ከአልሸባብ ሶስት የግድያ ሙከራዎች ተርፈው በቪላ ሶማሊያ በድጋሚ በፕሬዝደንትነት የተመረጡት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ ቀዳሚ አጀንዳቸው ሽብርተኝነትን መዋጋት የሚል ነበር። ሐሰን ሼክ ይህን የገለፁበት መጣጥፋቸው the Economist በተባለው የኒዮ ሊበራሊዝም መፅሔት ታትሞላቸውም ነበር። ሽብርተኝነት ከእስልምና ጋር አይገናኝም ሲሉ በይፋ የገለፁበት ይኸው መጣጥፋቸው ለአለም ተነበባቢ በሆነበት ሳምንት ውስጥ ነበር ታዲያ፣ አልሸባብ የኢትዮጵያን ድንበር ተሻግሮ መንደሮችን ያጠቃው። ለዚያ ጥቃት መነሾ ይሆን ዘንድ "ወኔ የሆናቸው ምን ይሆን?" የሚለውን በተለያዩ አካላት የተሰነዘሩ መላምቶችን በመጨመር ከትላንት እውነቶች ጋር ማገናዘብ እንችላለን።
አልሸባብ የኢትዮጵያን ድንበር ዘልቆ በወቅቱ የሰነዘረው ጥቃት ምን ፖለሂካዊ መነሾ ይኖረዋል የሚለው የበርካቶች ጥያቄ ነበር። የቀድሞው የቪላ ሶማሊያ ደህንነት ዋና ዳይሬክተር መነሻ ሰበብ ነው ያሉት በአዲሱ የሶማሊያ መንግስት ሰርጎ የገባው የአልሸባብ ኔትወርክ አንዱ ነበር። ሐሰን ሼክ ማህሙድም ይህን ድር ማፅዳት አለባቸው ሲሉም በወቅቱ መምከራቸው አይዘነጋም።
ይህን የአልሸባብ ድርጊት ከተለያዩ መላምቶችና በቀደሙት ፖለቲካዊ ክስተቶች መስኮትነት ለመመልከት እንሞክር። “አደጋ ያንዣበበበት የአፍሪካ ቀንድ” የተሰኘው የፕሮፌሰር መስፍን የ2004 እትም መፃሐፋቸው ከገፅ 112 ጀምሮ ከሰፈሩ ታሪኮች ተከታዩን መራረጥኩ..።
.
.
የሶማልያ ታሪክ የማያስደንቅም የሚያሳዝንም ነው፤ በመሠረቱ ሶማልያ ሳይጸነስ የተወለደ አገር ነው) ሶማሊላንድ እኤአ በሰኔ 26 ቀን 195ዐ ከእንግሊዝ ቅኝ አገዛዝ ነጻ ወጥቶ ራሱን ሲችል፤ በደቡብ በኩል የኢጣልያ ቅኝ ግዛት የነበረው ሶማልያም ለአሥር ዓመታት ያህል በኢጣልያ ስር የተባበሩት መንግሥታት የሞግዚት አስተዳደር ሆኖ ቆይቶ ራሱን የመቻል ዕድልን ኢኤአ በሐምሌ 195ዐ ዓም፤ ምንም የመመካከርና የመፈታተን ሙከራ ሳይደረግ ወዲያውኑ ሶማሊላንድና ሶማልያ የውኅደት ስምምነት ተፈራረሙና ሶማልያ የሚባል አገር በአጉል ቀዶ ጥገና ተፈጠረ፤ በእንግሊዝ አስተዳደርና በእንግሊዝ የባህል ተጽእኖ ስር የቆየሁ ሶማሊላንድ፣ በኢጣልያ አገዛዝና በኢጣልያ የባህል ተጽእኖ ስር ከቆየው ሶማልያ ጋር አንድ ላይ ሆነው : ሰማልያ በኋላ ደማዋ በጎሣ ስሜት ተቀዳዶ በመኖርና ባለመኖር መሀከል የሚያቃስት ነገር ሆኖአል፤ ያሳዝናል፣ አጀማመሩ ግን ከብዙ የአፍሪካ አገሮች የተሻለ የሕዝብ ሥልጣን የታየበት ነበር፣ ይህ ያስደንቃል፤
ሶማሊያ ጥሩ አብጦ የመፈንዳት ምሳሌ ነው፣ በአውሮፓ ጀርመን ሌላ አብጦ የመፈንዳት ምሳሌ ነበር፤ የእንግሊዝ ቅኚ ግዛት የነበረው የማሌላንድና የኢጣልያ ሶማሌላንድ ከላይ እንደተገለጸው አዲስ አገር ፈጠሩ፤ ገና መዳህ እንደ ጀመረ እኤአ በ 1963 ከኬንያ የድንበር ጠብ ጀመረ፤ በ1956 ዓ.ም. ኢትዮጵያን በቱግ ውጫሌ በኩል ለመውረር ሞከረ! በጄኔራል አማን የተመራው የኢትዮጵያ ጦር የሶማልያን ጦር አባርሮ በአሜሪካ ተጽእኖ መሆን በሶማልያ ድንበር ላይ ቆሞአል። ይህ ጦርነት የሁለቱ የቀድሞ ቅኝ ግዛቶች የመጀመሪያው የእብጠት መግለጫ ነበር። አንድ በ1956 ዓ.ም. የኢትዮጵያ የጦር ኃይል በምኑም በምኑም ከሶማልያ ጋር የማይወዳደር አገርን የሚያኮራ ነበረ፤ ነገር ግን በጦርነት ሳይንስ የሠለጠኑ ሰዎች ነበሩ ለማለት አያስደፍርም ምክንያቴን ልግለጽ፣ ሶማልያ ኢትዮጵያን የወረረው በቱግ ውጫሌ በኩል ወደ ኢትዮጵያ በመግባት ነበር፤ የጦርነትን ዓላማና ስልት የሚያጠና ሰው ሶማልያ በቱግ ውጫሌ በኩል ወደኢትዮጵያ የገባችው ለምንድን ነው? ብሎ በመጠየቅ መጀመር አለበት፣ ለዚህ ጥያቄ መልሱ ግልጽ ነው፤ የጂጂጋ፣ የሐረርና የድሬ ዳዋ ከተሞች በዚህ መስመር ናቸው፤ በተጨማሪም የባቡር ሀዲዱን ለመቆጣጠር ይህ አቅጣጫ አመቺ ነው ግን ሶማልያ በዚያን ጊዜ በኢትዮጵያ ላይ ይህንን ለማድረግ በፍጹም አትችልም ነበር፤ ታዲያ ለምን ደፈረች? ብሎ መመርመርና ማሰብን የሚፈልገው በትክክለኛ አስተሳሰብ ሲታይ ጦርነት ጭፍን የጥፋት ተልእኮ ብቻ አይደለም፤ መሆንም የለበትም። ጦርነት የፖሊቲካ እንዲኖረው ያስፈልጋል፤ እንግዲህ ስል በተግ ወሌ በኩል ያደረገው ወረራ ፊት ለመያዝ ካልሆነ የፖሊቲካ ዓላማው ምን ነበረ? ትንሽ ምርምር አድርጌ እንደደረስሁበት…።
በዚያን ጊዜ በሰሜን ሶማልያ (የብሪታንያ ሶማሊላንድ) ወጣት መኮንኖች ዓምፀው የመገንጠል ንቅናቄ ጀምረው ነበረ። በዚህ ምክንያት አንድ ብልህ መሪ በቱግ-ውጫሌ በኩል በኢትዮጵያ ላይ የማያዋጣ ጦርነት ከፍቶ በማፈግፈግ የኢትዮጵያ ጦር ተከታትሎ የሰሜኑን የሶማልያ ክፍል እንዲቀጣለት አቅዶ ከሆነስ? የደቡቡ ሶማልያ መሪ ዓላማው ይህ ከነበረ ተሳክቶለታል። ኢትዮጵያ ባለዓየር ኃይል ሆነችና ሀርጌሳን በአውሮጵላን ደበደበች። ስለዚህም ሶማሊያ በጡንቻ ተሸንፎ የፖሊቲካ ዓላማን አሳክቶ ሊሆን ይችላል። እንግዲህ ይህ የመጀመሪያው ሶማልያ ጋና በመዳህ ላይ እያለ የከፈተው ጦርነት ነበር።
…የዚያድ ባሬ አገዛዝ በሀገሬው ህዝብ እየተጠላ በሄደ መጠን ጭካኔውና ማናለብኝነቱ እየከፋ ሄደ። በተቃውሞው ጥንካሬ የተነሣ የጦር ኃይሉንና የፖሊስ ሠራዊቱን እንዲያጠናክርና በዘመናዊ መሣሪያዎች እንዲያስታጥቅ ግድ ሆነበት ለዚህም ዓላማ በቂ መሣሪያ ለማግኘት ሶማልያን ለጨረታ አቀረበ፤ ሶማልያ በደቡብ በኩል ወደቀይ ባሕር መግቢያውንና የህንድ ውቅያኖስን የመርከቦች ጉዞ ለመቆጣጠር አቀማመጡ የተመቸ ነው። ሶማልያን በፖሊቲካ ሽርክና ለማጠናከር እአአ በ1974 የአረብ ማኅበር አባል ሆነ፤ በተጨማሪ ሶማልያ በሕንድ ውቅያኖስ ላይ ረጅም የባሕር ጠረፍ ሌላው የአቀማመጥ ጥቅም ነው፤ ሶማልያ ለጨረታ ያቀረበው እነዚህን ጥቅሞች ነበር፤ ጊዜውም የአሜሪካና የሶቭየት ኅብረት በከፋ ውድድር ተወጥረው የነበረበትና አሜሪካ በኢትዮጵያ (ኤርትራን ጨምሮ) ላይ ሙሉ ተጽእኖ ያሳደረበት ነበር። ስለዚህም በኢትዮጵያ ውስጥ በፖሊቲካና በጦር መሣሪያ ጫና ተጠናክሮ የደረጀውን አሜሪካ ለመቋቋም ሶቭየት ኅብረት ሶማልያን በጣም በማስታጠቅ በጦር ኃይል ከአካባቢው የበለጠ አገር አደረገው።
በስዒረ-መንግሥት 1969እኤአ ስልጣን የጨበጠው ጄኔራል ዚያድ ባሬ ከጀርመን ናዚዎች ባገኙት የተውሶ ምኞት ሶማሌዎች የሚኖሩበት መሬት ሁሉ የሶማሊያ ነው ብሎ አወጀ። በዚህም መሰረት ከጂቡቲ ቢያንስ ግማሹን፣ ከኬኒያ የሰሜኑን ክፍል እንዲሁም ከኢትዮጵያ ኦጋዴንን ወደ ሶማሊያ ግዛት ለማስገባት የአገር መመሪያ አደረጉት።
የውስጥ ችግሩን በአፈና ከአስተካከለ በኌላ ጡንቻውን ወደ ኢትዮጵያ አዞረ። ይህም ሶማልያ በራሷ ለሁለተኛ ጊዜ ወረራ መጀመሩ ሲሆን፤ ደርግ በኢትዮጵያ መጠላት የጀመረበት ጊዜ ነበር። እንዲሁም ደርግ በሰሜን የሻቢያና የወያኔ ዓመጸኞች የተጠናከረ ጦርነት ከፍተው ነበር። በምዕራብ በኩል ደግሞ ኢዴኅ (የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኅብረት ወይም ኢዲዩ) የሚባለው የደርግ ተቃዋሚ ድርጅት ጦርነት ጀምሮ ነበር፤ እንግዲህ በሶማልያ በኩል የተከፈተው አራተኛ የጦር ግንባር ነበር።
በዚህም የተነሣ የሶማልያ ጦር በአሥር ቀኖች ውስጥ በ1977 ዓ.ም ጂጂጋን ለመቆጠር በታ ከኢጣልያ ወሪራ በኋላ ኢትዮጵያ ውርደትን የተከናነበችበት ጊዜ ነበር፤ በአንዲት ትንሽ አገር ተደፍራ ሰፊ የሆነ መሬት ለጥቂት ጊዜም ቢሆን በሶማልያ ቁጥጥር ስር የሆነበት..።
የዓባይ፡ልጅ