በለጠ ሞላ ከሁለተኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ጎን ለጎን የኒኩሌር ልማት ስምምነት ይፈጽማሉ

  • የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ ከሩሲያ የፌዴራል ማዕድን ኤጀንሲ ሚኒስትር ጋር ተወያይተዋል፤ የኒኩሌር ቴክኖሎጂ ልማት ስምምነት ውል ይፈጸማል

የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ ከሩሲያ የፌዴራል ማዕድን ኤጀንሲ ሚኒስትር ዶክተር ኢቭጌኒ ፔትሮች ጋር ውይይት አድርገዋል። ሁለተኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ በተያዘው ሳምንት ማገባደጃ ላይ በቅዱስ ፒተርስበርግ ከተማ ይካሄዳል። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ የኢትዮጵያ ልዑክ አባል ሆነው በጉባኤው ላይ ይሳተፋሉ።

የኢትዮ-ሩሲያ በይነ መንግስታት የጋራ ኮሚሽን ጥምር ሰብሳቢ የሆኑት በለጠ ሞላ ከሩሲያ የፌዴራል ማዕድን ኤጀንሲ ሚኒስትር ኢቭጌኒ ፔትሮቭ ጋር በሞስኮ ከጉባኤው ጎን ለጎን ስለሚፈረሙ የሁለቱ አገራት ስምምነቶች፣ በቀጣይ ስለሚጠበቁ ስምምነቶች ያሉበትን ደረጃ አስመልክቶ ሀሳብ ተለዋውጠዋል።

የሁለቱ አገራትን የኢኮኖሚ ግንኙነት የማጠናከር፣ የንግድ ምክር ቤቶችን የሚያሳትፍ ፎረም የሚዘጋጅበትን ሁኔታ መፍጠር፣ በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ዲጂታላይዜሽን፣ በስፔስ ሳይንስ ጥናት፣ በአቅም ግንባታ፣ በምርምር፣ በትምህርት፣ በጤና፣ እና በጋራ ስለሚሰሩ ዘርፈ ብዙ አጀንዳዎች መክረዋል።

በጉባኤው ኢትዮጵያ እና ሩሲያን የተመለከቱ የጎንዮሽ ውይይቶች እንደሚደረጉና የጋራ ስምምነቶች በአገራቱ መካከል እንደሚፈረሙ ይጠበቃል።

ኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ አገልግሎት ለማዋል የተዘጋጀውን ፍኖተካርታ እና በሩሲያ ተመራማሪዎች በኢትዮጵያ ላለፉት 35 ዓመታት በኢትዮጵያ ይካሄድ ለነበረው የባዮሎጅካል ኤክስፔዲሽንና ጥናት ስራን በጋራ ለማካሄድ የጋራ ጥናት ማዕከል ማቋቋሚያ ሰነድን እና ሌሎች የኢትዮጵያ ተቋማትን የተመለከቱ ስምምነቶች ይፈረማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮ-ሩሲያ በይነመንግስታት የጋራ ኮሚሽን ጥምር ሰብሳቢ የሆኑት የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ እና በሩሲያ የፌዴራል ማዕድን ኤጀንሲ ሚኒስትር የቭጌኔ ፔትሮቭ በሩሲያ ሞስኮ ተወያይተዋል።

በውይይታቸው ከመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ስለሚፈረሙ የሁለቱ ሀገራት ስምምነቶች፣ ያላለቁና ለወደፊት አልቀው ይፈረማሉ ተብሎ ስለሚጠበቁ ስምምነቶች የደረሱበትን ደረጃ የተመለከተ መረጃ መለዋወጣቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በሩሲያ ተመራማሪዎች ላለፉት 35 ዓመታት በኢትዮጵያ ይካሄድ ለነበረው የባዮሎጂካል ቅኝትና ጥናት ስራን በጋራ ለማካሄድ የጋራ ጥናት ማዕከል ማቋቋሚያ ሰነድ እና ሌሎች የኢትዮጵያ ተቋማትን የተመለከቱ ጉዳዮች ይፈረማሉ ተብለው ከሚጠበቁ ጉዳዮች መካከል ናቸው። ሲል የዘገበው ኦቢ ኤን አማርኛው ዝግጅት ነው።

See also  ትህነግ ሲዘጋ፤ ኢትዮጵያ ትወቀሳለች- እስከመቼ በዚህ ይቀጥላል?

ይህንን ማስፈንጠሪያ ethio12news ተጭነው በቴሌግራም ገጻችን ይከተሉን

Leave a Reply