመቅረብ ዘመቻ ላይ ሲሆኑ በአጭር ጊዜ ከ8 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለምርጫ ዘመቻ መሰብሰባቸውን መረጃው ያሳያል፡፡

(ዋልታ)

See also  በሙስና ወንጀል የተከሰሱት ሁለቱ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች የክስ መቃወሚያቸውን አቀረቡ

Leave a Reply