በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ 120 ሽፍቶች በሠላማዊ መንገድ እጃቸውን በመተከል ዞን ለተቋቋመው የተቀናጀው ግብረ ኃይል እጃቸውን ሰጡ።

በጫካ የነበሩ የሽፍታው ቡድን አባላት በሠላማዊ መንገድ እንዲገቡ፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የመከላከያ መረጃ ዋና መምሪያ እንዲሁም ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት በጋራ እንደሰሩ ተገልጿል።

በጫካ ሽፍቶችን ሲመራ የነበረው ላቀው ደረጄ እና አዲሱ ፈጠነ በሰጡት አስተያዬት፣ የህወሓት ቡድኑ መቀሌ በመጥራት ሲያሰለጥናቸው እንደነበረ ተናግረው፣ አሁን ግን በአካባቢያቸው በተጀመረው የሠላም እና የልማት እንቅስቃሴ ተጠቃሚ ለመሆን እጃቸውን መስጠታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

EBC

    Leave a Reply