አሳርፉልን! የመጨረሻ መልዕክት

በጌታቸው ሽፈራው

ታሪካዊቷ ጎንደር ያለ ስሟ ስም ተሰጥቷታል። ችግሮች ያልተፈጠሩበት አካባቢ የለም። ችግር ፈጣሪዎቹ እንጅ አካባቢና ሕዝብ ሲወገዝ አይኖርም። ሆን ብሎ በተቀነባበረ ሴራ የደረሰን ችግር ለጎንደርና ለአማራ ሕዝብ ስም ማጥፊያ፣ ለአማራ ሙስሊምና ክርስትያን መካከል ያለውን ግንኙነት ለመበጠስ፣ በሌሎች አካባቢዎች ግጭት ለመቀስቀሽ ከአሸባሪው ትህነግ ጋር ሆነው የሚሰሩት ፅንፈኞች ተግባራቸው ቀጥሏል።

በይፋ በሚዲያ፣ በአደባባይ የከተማና የክልል ስም እየተጠራ፣ የአማራ ሕዝብ ያለ ስሙ ስም እየተሰጠው፣ እንደ ቱርክ ያሉ አገራት መግለጫ እስኪሰጡብን ድረስ የሀሰት ፕሮፖጋንዳው ቀጥሏል።

መንግስት ይህን በአማራ ሕዝብ ላይ የተከፈተ፣ ለውጭና ለአገር ውስጥ ጠላቶቻችን አጋልጦ የሚሰጠንን የፕሮፖጋንዳ ጥቃት በአስቸዃይ ያስቁም!

የእምነት አባቶች የጎንደሩን ክስተት ተከትሎ በፅንፈኞች በኩል የሚደረጉ የሀሰትና ከጠላት ውጭ ለማንም የማይጠቅሙ የሀሰት ዘመቻዎችንና የፕሮፖጋንዳ ጥቃቶችን ያስቁሙ!

ይህ የማይሆን ከሆነ ችግር እንዳይባባስ ብለን ያስቀመጥናቸውን በእጃችን ላይ ያሉትን መረጃዎች ለመልቀቅ እንደምንገደድ መግለፅ እንወዳለን።

የጎንደር ሙስሊሞች በዓል እንዳያከብሩና ጎንደርንና አማራን ለማጥቃት ዕቅድ የያዙ ፅንፈኞች አሁንም የጎንደርንና የአማራውን ስም ያለ አግባብ እያጠለሹ እየቀጠሉ ነው። ይህ በአስቸኳይ ካልቆመ ለችግሩ መነሻና መባባስ የዳረጉት እነማን እንደሆኑ የሚያሳዩ መረጃዎቻችን ለሕዝብ የምናደርስ ይሆናል።

ጽሁፉ የጸሃፊው አመለካከት ብቻ የሚወክል ነው – ዝግጅት ክፍሉ

Leave a Reply