የጎንደር ከተማን በተለያዩ አቅጣጫዎች ለማጥቃት ተኩስ ከፍተው የነበሩ ታጣቂዎች በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች መመለሳቸውን የጎንደር ከተማ ወጣቶችና የከተማ አስተዳደሩ ዐስታወቁ።
ታጣቂዎቹ ከትናንት በስትያና ትናንት የጎንደር ከተማን የሽብር ማዕከል ለማድረግ በሦስት አቅጣጫዎች ተኩስ ከፍተው ጉዳት ማድረሳቸውን በጎንደር የአማራ ወጣቶች ማኅበር ፕሬዚደንት ተስፋ ታምራት ለዶይቼ ቬለ ተናግሯል። «ጎንደርን የሽብር ቀጠና ለማድረግ ሥራ ተሠርቶ ነበር። ድንበር አካባቢ ሰው በማገት እየተደራደሩ ገንዘብ ሲቀበሉ ቆዩ።
አሁን ደግሞ በሕዝብ ላይ ግልጽ የኾነ ጦርነት ከፍተው በአማራ ልዩ ኃይል እና ሚሊሺያ እንዲሁም የአካባቢው የፀጥታ ኃይል ሕልማቸው አልተሳካላቸውም። አሁን ዛሬ ነው፤ ጥሩ ሠላም ነው።»የጎንደር ከተማ የሰላምና ደህንነት መምሪያ ኃላፊ አቶ ናትናኤል ጎሹ በበኩላቸው በስም ያልጠቀሷቸውና «የተደራጁ ቡድኖች» ያሏቸው ኃይሎች በሦስት የጎንደር ከተማ አቅጣጫዎች ጥቃት ከፍተው በመንግሥት ታጣቂዎች መመለሳቸውን አብራርተዋል።
«አንደኛው ቁስቋም ይባላል፣ አንዱ ብላጅግ ዳብርቃ ነው፣ ሌላኛው ደግሞ አዘዞ ሳይድ (አቅጣጫ)፣ በእነዚህ ሦስቱ ቦታዎች፣ ያው ቁስቋም ትንሽ ጠንከር ያለ ነበር። በርከት ያለ የጥፋት ኃይል ገብቶ ከተማውን የማጥቃት ፍላጎት ነበረው። ይህን ያህል ሕይወት ጠፋና ይህን ያህል ቆሰለ ምናምን እንደዚህ የምጠቅሰው ነገር አይኖረኝም፣ ግን የተቃጠሉ ቤቶች አሉ ዳር ወጣ ወጣ ብለው ያሉ።
ድርጊቱን የፈፀመውን ሰው በክትትል አንዳንዶቹን በቁጥጥር ስር አውለናል፤ ክትትል እያደረግን ነው።»በነበረው የተኩስ ልውውጥ ምን ያህል ጉዳት እንደደረሰና የታጣቂዎችን ማንነት በተመለከተ ዶይቼ ቬለ የጠየቃቸው አቶ ናትናኤል «በጥናት ይመለሳል» የሚል ጥቅል ምላሽ ሰጥተዋል። አሁን የጎንደር ከተማና አካባቢው ሰላም እንደሆነ መምሪያ ኃላፊው ማመልከታቸውን የባሕርዳሩ ወኪላችን ዓለምነው መኮንን የላከልን ዜና ይጠቁማል።
DW Amharic
- አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎችባንኩ የክፍያ ሰነድ ቀረበለት። ማጣሪያ ጥያቄ ለህብረቱ አቀረበ። ሃሰት ሆኖ ተገኘና ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን ያዘ።… Read more: አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎች
- የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል 300 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ዕዳ አለብኝ አለ፤ ዕዳውና የክፍያው ጫና እንደከበደውም አስታውቋልየኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከንግድ ባንክ 300 ቢሊዮን ብር ዕዳ እንዳለበት ተገለጸ። የዕዳ ጫናውን ለማቃለል… Read more: የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል 300 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ዕዳ አለብኝ አለ፤ ዕዳውና የክፍያው ጫና እንደከበደውም አስታውቋል
- ዋና ዋና የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ይዘቶች – ሲጨመቁመግቢያ ሽግግር ፍትህ ጉልህ የመብት ጥሰቶች በተፈፀመባቸው ሀገራት ተጠያቂነትን ለማስፈን እና ተበዳዮችን ለመካስ ጥቅም… Read more: ዋና ዋና የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ይዘቶች – ሲጨመቁ
- “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”“የሚሊሻ ኀይሉን በተመለከተ የሚዘዋወረው መረጃ ፍጹም መሠረተ ቢስ ነው” ሲሉ ኮሎኔል ግርማ ገሰሰ አስታወቁ።… Read more: “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”
- “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን“የትግራይ ተወላጆች ትህነግ ለፈጸመው ወረራ፣ ዘረፋ፣ ማፈናቀልና የግድያ ተግባራት የተቀናጀ የፖለቲካና የሚዲያ ድጋፍ ሰጥተዋል።… Read more: “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን