ፕሮስቴት እጢ በወንዶች ፊኛ በታች የሚገኝ ተፈጥሯዊ የሰውነት አካል ነው ፡፡
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ዩሮሎጂ ትምህርት ክፍል ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር መሀመድ አብዱልሀዚዝ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ ÷የፕሮስቴት እጢ ዋነኛ ተግባር የዘር ፈሳሽ በማመንጨት ወደ ፊት ለፊት እንዲወጣ በማገዝ ለመራቢያነት ማገልገል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
የበሽታው መንስኤ ብለን የምንጠራቸው ምክንያቶች አብዛኛዎቹ ተፈጥሯዊ መሆናቸውንም ነው በቆይታቸው የገለጹት፡፡
እጢው በወንዶች ላይ ብቻ የሚገኝ እንደመሆኑ መንስኤው በጾታ ወንድ መሆን ሲሆን÷ እጢው ሊያድግ የሚችልባቸው ጊዚያቶችም አንደኛው ምክንያት አንድ ወንድ ለአቅመ አዳም ሲደርስ መሆኑን እና ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ እድሜው በ50ቹ የእድሜ ክልል ውስጥ ሲገባ ነው ይላሉ፡፡
ሌላኛው መንስኤ ቤተሰብ ውስጥ በፕሮስቴት እጢ ምክንያት የጤና ችግር ያጋጠመው የቤተሰብ አባል ሲኖርም በዘር ምክንያት የመጋለጥ እድል እንደሚኖረውም ያነሳሉ፡፡
በተጨማሪም÷ አንድ በጾታ ወንድ የሆነ ሰው የስኳር ፣የደም ግፊት፣የኮሌስትሮል መብዛትና የክብደት ከመጠን በላይ መጨመር ካለ ተጋላጭነቱ ሊሰፋ እንደሚችል ገልጸዋል፡፡
የእጢው እድገት ችግር ላያመጣ የሚችልበት አጋጣሚ ብዙ ቢሆንም አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የጤና ችግር በሚፈጥር መልኩ የሚያስቸግርበት አጋጣሚ እንደሚፈጠር ይጠቅሳሉ፡፡
የጤና ችግር የሚፈጠርበት ምክንያት የእጢው መገኛ የሽንት ፊኛ አንገት ላይ በመሆኑ የእጢው ማደግ ቀጥታ ከመሽናት ችግር ጋር ሊያያዝ ስለሚችል እንደሆነም ያስረዳሉ፡፡
የፕሮስቴት እጢ ምክንያት የሚመጣው የጤና ችግር የሚከተሉትን ምልክቶች እንዳሉት የሚገልጹት ዶ/ር መሀመድ ሽንት ለማጠራቀም መቸገር (ቶሎ ቶሎ መሽናት)፣ሲሸኑ የማቃጠል ስሜት መሰማት፣ለመሽናት መቸገር ፣ሽንት በደምብ ያለመፍሰስ፣ የሽንት መቆራረጥ የመሳሰሉት በዋነኝነት እንደሚጠቀሱ ገልጸዋል፡፡
የፕሮስቴት እጢ ቀላልና ከባድ ህመሞች የሚያስከትል ሲሆን÷ እንደ ችግሩ ሁኔታ መፍትሔውም የሚለያይ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡
ቀለል ያሉ የፕሮስቴት እጢ ችግሮች በምክርና በክትትል ሊሻሻሉ የሚችሉ እንደሆኑ የሚገልጹት ዶ/ር መሀመድ ከበድ ያሉት ደግሞ የህክምና እገዛ የሚፈልጉ ማለትም በመድሃኒትና በቀዶ ጥገና ጭምር የሚታገዙ እንደሆኑ ያነሳሉ፡፡
እጢው ከበድ ያለ ህመም ወደ ማስከተል ደረጃ ደርሶ የህክምና ክትትል ካልተደረገ ግን እንደ የኩላሊት ስራ ማቆምና ወደ ሌሎች ውስብስብ ችግሮች ሊያመራ ስለሚችል ከላይ የተጠቀሱትን የህመሙ ምልክቶች የሚያሳይና በተለይ ደግሞ እድሜው በ50ቹ የእድሜ ደረጃ ላይ ያለ ወንድ የጤና ባለሙያ ሊያየው እንደሚገባም ይመክራሉ፡፡
FBC
- የባህር ወንበዴ ሲሳዮች – በገሃነም የሚመሰለው ስቃይየ34 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ ከአውሮፕላኑ ሲወርድ እግሮቹ ቆስለው መራመድም ሆነ መቆም አቅተውታል። ብርክ ይዞት ይንገዳገዳል፡፡ ይህ ሰው የተሻለ ህይወት ይኖረናል ብለው በሕገ ወጥ መንገድ… Read more: የባህር ወንበዴ ሲሳዮች – በገሃነም የሚመሰለው ስቃይ
- የህፃናት የደም ካንሰር አይነቶች፣ ምልክቶችና ህክምናዎችየተለያዩ የደም ካንሰር አይነቶች ያሉ ሲሆን በዋናነት ብዙ ጊዜ በህፃናት ላይ በመከሰት የሚታወቀው ‘አኪውት ሊምፎብላስቲክ ሉኪሚያ’ ነው። ሁለተኛው በህፃናት ላይ የሚከሰት የደም ካንሰር… Read more: የህፃናት የደም ካንሰር አይነቶች፣ ምልክቶችና ህክምናዎች
- የቶንሲል ህመም ምንነትየቶንሲል በሽታ በጉሮሮ የኋላ ክፍል ላይ ያሉ ሁለት የጅምላ ቲሹዎች የሚከሰት ሆኖ በሕጻናት ላይ በስፋት የሚታይ ነው፡፡ ህመሙ አንዴ ከያዘና በትክክል ሕክምና ካልተደረገለት… Read more: የቶንሲል ህመም ምንነት
- የሪህ በሽታ ምንድን ነው?በዓላትን ተገን አድርገዉ ከሚከሰቱ በሽታዎች መካከል አንደኛዉ ሪህ ሲሆን በበዓላት ወቅት ከአመጋገባችን ጋር በተያያዘ የሚከሰት ነዉ፡፡ በሽታው ከበዓላት መምጣት ጋር ተያይዞ በብዛት ቢስተዋልም… Read more: የሪህ በሽታ ምንድን ነው?
- በትግራይ ክልል ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች እህልና አልሚ ምግብ እየተጓጓዘ ነውበትግራይ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ከ23 ሺ ኩንታል በላይ እህልና አልሚ ምግብ እየተጓጓዘ መሆኑን የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታወቀ። ኮሚሽኑ ወደ ትግራይ… Read more: በትግራይ ክልል ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች እህልና አልሚ ምግብ እየተጓጓዘ ነው