በመቀበር ላይ የሚገኘውን አሸባሪው ህወሓትን ለመታደግ የተካሄደው ምሥጢራዊ ስብሰባ ተጋለጠ

አሸባሪው ህወሓትን ከሚቀበርበት ጉድጓድ ለመታደግ የሽብር ቡድኑ አባላትና ምዕራባውያን የጥቅም አጋሮቹ ዲፕሎማቶች ያካሄዱት ምሥጢራዊ ስብሰባ ተጋልጧል።

ብርሃነ ገብረ ክርስቶስና ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሐቅን ጨምሮ የአሸባሪዎቹ ህወሃትና ሸኔ የውጭ አመራሮች፤ እንዲሁም የጥቅም አጋሮቻቸው ምዕራባውያንና ዳያስፖራዎች ወደ መቃብራቸው እየተሸኙ ያሉትን የሽብር ቡድኖች ለማዳን ድብቅ ምክክር አካሂደዋል።

ከዚህ በተጨማሪ በሶማሊያ የአሜሪካ አምባሳደር ዶናልድ ያማሞቶ እና የቀድሞ የአሜሪካ የመከላከያ የአፍራካ ጉዳዮች ምክትል ሀላፊ ቪኪ ኹደልስተን፣ የአውሮፓና የእንግሊዝ ዲፕሎማቶች ወደ መቃብራቸው እየተሸኙ ያሉትን የሽብር ቡድኖች ለማዳን በስብሰባው ከተሳተፉት መካከል ናቸው።

በዚህ ምሥጢራዊ ስብሰባ “በአሁኑ ወቅት የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መንግስትን ልናስቆመው አንችልም የአፍሪካ ህብረት የወከላቸው የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዚዳንትም ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ እኛ እንደምንፈልገው አልተንቀሳቀሱም” ማለታቸው ታውቋል።

እንደምንም ብለን አሁን በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ያለውን መንግስት በማውረድ የምንፈልገውን የሽግግር መንግስት ማቋቋም ይኖርብናልም ሲሉም ነው የዶለቱት፡፡

በድርድርም ሆነ በየትኛውም ሁኔታ የአሸባሪውን ህወሓትና የጥቅም አጋሮቹን ፍላጎት የሚያስፈጽም መንግስት መቋቋም እንዳለበት የተነሳ ሲሆን ይህንንም ለማሳካት የሰብአዊ ድጋፍ ሰጪ ድርጅቶችን ጨምሮ ሌሎች አካላትን መጠቀም ይጠበቅበናል ሲሉ ከንቱ ዕቅዳቸውን አቅርበዋል።

በሌላ በኩል አሸባሪውን ቡድን ወደ ስልጣን ለመመለስ እንደ ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሐቅ ያሉ ታዋቂ ግለሰቦች አሸባሪውን የሚደግፉ የአሜሪካ ባለስልጣናትን የማግባባት ሥራ ከመጋረጃ ጀርባ እያከናወኑ መሆኑም በዚህ ምሥጢራዊ ስብሰባ ተዳሷል።

አሸባሪውን ቡድን ወደ አዲስ አበባ ለማስገባት በዲፕሎማሲው መስክ ጫና ለማሳደር መንቀሳቀስ እንደሚገባም በሚስጢር መዶለታቸው ተረጋግጧል።

(ኢዜአ)

Related posts:

መንግስ የጸጥታ ሃይሎች ለየትኛውም ዓይነት ትንኮሳ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ማድረጉን አስታወቀ
በትግራይ 5.2 ሚሊዮን ሕዝብ ዕርዳታ እየደረሰ ነው፤ ከሺህ በላይ የጭነት መኪኖች ታግተዋል፤ 76 ቢሊዮን ብር ወደ ትግራይ ተልኳል
የደህንነት ጥናት አዲሱ ምዕራፍ - ጂኦስፓሻል ኢንተለጀንስ
ዳግም ጦርነት እንዳይጀመር ስጋት የገባው ኢሰመኮ የማስጠንቀቂያ ጥሪ አሰማ
"ህሊናን የሚፈታተን" የተባለ ሪፖርት ይፋ ሆነ - አማራ ክልል በተወረረበት ወቅት ግብረርሰዶም መፈጸሙ ተገለጸ
ፊንላንድ 3.6 ሚሊዮን ሕዝብ የሚይዙ ዋሻዎች አዘጋጀች - ለኢትዮጵያውያን ጠቃሚ የጥንቃቄ መረጃ
"አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድንና የጥፋት ኃይል ዳግም ከሞከረ የማያዳግም ቅጣት ይጠብቀዋልʺ
ሻዕቢያና ትህነግ - ሰሞኑን ይህ ሆነ
ትህነግ ጦርነት እንደሚከፍት ይፋ አደረገ፤ አማራ ክልል "ለክተት ተዘጋጁ"አለ፤ መከላከያ በተጠንቀቅ ላይ ነው
ወልቃይት "የወር ስንቅህን አዘጋጅተህ ለክትተ ጥሪ ተዘጋጅ”
በሶማሊያ በሚንቀሳቀሰው አልሸባብ የሽብር ተልዕኮ የተሰጣቸው ስድስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
አማራ ክልል ትህነግ ዳግም ጦርነት ስላወጀ የ"ዝግጁነትን" አዋጅ አወጣ
ኡጋንዳ ፀረ-ኢትዮጵያ ለሆኑ ሃይሎች ከለላና ድጋፍ እንደማታደርግ አስታወቀች፤ የሚወራው ሃሰት ነው አለች
በአገር አቋራጭ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ ተደረገ
በዳኝነት ስርአቱ ላይ የሚታዩ የሙስና ተግባራትን ለመከላከል የሚያስችል ስትራቴጂ ይፋ ሆነ

Leave a Reply