የጎንደርን ከተማ ምን አይነት ተኩስ እንደሌለ ተገለጸ፤ ጎንደር ተይዛለች ተብሎ ነበር

“ጎንደር ከተማን ሙሉ በሙሉ ይዘናታል” ሲሉ ስማቸው እንዳይገለጽ ጠይቀው ለጀርመን ድምጽ መረጃ በሰጡ የአማራ ሕዝባዊ ኃይል ፋኖ ቃል አቀባይ አየር ማረፊያውን ሆን ብለው እንዳልያዙ አመልክተዋል። እሳቸው ተናገሩ የተባለው በጀርመን ድምጽ እየተሰማ በለበት ሰዓት በተመሳሳይ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ውጊያ መደረጉን ሳያስተባብል ከተማዋን ለመያዝ የገባው ሃይል መደምሰሱን አሃዝ ጠቅሶ አመልክቷል። አገር መከላከያም ስም ጠቅሶ ከተደመሰሱት መካከል አመራሮች እንዳሉበት አስታውቋል።

“ቃል አቀባይ የተባሉት” እንዳሉት ይህ ማጥቃት ሁለተኛው ዙር ነው። እሳቸው ባይሉትም በመጀመሪያው ዙሩ ጎጃም ባህር ዳር ከተማን ጨምሮ ዙሪያዋንና ጎንደርን የመሳሰሉ ከተሞችን እስከ መቆጣጠር ተደርሶ ነበር። ክልሉ የፌደራል መንግስትን ጣልቅ እንዲገባ ከጠየቀ በኋላ ብዙም ሳይቆይ ከተሞቹና አብዣኛው አካባቢዎች በመከላከያ እጅ ስር መውደቃቸው መገለጹ አይዘነጋም።

“አሁን ላይ ጎንደር ከተማ ከተኩስ ድምፅ ነፃ ሆናለች” ሲሉ ምስክርነታቸውን የሰጡ እንዳሉት የመከላከያ ተጨምሪ ሃይል ገብቶ ተኩስ የተካሄደባቸውን ውስን ቀበሌዎች ተቆጣጥሯል። ቃል አቀባዩ ጎንደርን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠራቸውንና ተጨማሪ ከተሞችን የመቆጣተሩ ኦፕሬሽን ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አምልክተዋል። ከተማዋና ነዋሪዎቿ እንዳይጎዱ በጥበብ የታገዘ የጥንቃቄ ጦርነት እንዳካሄዱ ገልጸዋል። እሳቸው እንዳሉ የአገር መከላከያ በስም ያልተቀሷቸውን ባንኮችንና ተቋማትን እንደዘረፈ ጠቅሰዋል።

ነዋሪዎች እንደሚሉት ከሆነ የመንግስት የፀጥታ ኃይል ከተማዋን እንደተቆጣተረ ብቻ ሳይሆን ለሊት ሊነጋጋ አካባቢ በተጠቀሱት አካባቢዎች ወደ ጎንደር ገብቶ የነበረው የፋኖ ሃይል ታጣቂዎች ከነበሩባቸው አካባቢዎች ሊነጋጋ ሲል ግብተው ቀን ከምሳ በሁዋላ ጎንደርን ለቀዋል። አገር መከላከያ ባሰራጨው ዜና በ”ፋኖ ስም ይነግዳሉ” ያላቸው ታታቂዎች ዝርፊያ አካሂደዋል። እስረኛ ለማስለቀቅ ሞክረዋል። ተቋም አቃጥለዋል።

ነዋሪዎቹ ዝርዝር ባይነገሩም የከተማ ኮማንድ ፖስት የሚከተለውን አጭር ማብራሪያ አሰራጭቷል።

የጠላት ሀይል ዛሬ ሌሊት 10፡00 ላይ ሰርጎ በመግባት አንድ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር የሞከረ ሲሆን የፀጥታ መዋቅራችን አኩሪ ተጋድሎ አድርጓል። ንፁሐን እንዳይጎዱ በማድረግ የጠላት ሀይል አመራሮችን ጨምሮ ከ50 በላይ ሙትና ቁስለኛ በማድረግ የተወሰነው ደግሞ የወገን ሀይልን ምት መቋቋም አቅቶት በመፈርጠጥ ላይ ይገኛል። ጽንፈኛው ሃይል በጎንደር ዙሪያ ሲያደርግ የነበረው ትንኮሳ በመከላክያ ሃይል አፋጣኝ እርምጃ ተወስዶበት ሙሉ በሙሉ ከሽፎ ወደመጣበት ተመልሷል። የህዝቡን እና የከተማዋን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ለማወክ የተንቀሳቀሱ የጽንፈኛ ሃይል አመራሮች በጎንደር ከተማ የእርምት እርምጃ የተወሰደባቸው ቢሆንም ህዝብን በማደናገር አባዜ የተለከፈው ይህ ጽንፈኛ ሃይል ጎንደሬ ከተማን ተቆጣጥረነዋል በሚል የተለመደ የሃሰት ወሬዎችን ማሰራጨቱን ተያይዞታል። ይህ አላማ የሌለው ሀይል እንኳን ጎንደርን ያክል ትልቅ ከተማ መንደር መቋጣጠር የማይችል ደካማ ሀይል መሆኑን እየገለፅን በቀጣይም ጸረ ሰላም ሃይሉ ላይ የምንወስደውን እርምጃ አጠናክረን የምንቀጥል መሆኑን እየገለፅን ህዝባችንም ለሰጠን ድጋፍ ከልብ እያመሰገን ቀጣይም ህዝባችን የተለመደውን ድጋፍ እንዲያደርግ ስንል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። ወቅቱ የሚጠይቀውን መሰዋትነት በመክፈል ለህዝባችን ዘላቂ ሰላም እናጎናፅፍለን!! መስከረም 13/2016 ጎንደር

See also  ትህነግ በውጊያ በቆሰሉና በሞቱ ታጣቂዎቹ "የጅምላ ጭፍጨፋ ተደረገ የሚል" የሴራ እቅድ ማዘጋጀቱ ተጋለጠ

ልክ አስተዳደሩ እንዳለው “በጎንደር ከተማ ከትናንት ጀምሮ በመንግስት ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ከባድ ውጊያ ሲደረግ መቆየቱን የአይን ምስክሮች አመልክተዋል። የጀርመን ድምጽ ውጊያውን “ከባድ” ካለ በሁዋላ “በጎንደር ከተማ በተለይ በቀበሌ 18 ሸዋ ዳቦ በሚባል አካባቢ እስከ እኩለ ቀን የደረሰ ውጊያ ሲደረግ መቆየቱን እና በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት ሳይደርስ እንዳልቀረ “ነዋሪዎች ነግረውኛል” ብሏል። የተቃጠለ የመከላከያ ተሽከርካሪ ያዩ መኖራቸውንም አክሏል።
“በጎንደር ‘ከባድ ውጊያ’ መካሄዱን የፋኖ ቃል አቀባይም ለዶይቸ ቬለ አረጋግጠዋል” ያለው ዘገባ ቃል አቀባዩ የጎንደርን ሙሉ በሙሉ መቆጣተራቸውን አስታውቀው የአየር ማረፊያውን ግን ሆን ብለው እንዳይጎዳ በማሰብ እንዳልያዙ አመልተዋል። እኚሁ የጀርመን ድምጽ ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸውን እንዳይጠቀስ ጠይቀዋል ያላቸው የአማራ ሕዝባዊ ኃይል ፋኖ ቃል አቀባይ “አመሻሽ ጀምሮ የሁለተኛው የትግሉ ምዕራፍ የመጀመሪያ ዙር የማጥቃት እንቅስቃሴ ተጀምሯል” ማለታቸውን አመልክቷል።

ጎንደርን ለመቆጣጠር የተደረገው ሙከራ መክሸፉን አስተዳደሩ ብቻ ሳይሆን መከላከያም ለመጀመሪያ ጊዜ አስታውቋል። መከላከያ በስፍራው ያሉትን አመራሮች ጠቅሶ ዜና አሰራጭቷል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ክልከላዎች ተከተሎ የተሻሻሉ ጉዳዮችን በማዬት በጎንደር ከተማና በሌሎች አካባቢዎች የኮማንድ ፖስቱ የሠዓት እላፊ ማሻሻያዎችን ማድረጉን እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም የታሰበው ሁሉ መክሸፉን አመልክቷል።

“በፋኖ ስም የሚነግደው ፅንፈኛ ሃይል በጎንደር ከተማ ዛሬ ከጧት ጀምሮ በለኮሠው እሳት መለብለቡን ከሥፍራው የሚገኘው መከላከያ ሠራዊት አመራር አሥታወቀ” ሲል የሚጀምረው ዜና እንደሚከተለው ይነበባል። እንዳለ አቅርበነዋል።

በተለያዬ መንገድ በአማራ ክልል አካባቢዎች የተከሠተውን የፅንፈኛ ሃይሎች የህዝቡን የሠላም: የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ በሃይልና በአፈሙዝ የመፍታት ፍላጎት ከንቱ ነው።

የህዝቡን ፍትሃዊ ጥያቄ በሠላማዊ መንገድ ለመፍታት መንግስት በርካታ የሠላም አማራጮችን ቢዘረጋም ችግሩ ሊስተካከል ባለመቻሉ ምክንያት የሚኒስትሮች ምክር ቤት በተሠጠው ሥራና ሃላፊነት መሠረት የአሥቸኳይ ጊዜ አዋጅ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲፀድቅ ማድረጉ የሚዘነጋ አይደለም።

የአሥቸኳይ ጊዜ አዋጁን ክልከላዎች ተከተሎ የተሻሻሉ ጉዳዮችን በማዬት በጎንደር ከተማና በሌሎች አካባቢዎች የኮማንድ ፖስቱ የሠዓት እላፊ ማሻሻያዎችን ማድረጉም አይዘነጋም።

See also  የኮንትሮባንዲስት ፖለቲከኞች ሴራ አዲስ አበቤን እያነከተው ነው፤ የዚህ ሁሉ ሴራ ባለቤት ግን ማን ነው?

እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ነገሮች በሠላም ወዳዱ ህዝብና በፀጥታ ሃይሉ መሥመር እየያዙ መሻሻል እያሳዩ ባሉበት በዚህ ሰዓት የራሳቸውን ጥቅም ፍላጎት ብቻ የሚያራምዱ በፋኖ ሥም የሚነግዱ የሽፍታ ቡድኖች ዛሬ በጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ያልተገባ ድርጊት መፈፀማቸው ተገልጿል።

ይህ የህዝብን ሠላማዊ ህይወት የሚያናጋ ተግባር በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ ማሥነሳቱም አልቀረም። የሽፍታ ቡድኑ ቀበሌ 18 አካባቢ ክፍለ ከተማውን ማቃጠል የሸማቾች የህብረት ሥራ ማህበር ስኳር ዘይትና መሠል ፍጆታዎችን የመዝረፍ ተግባር ፈፅሟል።

ይህ አሻፈረኝ ባይ ፅንፈኛ ሃይል ያልገደለውን ገደልኩ ያልማረከውን ማረኩ ሲል በማህበራዊ ሚዲያ የተለመደውን የሀሠት ወሬ ቢያሠራጭም እውነታው ግን ፅንፈኛ ቡድኑ በለኮሰው እሳት የከተማውን እና የህዝብን ሠላም ለማረጋገጥ ሲባል መከላከያ ሠራዊቱ ሽፍቶቹ ላይ በወሰደው ህግ የማስከበር እርምጃ በርካታ የፅንፈኛ ቡድኑ አመራር አና አባላት ሙትና ቁስለኛ አድርጓል።

በዚህ መሠረት

  1. ክሩቤል ክንዱ መልካሙ 2. መልካሙ አበባው (የተሾመ አበባው ወንድም) 3. እሸቴ (የሀብቴ ምክትል) እና ለጊዜው ስማቸው ያልታወቁ 02 የፅንፈኛው ቡድን አመራሮች መገደላቸውን እና የሟች አመራሮች ቁጥር እየተጣራ ሲሆን ከዚህ በላይ ሊያሻቅብ እንደሚችልና እንዲሁም ሠለሞን አጥናው የተባለውን የሽፍታው ቡድን አባልን ጨምሮ በርካቶች መቁሰላቸውን ከሥፍራው የሚገኘው የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አመራር ገልፀዋል።

የእነኝህን ፅንፈኛ ሃይሎች ፎቶ እንደደረሠን የምናቀረብ መሆኑን ከወዲሁ እንገልፃለን።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት


Leave a Reply