በኦሮሚያ ክልል እስከ መስከረም መጨረሻ ድረስ ከአንድ ነጥብ ሶስት ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች መፈናቀላቸውን CDCB (Center For Development &Capacity Building ) ባወጣው ሪፖርት አስታወቀ።
የቡሳ ጎኖፋን መረጃ ዋቢ አድርጎ በኦሮሚያ ክልል እስከ መስከረም ባለው ጊዜ 1.3 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች መፈናቀላቸውንና ከተመዘገቡት ተፈናቃዮች ውስጥ 859,000 (66%) የሚሆኑት ከምስራቅ ወለጋ እና ምዕራብ ወለጋ ብቻ መሆናቸውን ይጠቅሳል። በመግለጫው የተጠቀሱት ቁጥሮች ምን ያሳያሉ ?
- የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር 1,292,323 መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 29 በመቶው ብቻ (374,448) ወደ መጠለያዎች መድረሳቸውን ያመለክታል። 71 በመቶ (916,606) የሚሆኑት በአካባቢው እና ራቅ ብለው በሚገኙ ማኅበረሰቦች ውስጥ ተበታትነው ይገኛሉ።
- – 739 ትምህርት ቤቶች ከአገልግሎት ውጪ ሆነዋል።
- – ከ210,000 በላይ ህጻናት ከትምህርት ውጪ ሆነዋል።
- – 1,117 መምህራንና የትምህርት ባለሙያዎች ወደ ሥራቸው አልተመለሱም።
- – 208 ጤና ተቋማት ሙሉ በሙሉ ወድመዋል፤ 788 በከፊል ወድመዋል። ( ከእነዚህ ውስጥ 13ቱ ሆስፒታሎች ሲሆኑ የተቀሩት ጤና ጣቢያዎች ናቸው)
በዚህ አጭር መግለጫ በምዕራብ ኦሮሚያ እና መካከለኛው አከባቢ በፌዴራል መንግስት እና በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀው ራሱን የኦሮሞ ሕዝብ ነጻ አውጭ ብሎ በሚጠራውና መንግሥት ” ኦነግ ሸኔ ” የሚለው ታጣቂ ቡድን መካከል የተፈጠረው ግጭት፣ እንዲሁም በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ድንበር ላይ በአማራ ክልል በሚንቀሳቀሰው ” ፋኖ ” በመባል የሚታወቀው ታጣቂ ቡድን ጋር በሚፈጠሩ ግጭቶች ለችግሮቹ መንስዔ መሆናቸውን ይጠቅሳል።
በእነዚህ ግጭቶች በተለይ ሴቶች እና ህጻናት ለአደጋ የተጋለጡ ናቸው ያለው ይህ አጭር መግለጫ እናቶቻቸውን እና አባቶቻቸውን በድንገት የሚያጡ ህፃናት ቁጥር እየጨመረ ነው፤ ባል የሞቱባቸው ሴቶች ለዝርፊያ እና ለ አስገድዶ መድፈር (በፆታ ላይ የተመሰረተ ጥቃት) እና አካላዊ ጥቃት እየተጋለጡ መሆናቸውን ያነሳል።
“በኦሮሚያ ክልል ያለው ግጭት ውስብስብ እና አሳሳቢ ሁኔታን ፈጥሯል። ይሄን ግጭት ለማስቆም ሁሉን አቀፍ ውይይት እና ሰላም ማስፈን ያስፈልጋል። በግጭቱ ወቅት ለተፈናቀሉ እና ችግር ውስጥ ላሉ ዜጎች አስቸኳይ የተቀናጀ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል።” ሲል በCDCB የቀረበው የፓሊሲ ብሪፍ ጠይቋል።
በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ የተዘጋጀውን ሙሉ መግለጫ @tikvahethafaanoromoo ላይ ያገኙታል።
- Ethiopia Working To Secure New Development Bank MembershipThe Ministry of Foreign Affairs disclosed that Ethiopia is working hard to become member of BRICS’ New Development Bank. In… Read more: Ethiopia Working To Secure New Development Bank Membership
- የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ዳግም ዝርፊያ እያፈጸሙ ነው፤ የተማሪዎች መጽሃፍትን “የአማራ ክልል ናቸው እየሉ ቀደዋል”በአላማጣ ከተማ በተለየ መልኩ የትግራይ ክልል ታጣቂዎች በከተማዋ ውስጥ እንደሚንቀሳቀሱ ነዋሪዎች መመስከራቸውን ቢቢሲ አስታወቀ። ይህ የተገለጸው ከአለማጣ እና አካባቢው የተፈናቀሉ… Read more: የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ዳግም ዝርፊያ እያፈጸሙ ነው፤ የተማሪዎች መጽሃፍትን “የአማራ ክልል ናቸው እየሉ ቀደዋል”
- በዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ችግኝ ልትተክል ነውለዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር 6 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል ዕቅድ መያዙንna ለዚህም ተግባራዊነት ከሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊየን በላይ ችግኝ… Read more: በዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ችግኝ ልትተክል ነው
- አፍሪካ ህብረት ” የውጭ ምንዛሪ ሒሳቡን ወደ ሌላ ሀገር ሊያዘዋውር ነው” የሚለው ዜና ሃሰት መሆኑን አረጋግጠአፍሪካ ህብረት የውጭ ምንዛሬ አካውንቱን ወደ ሌላ አገር እንደሚያዘዋውር ተጠቅሶ በህብረቱ ስም የወጣው ዜና ሃሰት፣ ሆን ተብሎ የተቀነባበረ መሆኑን መንግስት… Read more: አፍሪካ ህብረት ” የውጭ ምንዛሪ ሒሳቡን ወደ ሌላ ሀገር ሊያዘዋውር ነው” የሚለው ዜና ሃሰት መሆኑን አረጋግጠ
- አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎችባንኩ የክፍያ ሰነድ ቀረበለት። ማጣሪያ ጥያቄ ለህብረቱ አቀረበ። ሃሰት ሆኖ ተገኘና ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን ያዘ። ጉዳዩ ወደ ህግ አመራ። አሁን ምኑ… Read more: አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎች