አርቲስት አብርሃም ከተደበቀበት በህዝብ ጥቆማ ተያዘ – በርካታ ከአዲስ አበባና ተምቤን እየተያዙ ነው


አርቲስቲ አብርሃም ገብረመድህን ዛሬ አመሻሽ ላይ ከተደበቀበት ቦታ በመከላከያ ሰራዊት በቁጥጥር ስር እንደዋለ ተሰምቷል። ገብረ መድህን የተያዘው ከተደበቀበት በጥቆማ ሊያዝ ሲል ለማምለጥ ሞክሮ ነበር። ይሁን እንጂ በጥቆማው መሰረት ስፍራውን የወጠረው የመከላከያ ልዩ ኮማንዶ አሯሩጦ እነደይዛወ ነው የተሰማው።

“ከህዝብ የሚሰወር ማንም ጁንታ እና የጁንታ ደጋፊ የለም” ሲል ነዋሪዎችን ጠቅሶ ግዕዝ ሚዲያ ዜናውን ለማወጅ ቀዳሚ ሆኖኗል። “የትግራይ ህዝብ ጁንታዎቹ አሳልፎ እየሰጠ ይገኛል” ሲልም አክሏል።

በስም አይጠቀስ እንጂ ሰሞኑንን በርካታ መያዛቸውና እጅ መስተታቸው ተገልጿል። ይህን ካተምን በሁዋላ በደረሰን ዜና አዲስ አበባ የትህነግ የጫካ ሃይል የህክምና መሳሪያና መድሃኒቶችን ሲልኩና ሲያዘጋጁ የነበሩ፣ ከአዲስ አበባ ወደ በረሃ የሄዱና ተንቤን በየመኖሪያ ቤት ተመሽገው የነበሩ አሁን እየተያዙ መሆኑ ታውቋል።

አዲስ አበባ ላይ የተያዙት የሚጠቀሙት የውጭ አገር የስልክ መስመር በዋትስ አፐንደሆእ የትግራዮቹ ደግሞ የሱዳንና የአሜሪካ ሲም እንደሚጠቀሙ ለማወቅ ወሬውን ያደርሱ ነግረውናል።

Leave a Reply

%d bloggers like this: