«ኢትዮዽያን ማስቀጠል ከሚፈልጉት ጎን በመሆናችን የሚከፋ ከአለ እርሱ መፍረሷን የሚናፍቅ ብቻ ነው!»

“ኢትዮዽያን ማስቀጠል ከሚፈልጉት ጎን በመሆናችን የሚከፋ ከአለ እርሱ መፍረሷን የሚናፍቅ ብቻ ነው!” ጄ/ል ስብሃት ኤፍሬም :- የኤርትራ መከላከያ እና ማዕድን ሚኒስቴር

“የኢትዮዽያ መፍረስ ቀድሞ የሚጎዳት ኤርትራን ነው! እኛም ይህንን በመረዳታችን በኢትዮዽያ መቀጠል የማያወላውል አቋም ያላቸውን ወጣቶች ያለንን ወታደራዊ ክህሎት ለማካፈል ፈቃደኛ በመሆናችን የሚከፋ ከአለ የኢትዮዽያን መፍረስ የሚናፍቅ ብቻ ነው።

ከጥንት ጀምሮ ‘በኢትዮዽያ መቀጠል የማያወላውል አቋም አለው’ ተብሎ ከሚታመንባቸው ብሔሮች መካከል ግንባር ቀደሙ «የአማራ» ብሔር ነው።

ከነፃነት ኤርትራ በፊት በትጥቅ ትግሉ ወቅት የአማራ ብሄር አባል የሆነ ወይም በእናቱ ወይም በአባቱ የአማራ ዘር ያለበት ኤርትራዊ ሳይቀር የኤርትራን ከኢትዮዽያ መለየት ፈጽሞ የማይቀበለው መሆኑን ስለተገነዘብን ለትግሉ ውጤታማነት ሲባል #በአማራ ህዝብ ላይ ብዙ የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ሰርተናል። በወቅቱ ትግሉን ውጤታማ ከደረጉልን ቁልፍ ስልቶች መካከል አንዱ ነበር።

ሆኖም ግን በቅርቡ ሁለቱ ሀገራት በዶ/ር አብይ ምክንያት ዳግም ሲገናኙ በመጀመርያ በአፋጣኝ ኢንዲታረም ያደረግነው ፤ ለትግሉ ስኬታማነት ለሰራነው የሃሰት ፕሮፓጋንዳ በይፋ ይቅርታ መጠየቅና «አማርኛ» ቋንቋ ኤርትራ ውስጥ በሚገኙት ትምህርት ቤቶች በሙሉ እንደ አንድ የትምህርት አይነት እንዲሰጥ መወሰን ነበር፤ ተግባራዊ አድርገነዋል።

በመሆኑም አሁን በወያኔ የሽብር ድርጊት በቀጠናው በተከሰተው የሰላም መደፍረስ ምክንያት በተለይም ሱዳን፣ ኢትዮዽያንና ኤርትራን በሚያዋስነው ድንበር አካባቢ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ከኢትዮዽያ ጋር ከሚያዋስነን የአማራ ክልል ህዝብ ጋር በመተጋገዝና በመረዳዳት እየሰራን ነው።

የእኛ እቅድ የቀጠናውን ሰላም በጋራ ለመጠበቅ በአዋሳኝ ከሚገኘው ከአማራ ክልል የፀጥታ አካላት ጋር በመተጋገዝ በሱዳን ኮሪደር የሚገቡ ማናቸውንም ፀረ-ሰላም የውጭ ኃይሎች መከላከል እንጁ በኢትዮዽያ የውስጥ ጉዳይ ፈጽሞ መግባት አይደለም።

ይህንን ተግባራዊ ስናደርግ በወያኔ ስርአት በሴራ ፖለቲካ ተጠልፎ የተዳከመውን የአማራ የፀጥታ አካላትን ወታደራዊ ክህሎታችንን እና ልምዳችንን በማካፈል በቀጠናው ጠንካራ አቋም ያለው አንድነት መፍጠር ወሳኝ ጉዳይ በመሆኑ፤ ለኢትዮዽያ ቀጣይነት የማያወላውል አቋም ያላቸውን የአማራ ወጣቶች ፈቃደኛ እስከሆኑ ድረስ በአሉበት ስፍራ ወይም ወደ ኤርትራ በመምጣት ወታደራዊ ክህሎት እንዲኖራቸው እናግዛ
ቸዋለን። ” via Eritrean press @NationalEr Interest

You may also like...

Leave a Reply