በትግራይ ሶስት ልጆቻቸውን ያጡ እናት ትህነግ በይፋ መርዶ ከማወጁ በፊት ህይወታቸው አጠፉ

ትግራይ ውስጥ ተቀስቅሶ ወደ ሌሎች ክልሎች በተስፋፋው የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት “በሺዎች የሚቆጠሩ” የኢትዮጵያ ልጆች ሞተዋል። በመልሶ ማጥቃሩ በተለይ የትግራይ ተዋጊዎች ላይ ክፉኛ ሰብአዊ ጉዳት መድረሱ በየአቅጣጫው ሲገለጽ ቆይቷል። ከሰላም ስምምነቱ በሁዋላ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ቢልም ይህ ከመሆኑ በፊት ሶስት ልጆቻቸውን ያጡ እናት በአሰቃቂ ሁኔታ ራሳቸውን ማጥፋታቸውን ዘጽዓት በሚል ስያሜ የሚታወቀው የትህነግ ደጋፊ በትግርኛ ጽፏል።

ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ከባድ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸውና ዘላቂ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸዉ የክልሉ ባለስልጣናት ማስታወቃቸውን ጠቅሶ የመርዶ አዋጅ እንደሚካሄድ የዘገበው ዶቼ ቨለ ሬድዮ ሬዲዮ ነው።

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር እንዳስታወቀዉ በጦርነቱ ለሞቱ የቀድሞ የትግራይ ሐይሎች አባላት፣ ቤተሰቦቻቸው በቅርቡ በይፋ መርዶ ይነገራቸዋል።

በመቐለ ከተማ የትግራይ የጦር ጉዳተኞች ማእከል ስራ ባስጀመሩበት ወቅት ንግግር ያደረጉ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ሊቀመንበር ጌታቸው ረዳ፣ ቁጥሩን በትክክል ባይጠቅሱም “በሺዎች የሚቆጠሩ” ያልዋቸው የቀድሞ የትግራይ ሐይሎች አባላት በሁለት ዓመቱ ጦርነት መሞታቸውን አረጋግጠዋል። የሟች ቤተሰቦችን ከማርዳት በተጨማሪ መስተዳድራቸዉ ድጋፍ እንደሚያደርግ ጠቁመዋል።

ዘፀዓት በትግርኛ ፅፎት ሌሎች ኢትዮጵያውን እንዲያውቁት የትግርኛውን ጽሁፍ በማያያዝ ወደ አማርኛ በመለሰ ጽሁፍ በርካቶችን ያሳዘነ መረጃ ይፋ ሆኗል። “ሶስት ልጆቼን ካጣሁ እኔ ምን አለኝ” በሚል ነው እኚህ እናት ራሳቸውን በገመድ ያጠፉት። ሙሉውን ትርጉም ያንብቡ

ከሶስት ቀናት በፊት የሶስት ልጆችዋ መርዶ የተነገራት እናት ከደቂቃዎች በኋላ እኔስ ምን አለኝ በማለት ራስዋ በገመድ አጥፍታለች። የስነ ስርአት ቀብርዋ በስንቃጣ አብነቃ የሚባል ቦታ እንደተፈፀመ አረጋግጫለሁ ። ይህቺ እናት የራስዋ እንደባይቃ በድንጋጤ ሓዘን በርትቶ ራስዋ አጥፍታለች ልብ የሚሰብር ነው።

ይህ በስነስርዓት ተነግሮ የሁሉም ብሔራዊ ሓዘን ታውጆ አጥኒ ኮሚቴ ተደርጎ ካልተነገረ የህዝብ ሓዘን ከባድ ይሆናል ። መፅናናትን ለመላው የተሰው ቤተሰቦች

See also  ለአገራዊ የምክክር ኮሚሽን የ42 ተጠቋሚ ዕጩዎች ዝርዝር ይፋ ሆነ

ህይወቱ እንደ እቃ የተጫወቱበት የቀለዱበት የትግራይ ወጣቶች መስዋዕትነት ህዝብ መበደል አልነበረባቸውም ። መስዋዕትነት እንዲህ ርካሽ ማድረግ አልነበረባቸውም ። ቢያንስ በስነስርዓት መናገር ነበረባቸው መድከም አልነበረባቸውም ። መርዶ ለመንገር ገንዘብ መክፈል አልነበረባቸውም ፤ በእውነት ነውር ነው ።

ይህ ታሪክ ልብ ይነካል። ጦርነት ክፉ ነው። ባህላዊ ጨዋታችን ነው ያሉት እነ አሉላ ሰለሞን በውጪ አለም እየተምነሸነሹ ነው። የፃድቃን ልጆች ውጪ ናቸው። አብዛኛው ወያኔ ዘመድ አዝማዱ ውጪ ነው። በጦርነት ሟቹ ግን የደሃ ልጅ ነው። አሁንም የጦርነት አዙሪት ላይ ነን። ያሳዝናል

ይህ አሳዛኝ መረጃ ዛሬ ላይ ለሁሉም ወገን የሚያስተምር ነው። ውጭ አገር ተቀምጠው የደሃ ልጅ የሚማግዱ “በቃችሁ” ሊባሉ ይገባል። እስከመቼ ነው በንጹሃን ደምና ሞት የሚነገደው? የትግራይ ሃዘንና ገጠመኝ ለሌሎች ሁሉ ትምህርት ሊሆን ሲገባ ወደ ሌላ ኪሳራና ሞት መሸጋገር ነገ የሌሎች እናቶች በተመሳሳይ ራሳቸውን ሲያጠፉ፣ በሃዘን ሲቆራመዱ፣ ረጂና ጧሪ አጥተው አመድ ስር ሲንደፋደፉ ከማየት የዘለለ ውጤት አይስገኝም።


Leave a Reply