“እናቴ ፍጹም እስር ቤት እንድትገባ አልፈግም” ብሎ እግሩን ያጣው ወጣት ምስክርነት ለሮይተርስ

Filimon, 18, a captured fighter from the Tigray People's Liberation Front (TPLF), sits in a guarded hospital room in Dubti Referral Hospital, Afar region, Ethiopia February 24, 2022. Picture taken February 24, 2022. REUTERS/Tiksa Negeri

“እናቴ ፍጹም እንድትታሰር አልፈልግም” ሲል ቃሉን ለሮይተርስ የሰጠው ወጣት አንድ እግሩን አጥቷል። ህክምና የተደረገበትም ዱብቲ ሆስፒታል ነው። አሁንም እዛው ነው። ሮይተርስ በምስል አስደግፎ ያሰፈረው ዘገባ በትግራይ ክልል አስገዳጅ የውትድርና ምልመላው ተጠናክሮ መቀጠሉን በበርካታ ምስክሮች አስደግፎ ያሳየ ነው። ኢዜአ እንዲህ ተርጉሞታል።

በትግራይ ክልል ዕድሜና ጾታ ያልገደበው አስገዳጅ የውትድርና ምልመላ ተጠናክሮ መቀጠሉን ሮይተርስ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ገለጹ። ልጆቻቸውን ወደ ውትድርና ማሰልጠኛ ጣቢያዎች የማይልኩ ወላጆች ለእስር እንደሚዳረጉም ዘገባው አመልክቷል።

ካለፈው የካቲት ወር ጀምሮ በደርዘን የሚቆጠሩ ነዋሪዎችና የረድኤት ድርጅት ሰራተኞችን ቃለ መጠይቅ ያደረገው ሮይተርስ፤ በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት የሌለው የግዳጅ የውትድርና ምልመላው ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጿል።

በሰሜን ምዕራብ ትግራይ እንዳባጉና ከተባለው መንደሩ በግዳጅ ተመልምሎ ወደ ውትድርና የተቀላቀለው የ18 ዓመቱ ወጣት አላዩ እንደገለጸው፤ ወላጆች ልጆቻቸውን ለጦርነቱ ካላቀረቡ ከ10 እስከ 20 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣትና እስር ይጠብቃቸዋል።

በጭፍራ በነበረው ከባድ ውጊያ እግሩን በመትረየስ በመመታቱ ለእድሜ ልክ የአካል ጉዳት መጋለጡን የተናገረው አላዩ በአፋር ክልል በሚገኘው ዱብቲ ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገለት መሆኑንም ገልጿል።

“እናቴ በፍጹም እስር ቤት እንድትገባ አልፈልግም” በሚል በግዴታ የውትድርና ምልመላው ውስጥ በመካተት ወደ ጦርነቱ መላኩን የተናገረው ደግሞ ሌላው ታዳጊ የመቀሌ ከተማ ነዋሪ የነበረው ጊልሞን ነው።


“I DIDN’T WANT MY MUM TO GO TO JAIL”

“I joined. I didn’t want my mum to go to jail, ”said Filmon, receiving treatment after losing his left leg in an ambush. He said he lay injured for nine days – surviving on a few biscuits in his pockets and river water – before a farmer handed him over to the Ethiopian military, who treated him in a military makeshift hospital. His medical records say his leg had gangrene and so it was amputated.


በግራ እግሩ ላይ በደረሰበት የመቁሰል አደጋ በዱብቲ ሆስፒታል ህክምና እየተከታተለ የሚገኘው ወጣቱ በጦርነቱ ቆስሎ በመከላከያ ሰራዊት ከመያዙና ለህክምና ከመድረሱ በፊት በጥቂት ብስኩትና ውሃ እራሱን ለማቆየት ያደረገው ትግል ፈታኝ እንደነበረ ያስታውሳል።

ትግራይ ውስጥ ባለው ጠንካራ የአፈና መዋቅር ምክንያት በእያንዳንዱ የክልሉ መንደር ያሉ ሰዎች ላይ ክትትል እንደሚደረግ መስክሯል።

በመኖሪያ መንደሩ ማንነታቸውን ያላወቃቸው አፋኞች ወላጆቹ ልጃቸውን ካላዘመቱ ከ10 እስከ 20 ሺህ ብር እንዲከፍሉ ካልሆነ ደግሞ እንደሚታሰሩ ስለተነገራቸው የተባለው ገንዘብ የመክፈል አቅም የሌላቸው በመሆኑ ለመዝመት መገደዱን ተናግሯል።

በጭፍራ በነበረው ከባድ ውጊያ እግሩን በመትረየስ በመመታቱ ለእድሜ ልክ የአካል ጉዳት አጋጥሞት በአፋር ክልል ዱብቲ ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገለት መሆኑን ገልጿል።

“ጥንብ አንሳዎች የጓደኛህን ሙት ገላ ሲበሉት ስለሚያሳይህ ጦርነት መጥፎ ነው” ያለው ፊልሞን አካሉ፤ ዱብቲ ሆስፒታል ቢሆንም በህወሃት ሃይሎች ስለሚንገላቱት ቤተሰቦቹና ዘመዶቹ ማሰቡን አላቆመም።

ባለፈው ጥር ተበትኖ የነበረ አንድ በራሪ ወረቀት እንደሚያመለክተው ሁሉም ነዋሪ ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋማት በመቅረብ እንዲመለመልና መደበቅ የማይቻል መሆኑን ያረጋግጣል።

ራሱን የትግራይ የውጭ ግንኙነት ቢሮ ሃላፊ ያደረገው ክንደያ ገብረህይወት ህወሃት ልጆቻቸውን የማያዘምቱ ሰዎች ይታሰሩ የሚል አሰራር ከፍተኛ አመራሩ ውስጥ የሌለ መሆኑን በመግለጽ “የወረዳና የቀበሌ አመራሮች ያሰሯቸው ጥቂት ወላጆች እንዲፈቱ አድርገናል” ቢልም የሚመጡት መረጃዎች ይሄንን አያሳዩም ብሏል ሮይተርስ በዘገባው።

Leave a Reply