የጡት ካንሰር ከቁጥጥር ውጭ በሆነ መንገድ በጡት ውስጥ ያሉ ሕዋሳት አድገው እና ተከፋፍለው ዕጢ ሲፈጥሩ የሚከሰት ሕመም ነው።
እንደ ሌሎች የካንሰር ሕዋሳት ሁሉ የጡት ካንሰርም በጡት ዙሪያ ወደሚገኙ ሕዋሳት ውስጥ ገብቶ ሊያድግ እና ሊሰራጭ ይችላል፡፡
ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎችም በመጓዝ አዳዲስ ዕጢዎችን ሊፈጥር ይችላል።
የጡት ካንሰር በሴቶች ላይ ከሚከሰቱት የካንሰር ዓይነቶች አንዱ ነው።
የጡት ካንሰር ከቆዳ ካንሰር ቀጥሎ በብዛት ከሚከሰቱ ካንሰሮች ውስጥ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ነው።
የጡት ካንሰር ብዙውን ጊዜ ከ 50 ዓመት በላይ በሆኑ ሴቶች ላይ ይከሰታል፡፡
ሲጋራ እና አልኮል መጠቀም ፣ ከልክ ያለፈ ውፍረት ፣ የሆርሞን ወሊድ መከላከያ ወይም ሌላ የሆርሞን መድሃኒት ለረጅም ጊዜ መጠቀም እና የጨረር ሕክምና ለጡት ካንሰር መከሰት ምክንያቶች ናቸው::
በተጨማሪም በቤተሰብ ውስጥ የጡት ካንሰር መኖር፣ አለመውለድ ወይም የመጀመሪያ ልጅን ከ30 ዓመት በኋላ መውለድ፣ ከወለዱ በኋላ ጡት አለማጥባት ፣ ከ12 ዓመት ዕድሜ በፊት የወር አበባ መምጣት እና ከ 55 ዓመት ዕድሜ በኋላ የወር አበባ ዘግይቶ መቆም እንደ መንስዔ ሊወሰዱ ይችላሉ::
የጡት ካንሰር ምልክቶች ምንድን ናቸው?
በብዛት የሚስተዋሉ የጡት ካንሰር ምልክቶች በጡት መጠን ወይም ቅርጽ ላይ ለውጥ ማየት ፣ የአተር መጠን ያለው እብጠት፣ በጡት ወይም በጡት ጫፍ ላይ የመልክ ወይም የቆዳ ለውጥ፣ ከቆዳው በታች እብነ በረድ የመሰለ ጠንካራ ቦታ መኖር ናቸው፡፡
በተጨማሪም ከጡት ጫፍ ውስጥ በደም የተበከለ ወይም ንጹህ ፈሳሽ መኖር ፣የተሰራጨ ዕጢ ከሆነ ደግሞ የደረት ሕመም፣ የአጥንት ሕመም እና የመሳሰሉት ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡
ሕክምናውን በተመለከተ
የጡት ካንሰር ምርመራ ለማድረግ በዋነኛነት ማሞግራፊ ፣ አልትራሳውንድ ፣ እና ፒኢቲ(PET) የተሰኙት ምርመራዎች የሚታዘዙ ሲሆን አጠራጣሪ ውጤቶች ሲገኙ ናሙና ተወስዶ ምርመራ ይደረግበታል ::
ሕክምናን በተመለከተም ቀዶ ጥገና ፣ ኪሞቴራፒ፣ የጨረር ሕክምና፣ የሆርሞን ቴራፒን ጨምሮ በርካታ የጡት ካንሰር ሕክምና አማራጮች አሉት።
ሕክምናው የሚወሰነው ዕጢው ያለበት ቦታ እና መጠን፣ የላብራቶሪ ምርመራ ውጤቶች እና ካንሰሩ ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች መስፋፋቱን ጨምሮ በተለያዩ ሁኔታዎች ላይ ይደረጋል።
ሕክምናው ቀደም ብሎ ከተሰጠ የመዳን ዕድሉ ከፍ ያለ በመሆኑ ማንኛውም ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች ያለበት ሰው በተቻለ ፍጥነት የሕክምና ምርመራ ማድረግ እንዳለበት ዶክተሮች ይመክራሉ፡፡
ምንጭ፡- የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ + fana
- የባህር ወንበዴ ሲሳዮች – በገሃነም የሚመሰለው ስቃይየ34 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ ከአውሮፕላኑ ሲወርድ እግሮቹ ቆስለው መራመድም ሆነ መቆም አቅተውታል። ብርክ ይዞት ይንገዳገዳል፡፡ ይህ ሰው የተሻለ ህይወት ይኖረናል ብለው በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ሳኡዲ… Read more: የባህር ወንበዴ ሲሳዮች – በገሃነም የሚመሰለው ስቃይ
- የህፃናት የደም ካንሰር አይነቶች፣ ምልክቶችና ህክምናዎችየተለያዩ የደም ካንሰር አይነቶች ያሉ ሲሆን በዋናነት ብዙ ጊዜ በህፃናት ላይ በመከሰት የሚታወቀው ‘አኪውት ሊምፎብላስቲክ ሉኪሚያ’ ነው። ሁለተኛው በህፃናት ላይ የሚከሰት የደም ካንሰር ‘አኪውት ማይሎጂነስ… Read more: የህፃናት የደም ካንሰር አይነቶች፣ ምልክቶችና ህክምናዎች
- የቶንሲል ህመም ምንነትየቶንሲል በሽታ በጉሮሮ የኋላ ክፍል ላይ ያሉ ሁለት የጅምላ ቲሹዎች የሚከሰት ሆኖ በሕጻናት ላይ በስፋት የሚታይ ነው፡፡ ህመሙ አንዴ ከያዘና በትክክል ሕክምና ካልተደረገለት በተደጋጋሚም ሊያጋጥም… Read more: የቶንሲል ህመም ምንነት
- የሪህ በሽታ ምንድን ነው?በዓላትን ተገን አድርገዉ ከሚከሰቱ በሽታዎች መካከል አንደኛዉ ሪህ ሲሆን በበዓላት ወቅት ከአመጋገባችን ጋር በተያያዘ የሚከሰት ነዉ፡፡ በሽታው ከበዓላት መምጣት ጋር ተያይዞ በብዛት ቢስተዋልም በአዘቦት ቀንም… Read more: የሪህ በሽታ ምንድን ነው?
- በትግራይ ክልል ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች እህልና አልሚ ምግብ እየተጓጓዘ ነውበትግራይ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ከ23 ሺ ኩንታል በላይ እህልና አልሚ ምግብ እየተጓጓዘ መሆኑን የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታወቀ። ኮሚሽኑ ወደ ትግራይ ክልል ከትናንት… Read more: በትግራይ ክልል ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች እህልና አልሚ ምግብ እየተጓጓዘ ነው